Friday, February 24, 2012

ኪዳነ ምሕረት



ኪዳን የሚለው ቃል ‹‹ቃል›› ከሚለው ጋር እየተዛረፈ በብሉይ ኪዳን 280 ጊዜ ያህል ሲጠቀስ በአዲሰ ኪዳን ደግሞ 32 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ ‹‹ኪዳን›› ቃሉ ‹‹ተካየደ›› ተማማለ፣ ቃል ተገባባ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹‹ምሕረት›› የሚለው ቃል ደግሞ ማብራሪያ ሳያሻው ምሥጢሩ ከነዘይቤው ከግእዝ የተወረሰ ነው፡፡ ስለዚህ ኪዳነ ምሕረት ማለት የምሕረት፣ የይቅርታ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ ኪዳን ከተራ ውሎችና ስምምነቶች የበለጠ ጽኑና ቀዋሚ ነው፡፡ ከፍ ያለ ክብደትም አለው፡፡

‹‹
ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አድርጋለሁ›› ተብሎ በዳዊት መዝሙር እንደተጻፈ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡ ወደፊትም ያደርጋል፡፡ (መዝ88.3) ቃል ኪዳኑም የምሕረት ቃል ኪዳን ነው፡፡

        በቅዱሳን አበውና በቅዱሳት እማት እናቶች ታሪክ፣ ገድልና ድርሳን እንደምናነበው እግዚአብሔር ለቅዱሳን ከመሞታቸው አስቀድሞ ይገለጥላቸውና የምሕረት ቃል ኪዳን ይሰጣቸው ነበር፡፡ የእግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን በቅዱሳኑ ሕይወት ዙሪያ ብቻ የሚያተኩር አይደለም፡፡ ለስማቸው፣ ለመስቀላቸው፣ ለልብሳቸው ገድላቸውን ከትቦ ለያዘ መጽሐፍ፣ አልፎ ተርፎም ለረገጡትና አፈርና ለተጋደሉበት ቦታ ሁሉ ተርፎላቸዋል፡፡ ስለዚህ ልዩ ልዩ ቃል ኪዳን የተገባላቸው ቅዱሳት መካናት ሞልተዉናል፡፡

Sunday, February 19, 2012

ዘወረደ(የዐቢይ ጾም አንደኛ ሳምንት)



ቅድስት ቤተክርስቲያናችን የዐቢይ ጾም የመጀመሪያውን እሁድ ዕለት  “ዘወረደ” በማለት ትጠራዋለች።
እግዚአብሔር በገባዉ ቃልኪዳን መሰረት “…የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ” እንዳለ ሐዋርያዉ ቅዱስ ጳዉሎስ የጠፋዉን አዳም ፍለጋ ከአባቱ እሪና ሳይጎድል ሳይለይ ከሰማይ መዉረዱን የምናዘክርበት በዓል ነዉ። 

ሰዉ የተሰጠዉን የሞት ማስጠንቀቂያ ባለመጠበቁ ፍርድ ተፈርዶበት፣ መዊተ ስጋ መዊተ ነፍስ ነግሶበት፣ በህይወተ ስጋም እያለ በሞት ጥላ ስር የሚኖር እና በሞት ፍርሃት የታጠረ ነበር። ከእግዚአብሔር አንድነት ተለይቶ የተስፋ ቦታዉን ለቆ ከዓለመ መላዕክት ወደ ዓለመ እንሰሳ ተጥሎ የፀጋ ልጅነቱን እና ክብሩን አጥቶ በባርነት ዉስጥ እኩያት ፍትወታት ሰልጥኖበት ይኖር ነበር። (መዝ፡- 18፡4-5) 

Sunday, February 12, 2012

ዐቢይ ጾም


በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ባሕልና ትውፊት  እና ሥርዓት መሠረት በዘንድሮው ዓመት በመጪው ሰኞ የካቲት 12 2004 ( 20 ፌብርዋሪ 2012 ) የሚጀመረው የጾም ወራት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱና ዋነኛው፣ ጌታ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው፡፡ ምእመናን ጌታቸው ያደረገውን ምሳሌ ተከትለው ይጾሙታል፡፡

   ይህ ታላቅ የሆነው የጾማችን ወራት በተለያየ ስያሜ  ይጠራል፡፡
1. ዐቢይ ጾም ይባላል፡፡

ሌሎች አጽዋማት ከቅዱሳን አበው የወረስናቸው የኑሮአቸው ፍሬዎች (ዕብ.13፤7) ሲሆኑ ይኼኛው ግን በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተመሠረተ በመሆኑ ዐቢይ (ታላቅ) ይባላል፡፡ የጌታ ጾም ስለሆነ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች (አርእስተ ኃጣውእ) ድል የተነሡበት፣ ድል የሚነሡበት ጾም ስለሆነም ዐቢይ ጾም ይባላል፡፡


2. ጾመ ሁዳዴ ይባላል፡፡

ሁዳድ ማለት የመንግሥት መሬት፣ የመንግሥት ርስት ማለት ነው፡፡ የመንግሥት ሁዳድ በሚታረስበት ጊዜ፣ አዝመራው በሚሰበሰብበት ጊዜ ልጅ ዐዋቂ ሳይባል የመንግሥቱ ዜጋ ሁሉ ለሥራ ታጥቆ እንደሚነሣ ይህንንም የጌታ ጾም የጌታ ወይም የጌታ ሁዳድ የክርስቶስ ዜጎች የሆኑ ምእመናን ሁሉ ይጾሙታልና ጾመ ሁዳዴ ይባላል፡፡

Wednesday, February 8, 2012

አባ አርሳንዮስ


አባ አርሳንዮስ በ360 ዓ.ም በሮም ተወለደ፡፡ በዘመኑ ትምህርት በሚገባ የተማረና ለሴናተርነትም መዓርግ የደረሰ ሰው ነበር፡፡ የሮሙ ንጉሥ ቴዎዶስየስ ለልዕልት አርቃድዮስ እና ለልዕልት አኖሬዎስ መምህር አድርጎ መድቦት ነበር፡፡ በ394 ዓ.ም የሮምን ቤተ መንግሥት ንቆ ትቶ በድብቅ ወደ እስክንድርያ መጣ፡፡ በመቀጠልም ወደ ገዳመ አስቄጥስ ገብቶ የአባ ዮሐንስ ሐፂር ደቀ መዝሙር ሆነ፡፡ በገዳመ አስቄጥስ አጠገብ በሚገኘው በጴጥራ በምናኔ ይኖር ጀመር፡፡ የታወቁ ሦስት ደቀ መዛሙርት ነበሩት፡- እስክንድር፣ ዞይለስ እና ዳንኤል፡፡ ድሎት የለሽ ኑሮን በመኖር እና በአርምሞው የታወቀ አባት ነው፡፡ በ434 ዓ.ም ገዳመ አስቄጥስ ለሁለተኛ ጊዜ ከጠፋ በኋላ ወደ ትሮኤ ተራራ ወጣ፡፡ እዚያም በ449 ዓ.ም ዐረፈ፡፡

አባ አርሳንዮስ በቤተ መንግሥት በነበረበት ሰዓት ‹ጌታ ሆይ በድኅነት ጐዳና ምራኝ› እያለ ይጸልይ ነበር፡፡ እናም ‹አርሳንዮስ ›ሆይ ከሰዎች ተለይ ያን ጊዜ ድኅነትን ታገኛለህ› የሚል ድምጽ ሰማ፡፡ ወዲያውም ቤተ መንግሥቱን ትቶ ወደ ገዳም ገባ፡፡

Sunday, February 5, 2012

የኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ፈተና በሳዑዲ አረቢያ


35 ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች የልደትን በዓል በማክበር ላይ እንዳሉ በቁጥጥር ሥር ውለው ተጠርፈው ወደሀገራቸው ሊላኩ ነው ፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው ( http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-16808429)

Some 35 Ethiopian Christians face deportation from Saudi Arabia for "illicit mingling", the global rights body Human Rights Watch (HRW) says.
Police arrested the group - including 29 women - after raiding a prayer meeting in the second city of Jeddah.
The women were subjected to strip searches and the men beaten and called "unbelievers", according to HRW.
In 2006, the Saudi government promised to stop interfering with private worship by non-Muslims.
The group was arrested in a private home as they gathered to pray during the run-up to Christmas, celebrated by Ethiopian Orthodox Christians on 7 January.

Saturday, February 4, 2012

የተባበሩት አረብ ኢሚሬት ሀገረ ስብከት

አቡዳቢ ፤ ዱባይ እና አላይን ፤ ቅኝት በፎቶ
ዘገባውን እመለስበታለሁ 












ክርስቲያን ወገኖቻችንን በሄዱበት መጽናኛ ይሆናቸው ዘንድ ቤተክርስቲያን መኖሩ ሁሉን ላዘጋጀ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው ፡፡

የበረሃውን ዋዕይ ሳይሰቀቁ በማገልገል ላይ ላሉት

ብፁዕ አባታችን አቡነ ድሜጥሮስ
የሊባኖስ ፤ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ

መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ሰይፈ ገብርኤል የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ እና የአቡዳቢ ደብረሰላም መድኃዓኔለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ

መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ገሪማ የዱባይ ቻርጃ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ
መልአከ ኃይል ቆሞስ አባ ወልደገብርኤል የአላይን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ
እንዲሁም አገልጋይ ዲያቆናት እና ምዕመናን በሙሉ
ረጅም ዕድሜ እና ጤና ይስጥልን
አሜን
ከአቡዳቢ - የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ