Sunday, March 18, 2012

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ 3ኛ አረፉ፡፡


የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ማርቆስ መንበር 117 ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ትናንት መጋቢት 8 ቀን 2004 .. አረፉ፡፡ቢቢሲ የግብፅን ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጠቅሶ እንደዘገበው ቅዱስነታቸው በካንሰር ሕመም ምክንያት 88 ዓመታቸው አርፈዋል፡፡
በሰሜናዊ ግብፅ፣ አስዩት ውስጥ ሐምሌ 27 ቀን 1915 . ሲወለዱ ናዚር ጋይድ የሚል መጠሪያ ከቤተሰባቸው የተሰጣቸው ቅዱስነታቸው፣  ቅስናን ሲቀበሉ አባ እንጦንስ ተብለው ይጠሩ የነበር ሲሆን አቡነ ሲኖዳ የተባሉት 1955 . የክርስትና ትምህርት ኤጲስ ቆጶስ ተብለው በተሸሙበት ወቅት ነበር፡፡
ቅዱስነታቸው ካረፉ በኋላ
ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ የቅብጥ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን 117 ፓትርያርክ ሆነው በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ መንበር ላይ የተሾሙት ከፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ 6 በኋላ ኅዳር 4 ቀን 1964 . ነበር፡፡

ቅዱስነታቸው ካረፉ በኋላ
ቅዱስነታቸው 5ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ የቲዎሎጂ ሴሚናሪ ዲን የሆኑ የመጀመሪያው ፓትርያርክ ሲሆኑ በአገልግሎት ዘመናቸው 3 የአሜሪካን እንዲሁም 1 የጀርመን ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ተቀብለዋል፡፡
ቅዱስነታቸው ሕይወታቸው የትሕርምት፣ የጸሎትና የአገልግሎት እንደነበር የሕይወት ታሪካቸውን የሚዘግቡ ድርሳናት የሚገልጹ ሲሆን ባለፉት 20 ዓመታት የዓለምን ሕዝብ ያስተማሩባቸው 80 መጻሕፍትን ደራሲና የቤተ ክርስቲያኗ ኦፊሴላዊ መጽሔት ኤል-ኬራዛ ዋና አዘጋጅ ነበሩ፡፡
በግብፅ ርዕሰ ብሔር አንዋር ሳዳት ጊዜ አክራሪ ሙስሊሞች በክርስቲያኖች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት መጨመርና መፋፋም ያሳሰባቸው ቅዱስነታቸው በመንግሥቱ ላይ ባነሱት ተቃውሞ፣ 40 ወራት ከመንጋዎቻቸው ተለይተው ወደ ቅዱስ ቢሶይ ገዳም ተግዘው የአባቶቻቸውን በረከት ተካፍለው እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በኋለኛው መሪ ሆስኒ ሙባረክ ዘመን ወደ መንበራቸው ተመለሰው እስከ ዛሬ ድረስ ጠቦቶችን ሲጠብቁ፣ ግልገሎችና በጎችን ሲያሰማሩ ቆይተው አርፈዋል፡፡
በግብፅ ሕዝብ በተለይም በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ተወዳጅ አባት እንደሆኑ የሚነገርላቸው ቅዱስነታቸው በግብፃውያን ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻልና ሰላማዊ ለማድረግ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እንደደከሙ ይመሠከርላቸዋል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ኢትዮጵያን  ሁለት ጊዜ የጎበኙ ሲሆን ከመጀመሪያው ጉብኝታቸው 30 ዓመታት በኋላ 2000 . ሚያዝያ ወር ላይ ያደረጉት ጉበኝት የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነበር፡፡
ቀብር ሥነሥርዓታቸው በዕለተ ሠሉስ የሚፈጸም መሆኑን ተገልጧል ፡
ጸሎታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን፣

 

4 comments:

  1. Ameen, Nebsachewun bimbetachin, Babireham -- ategeb Yanurilin

    ReplyDelete
  2. ጸሎታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን፣
    Amen!
    Amen!
    Amen!
    03/20/2012 @ 8:04AM

    ReplyDelete
  3. የአባታችን በረከታቸው አይለየን፡፡ ጸሎታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን፣

    ReplyDelete