Friday, November 22, 2013

የገና ጾም - ጾመ ነቢያት

ነቢዩ ኢሳይያስ
ነቢያት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ፣ ወደ ግብፅ ስለ መሰደድ፣ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለመጠመቅ፣ በትምህርተ ወንጌል ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ጸዋትወ መከራ ስለመቀበሉና ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ትንሣኤው፣ ስለ ዕርገቱና ስለ ዳግም ምጽአቱ ትንቢት ተናግረው አላቆሙም፤ ለአዳም የተሰጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት ትንቢት ፍፃሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑትም እንጂ፡፡ በየዘመናቸው «አንሥእ ኃይለከ፣ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሳ እጅህንም ላክ» እያሉ ጮኹ፡፡ በጾምና በጸሎት ተወስነውም ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት ቆጠሩ፡፡ ለምሳሌ ነቢዩ ኤርምያስ ስለ ሥጋዌው ትንቢት በተናገረ በ446 ዓመት ጌታችን ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኗል፡፡
አባታችን አዳም እና እናታችን ሔዋን ዕፀ በለስ በመብላታቸው ምክንያት ከገነት እንደተባረሩነቢያት ተስፋው በዘመናቸው ተፈጽሞ በዓይነ ሥጋ ለማየት ባይችሉም እግዚአብሔር «የማያደርገውን ይናገር የተናገረውን አያስቀር» ብለው አምነው ከወዲሁ ተደሰቱ፡፡ለዘመነ ሥጋዌ ቅርብ የነበሩት እነ ኢሳይያስ ጾሙ እንዴት መፈጸም እንዳለበትተናግረዋልም፡፡ ኢሳ 58-1፡፡

በመሆኑም በጌታ ልደት ትንቢተ ነቢያት ስለ ተፈጸመበት ይህጾም «የነቢያት ጾም» ይባላል፡፡ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰውልጆች ተስፋ የተመሰከረበት የምሥራቹ የተነገረበት ስለሆነም «ጾመ ስብከት» ይባላል፡፡
                     ነቢዩ ኤርምያስ
ሰው በኃጢአት ቢወድቅም ፈጣሪው ሊያነሳው፤ ቢጠፋ ሊፈልገው እንደሚመጣ በተስፋ ሲጠብቀው ወልደ አምላክ ሰው መሆኑ የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡ ስለዚህ አዳም የልደቱን ነገር በትንቢት መነፅርነት ሲመለከተው /በነቢያቱ ትምህርትና ስብከት/ በሚኖርበት ዓመተ ፍዳ የምሥጢረ ሥጋዌ  ብርሃን ከሩቅ ሲመለከተው ኖረ፡፡ ምሥጢረ ሥጋዌን በትንቢት መነፅርነት ማየቱም መከራውን እንዲቋቋመው የተስፋ ስንቅ ሆነው፡፡
ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር በጸጋ እንደተወለዱ በማመን ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር ከሚገልጡባቸው ነገሮች አንዱ ጾም ነው፡፡ ጾም የፍቅር ስጦታ ከመሆኑ በተጨማሪ ታዛዥነትንና የገቡትን ቃል ኪዳን ጠባቂነትንም ማሳያ ነው፡፡ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አርአያ ተፈጥሯአል፡፡ ኃጢአት ሠርቶ የእግዚአብሔር አርአያነቱን ቢያጠፋውም እግዚአብሔር ግን በአርአያው ሲፈጥረው ምን ያህል እንደሚወደው ማረጋገጫ ስለነበር በኃጢአት ሲወድቅም እንደወጣ ይቅር ሳይል ሊፈልገው መጣ፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሊፈልግ የመምጣቱ ተስፋ የተነገረበትንና ሱባኤ የተቆጠረበትን ዕለት ለማየት በመናፈቅ ከቀረበው መሥዋዕት አንዱ ጾም ነበር፡፡
  ጾም ሰው ለእግዚአብሔር ያለውን ፍቅር እና ታዛዥነት መግለጫና ማረጋገጫ ብቻ ሳይሆን ሲወድቁ መነሻ ከብልየት (እርጅና )መታደሻ፥ ከኃጢአት ቆሻሻ መታጠቢያ /ከንስሓ ጋር አብሮ ሲፈጸም/ ሳሙናም ነው፡፡ ሊቀ ነቢያት ሙሴ በሲና ተራራ ላይ እግዚአብሔር ወደ ነበረበት ጨለማ የገባው፣ አስፈሪውን መብረቅና ነጐድጓድ የተቋቁመው፣ ጨለማውን አልፎ የሰው ልጅ ያልሠራትን ሰማያዊ መቅደስ የተመለከተውና ወደ ዓለቱ ድንጋይ የቀረበው ራሱን ለእግዚአብሔር በጾም በመቀደስ ጭምር ነው፡፡ /የወገን ፍቅርና ለእግዚአብሔር ታዛዥነቱ እንዳለ ሆኖ/፡፡
ጾም እነዚህንና መሰል መንፈሳዊ በረከትን ስለሚያስገኝ ክርስቲያኖች ይመጣላቸው ዘንድ ይናፍቁታል፡፡ ከእነዚህ የሚናፈቁ አጽዋማት መካከል አንዱ ጾመ ነቢያት ነው፡፡ ጾመ ነቢያት የሚባለው ጾመ ገና፣ ጾመ ማርያም፣ ጾመ አዳም፣ ጾመ ፊልጶስ ተብሎ ይጠራል፡፡
 ጾመ ነቢያትም ሆነ ሌሎች አጽዋማት ሲደርሱ ክርስቲያኖች የሚደሰቱት ጾም የሥጋ ፈቃድ እንዳይሰለጥንባቸው፣ ቁስለ ሥጋን በማከም፣ ቁስለ ነፍስን ስለሚፈውስላቸው ነው፡፡  ጾም የቁስል መፈወሻ ኃይለ መዊዕም(ድል ማድረጊያ) ይሆናል፡፡ ከሥጋም ከመንፈስም ተቆራኝቶ ሰውን ወደ ጥፋት የሚወስድን ክፉ መንፈስ ለማራቅም ይጠቅማል፡፡
ጾም የሥጋን ምኞት እስከመሻቱ ቆርጦ የሚጥል፣ ለመንፈስ ልዕልና የሚያበቃውን መሳሪያ የሚያስታጥቅ ነው፡፡ ክርስቲያን ይህን መሰል መንፈሳዊ የጦር እቃ እንዳይለየው አጥብቆ ይለምናል፡፡ የጦር ልምድ እንደሌለው ወታደር ጠላቱን የሚቋቋምበት የጦር ትጥቅ ሳይዝ አውላላ ሜዳ ላይ  ባዶውን አይቆምም፡፡ መንፈሳዊ ውጊያን በሥጋዊ ጥበብ ማሸነፍ ስለማንችል ነው አበው ፍቅረ አጽዋማትን በአስተምህሮአቸውና በሕይወታቸው የሰበኩልን፡፡
ጾም እነዚህንና መሰል መንፈሳዊ በረከትን ስለሚያስገኝ ክርስቲያኖች ይመጣላቸው ዘንድ ይናፍቁታል፡፡ ከእነዚህ የሚናፈቁ አጽዋማት መካከል አንዱ ጾመ ነቢያት ነው፡፡ ጾመ ነቢያት የሚባለው ጾመ ገና፣ ጾመ ማርያም፣ ጾመ አዳም፣ ጾመ ፊልጶስ ተብሎ እንደሚጠራ መምህር ቃኘው ወልዴ ጾምና ምጽዋት በተሰኘው መጽሐፋቸው ገልጠውታል፡፡
 ጾመ ነቢያት ለአዳም የተነገረው ትንቢት፣ የሚጠበቀው ሱባኤ እንደደረሰ የሚያበስር በመሆኑ ጾመ አዳም ይባላል፡፡ አዳም ቢበድልም ንስሐ ገብቶ በማልቀሱ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ ብሎ የተነገረው ተስፋ መድረሱን፣ ምሥጢረ ሥጋዌ እውን ሊሆን መቃረቡን የሚያስረዳ ጾም ነው፡፡
ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው፣ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢት ተመልክተው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡፡ ይህ ጾም የራቀውን አቅርቦ፣ የረቀቀውን አጉልቶ ስላሳያቸው እስከሞት ድረስ ቢደበደቡም፣ ከመከራው ጽንአት የተነሣ ዋሻ ለዋሻ፣ ፍርኩታ ለፍርኩታ ቢንከራተቱም፣ የፍየል ሌጦ ለብሰው ቢዞሩም የተስፋው ቃል ሁሉን አስረስቶአቸው ከትንቢቱ ባለቤት ጋር በመንፈስ ተዋሕደው አልፈዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ሐዋርያት ምን ሠርተን የክርስቶስን ልደት እንቀበለው ብለው ስለጾሙት ጾመ ሐዋርያት ተብሎ ይጠራል፡፡

ጾመ ነቢያት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ወልደ አብን ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ በማለት ጾማዋለችና ጾመ ማርያም ይባላል፡፡ ይህን ያለችው በመደነቅ፣ አንድም በትሕትና አንድም ቀደምት አባቶቿ ነቢያት ሲጾሙት አይታ ጾማዋለች፡፡ እንዴት ፀንሼ እወልደዋለሁ ማለት ጥርጥር ሳይሆን ተደሞ፣ መደነቅ የነገረ ልደቱን አይመረመሬነት ይገልጻል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ትሕትና ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ቅድስናዋን አይቶ በብስራተ መልአክ አማካኝነት ክርስቶስን እንደምትወልድ ቢነግራትም የትሕትና እናት ናትና ምን ሠርቼ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ እችለዋለሁ ስትል ጾማዋለች፡፡
ይህ ጾም ጾመ ፊልጶስም ይባላል፡፡ ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ ሲያስተምር በሰማዕትነት ሲሞት አስከሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስከሬን እንዲገልጽላቸው ከኅዳር አስራ ስድስት ጀምረው ሲጾሙ በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስከሬን ቢመልስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፡፡  ጾምን ትእዛዝ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን የፍቅርና የበረከት ምንጭ በመሆኑ ጭምር ደስ እያለን ብንጾመው የቅዱሳኑ በረከት ያድርብናል፡፡

ጾሙን ጾመ ሥርየት ፤ ጾመ መድኃኒት ያድርግልን ፤
ለብርሃነ ልደቱ በሰላም እና በጤና ያድርሰን ፤
ጾመን ለማበርከት ያብቃን - አሜን ፡፡
ዋቢ
ማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ
ጾምና ጸሎት መጽሐፍ

41 comments:

 1. ጾሙን ጾመ ሥርየት ፤ ጾመ መድኃኒት ያድርግልን ፤
  ለብርሃነ ልደቱ በሰላም እና በጤና ያድርሰን ፤
  ጾመን ለማበርከት ያብቃን - አሜን ፡፡kalehiwot yasemalin!betena,betsega yitebiklin!

  ReplyDelete
 2. kale hiwot Yasemalin d/n

  ReplyDelete
 3. ሆሳዕናሆሳዕናNovember 20, 2012 at 10:11 AM

  በእውነት በእውነት....እመቤታችን ትጦመው እንደነበር አስተውዬው አላውቅም ነበር....ልቤ በሲቃ ዘለለ በእውነት....የጌታችን እናት እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ እንደጦመችው እያሰብኩ እንድጦም የቅዱሳን አምላክ ይርዳኝ፡፡ ወይጉድ....

  የእመቤታችንን የምህረት ቃል ያሰማልን!

  ReplyDelete
 4. thank you so much d/n keep going

  ReplyDelete
 5. Kale hywot yasemalen! If you don't mind I have got one question which is you say this fasting season (Tsome Nebiyat) also called Yehawariyat Tsome because you did say Apostles did fast it as well in remembering Christ Birth. My question is here to my knowledge Hawariyat didn’t come before Christ was born therefore, how can we call this fast Tsome hawariya? The way I forward or interpret it could be wrong but the whole idea is I want understand it clearly? Thanks for your time.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I think the write wants to say it is fasting of Apostles in the reason that the apostles fasted it after Jesus christ ascention and they fasted before celebrating Jesus christ Birth Day

   Yes You are correct that The Apostles werenot present before the Birth Of jesus Christ - It is to my View

   Delete
 6. God bless you. I didn't know about all those informations.
  Really God bless you.
  Habtay......

  ReplyDelete
 7. kale hiwot yasemalin,yeagelgilot zemenhin yarzimlih

  ReplyDelete
 8. kalehiwot yasemalene!

  ReplyDelete
 9. kale hiwote yasemalen wonedemachen.ersu wagahen yekefelehe.

  ReplyDelete
 10. thank you for the article.

  ReplyDelete
 11. Kale hiwot yasemalin! betena behiwot yitebikilin! Endezih Ye Egziabhern kal lenebsachin yemitimegibatin amlak bebereketu yigobgnih!

  ReplyDelete
 12. Kale Hiwot yasemalin Memhir.

  ReplyDelete
 13. so meche new yemigebawu tsomu?

  ReplyDelete
  Replies
  1. It will start on Kidame ( Saturday ) Hidar 15 2005 / November 24 2012

   Delete
 14. Kale Hiwot yasemalin Memhir.Berta!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear Melaku

   Kale Hiywoyt Yasemalin
   Yageliglot Zemenihin Yarzimilin, Beratlin

   Delete
 15. እናመሰግናለን!!!!!

  ReplyDelete
 16. ርብቃ ከጀርመንNovember 23, 2012 at 3:15 PM

  እንኩዋን አብሮ አደረሰን ቃለሂወት ያሰማልን ጾመን ለመጠቀም ያብቃን ከምንም በላይ የቤተክርስቲያናችንን ችግር እያሰብን እድንጾመው ይሁን የድንግልማርያም ልጅ ሀገራችንንይጠብቅልን አሜን

  ReplyDelete
 17. yebele new adise negre agegnchalu

  ReplyDelete
 18. የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አርአያ ተፈጥሯአል፡፡ ኃጢአት ሠርቶ የእግዚአብሔር አርአያነቱን ቢያጠፋውም እግዚአብሔር ግን በአርአያው ሲፈጥረው ምን ያህል እንደሚወደው ማረጋገጫ ስለነበር በኃጢአት ሲወድቅም እንደወጣ ይቅር ሳይል ሊፈልገው መጣ፡፡

  ReplyDelete
 19. አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን እግዚአብሔር አምላክ ጤና ከእድሜ ጋር ይስጥልን

  ReplyDelete
 20. +++ በሥመ ሥላሴ +++
  የህይወትን ቃል እግዚአብሔር ያሰማልን! በጣም ጠቃሚ መረጃ ነው ያደረሳችሁን፤ እንዲሁ እንግዚአብሔር ይደረስላችሁ፡፡
  ይህን ፆም በፀሎት በስግደት እናድርግ፤ የምንፀልየው ፀሎት ከልባችን ይሁን፤ በንስሀ የምንመለስበት ጊዜም ይሁንልን፡፡ አሜን እግዚአብሔር ሆይ እርዳን!!!
  እግዚአብሔር ለአዳምና ለዘሩ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ ያለውን ቃል ይፈፅም ዘንድ ጌታ በቤተልሔም ተወለደ!
  በሰላምና በጤና ለብርሀነ ልደቱ ያድረሰን አሜን

  ReplyDelete
 21. qale heyeweten yasemalen edeme,tena yesetelen

  ReplyDelete
 22. ye agelglot edmehen yarzmlh memher

  ReplyDelete
 23. qale kihidet yasemalin

  ReplyDelete
 24. ኣሜን እግዚያብሔር ይለመነን የሰላም የፍቅር የመዳን ዘመን ይሁንልን

  ReplyDelete
 25. ቃለ ህይወት ያሰማልን ።

  ReplyDelete
 26. ቃለ ህይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete
 27. D/N kedem bilo biweta tiru neber.
  Kale hiwot yasemalin

  ReplyDelete
 28. Ende ke Mariyam ke segawa sega ke nefsua nefes wesede yemil metshaf kidus lai ale ende? Kesemai yewerede Injera ene negn yehm injera segaye newu newu Geta Eyesus Kirstos yalew. Ebakehn wondeme kale negeren.

  ReplyDelete
 29. ጾም የሥጋን ምኞት እስከመሻቱ ቆርጦ የሚጥል፣ ለመንፈስ ልዕልና የሚያበቃውን መሳሪያ የሚያስታጥቅ ነው፡፡ ክርስቲያን ይህን መሰል መንፈሳዊ የጦር እቃ እንዳይለየው አጥብቆ ይለምናል፡፡ የጦር ልምድ እንደሌለው ወታደር ጠላቱን የሚቋቋምበት የጦር ትጥቅ ሳይዝ አውላላ ሜዳ ላይ ባዶውን አይቆምም፡፡ መንፈሳዊ ውጊያን በሥጋዊ ጥበብ ማሸነፍ ስለማንችል ነው አበው ፍቅረ አጽዋማትን በአስተምህሮአቸውና በሕይወታቸው የሰበኩልን፡፡
  Dear brothers and sisters,
  Don't we believe that we have to fast???

  ReplyDelete
 30. kalehywet yasemaln. e/r behywet betena yitebklin.continiw in this way

  ReplyDelete

 31. Ewnet buzu neger awekalehu. kalehiwet yasemaln. Amen!!

  ReplyDelete
 32. kalehiwot yasemaln yagelglot zemenhn ybarkln,egzihabier wagahan ykfelh

  ReplyDelete
 33. ቃለ ህይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete