Monday, July 25, 2011

አርባ አራቱ ታቦታተ ጎንደር

መግቢያ
ጎንደር በኢትዮጵያ የመንግሥት ታሪክ ከአክሱምና ላሊበላ ቀጥሎ ትልቋ የመንግሥት ማዕከል ነበረች፡፡ በመንግሥት ማዕከልነት የተቆረቆረችው በአፄ ፋሲል (1624-1660 ዓ.ም) ነው፡፡

ጎንደር የመንግሥት ማዕከል ብቻ ሳትሆን በጊዜው የመንፈሳዊ ትምህርት ማዕከልም ነበረች፡፡ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የመጻሕፍት እና የአቋቋም ትምህርት ይበልጥ የተስፋፋውና በየሀገሩ ያሉ ሊቃውንት በመናገሻ ከተማዋ ጎንደር በነገሥታቱ አማካይነት በመሰባሰባቸው ሲሆን ከዚያን ዘመን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ መንፈሳዊ ትምህርት በስፋት የሚሰጥባት የትምህርት ማዕከል ለመሆን ችላለች፡፡
በአሁኑ ሰዓት በሰሜን ጎንደር በሚገኙ 21 ወረዳዎች ከ2117 ያላነሱ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት ሲኖሩ በዋና ከተማዋ ደግሞ ከ92 ያላነሱ አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ፡፡

በአብነት ት/ቤት ረገድም የመጻሕፍት ጉባዔያት፣ የአቋቋም ምስክር፣ የቅኔ አብያተ ጉባዔያት እንዲሁም የዜማ ት/ቤቶች በከተማዋ እና በዙሪያዋ በሚገኙ ወረዳዎች ይገኛሉ፡፡ (ስለአብነት ት/ቤቶች በሚቀጥሉት ጊዜያት እመለስበታለሁ፡፡)

44 የመሆናቸው ምሥጢር
በአሁኑ ሰዓት በከተማዋ ከ92 ያላነሱ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም በአብዛኛው ስማቸው ደጋግሞ የሚነሳው የ44ቱ ብቻ ነው፡፡ በተለያየ ጊዜ በተለይም ጎንደርን ከማያውቁት ሰዎች ጋር ባደረኩት ውይይት 44ቱን ታቦታተ ጎንደርን በተመለከተ የተለያየ ግንዛቤ እንዳለ ለመገንዘብ ችያለሁ፡፡
አንዳንዶቹ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙት የአብያተ ክርስቲያናት ታቦታት ስያሜ ብዛት ሲመስላቸው ሌሎቹ ደግሞ በጎንደር በጥምቀት በዓል ወደጥምቀተ ባህር የሚወርዱትን ብቻ ስሉ ይደመጣሉ፡፡ ጎንደር ከተማ እየኖሩም የ44ቱን ዝርዝር በውል የማያውቁ ብዙ ሰዎች ገጥመውኛል፡፡
ጎንደር ደብረብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን
አርባ አራቱ ታቦታተ ጎንደር ከቤተ መንግሥቶቹ በተጨማሪ ታሪካዊዋ ጎንደር የምትታወቅበት ቅርስ ነው፡፡ ጎንደር ከተማ በአፄ ፋሲል የመንግሥት ከተማ ከመሆኗ አስቀድሞ የአካባቢው ነዋሪዎች ተክለዋቸው የነበሩ አብያተ ክርስቲያናት ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ቀሐ ኢየሱስ፣ አርባዕቱ እንስሳ፣ አበራ ጊዮርጊስ፡፡

ጎንደር የመንግሥት ከተማ ከሆነችበት እስከ ጎንደር ዘመን ማክተሚያ ፈፃሜ መንግሥት አፄ ተክለ ጊዮርጊስ (1772-1777) ድረስ 18 ነገሥታት የነገሱ ሲሆን እነዚህም አብዛኛዎቹ አብያተ ክርስቲያናትን አሠርተዋል፡፡

እንግዲህ 44 የሚባሉት አብያተ ክርስቲያናት ጎንደር የመንግሥት ከተማ ከመሆኗ አስቀድሞ የተተከሉበትን ጨምሮ እስከ ፈፃሜ መንግሥት ተክለ ጊዮርጊስ (1772-1777) ድረስ የተተከሉትን ብቻ ሲሆን ቁጥራቸውም 44 ነው፡፡

ከዚያ ወዲህ ከዘመነ መሣፍንት እስከ አሁን የተተከሉ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም ከ44ቱ የሚቆጠሩ አይደሉም፡፡ በአጠቃላይ አርባአራቱ ታቦታተ ጎንደር በጎንደር ዘመን በጎንደር ከተማና አካባቢው የሚገኙና የነበሩ 44 አብያተ ክርስቲያናት ጥቅል ስም ነው፡፡
ይህም ማለት አሁን ባለው የጎንደር ከተማ ክልል እና ዙሪያውን በሚገኙ አዋሳኝ የገጠር ቀበሌዎች ለምሳሌ፣ ጠዳ፣ ፈንጠር፣ ብላጅግ፣ ደፈጫ እና በመሳሰሉት ቦታዎች የሚገኙ አጠቃላይ የአድባራት ቁጥር ነው፡፡

በጎንደር ዘመን የነገሡ ነገሥታት
ተ.ቁ
የንጉሡ ስም
ዓመተ ምህረት
የዓመት ብዛት
1
አፄ ሠርጸ ድንግል
1553-1587
34
2
አፄ ያዕቆብ
1587-1594
7
3
አፄ ዘድንግል
1594-1595
1
4
አፄ ሱስንዮስ
1595-1623
28
5
አፄ ፋሲል
1623-1659
36
6
አፄ ዮሐንስ (ፃድቁ)
1659-1674
15
7
አፄ ኢያሱ (አድያም ሰገድ)
1674-1698
24
8
አፄ ተ/ሃይማኖት (ርጉም)
1698-1700
2
9
አፄ ቴዎፍሎስ
1700-1703
3
10
አፄ ዮስጦስ
1703-1708
5
11
አፄ ዳዊት (አድባርሰገድ)
1708-1713
5
12
አፄ በካፋ (መሢህ ሰገድ)
1713-1722
9
13
አፄ ኢያሱ 2
1722-1747
25
14
አፄ ኢዮአስ
1747-1762
15
15
አፄ ዮሐንስ 2ኛ (ዘዋሕድእዴሁ)
1762-1763
1
16
አፄ ተ/ሃይማኖት (መናኔ መንግሥት)
1763-1770
7
17
አፄ ሰሎሞን
1770-1772
2
18
አፄ ተ/ጊዮርጊስ (ፈፃሜ መንግሥት)
1772-1777
5

ተካያቸው
አርባአራቱ ታቦታተ ጎንደር የተተከሉት በነገሥታት፣ በመሣፍንት እና በባላባት ወይም በመንጣሪ ሲሆን በቁጥር ደረጃ በነገሥታት የተሠሩት ይበልጣሉ፡፡
አፄ ፋሲል እና መናኔ መንግሥት ተ/ሃይማኖት ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ሲያሰሩ የሀገሬው ሰው ደግሞ 10 አብያተ ክርስቲያናትን እንዲተከሉ አድርጓል፡፡ የአፄ ፋሲል አባት አፄ ሱስኒዮስ አዘዞ ተ/ሃይማኖትን የተከሉ ሲሆን ዳግሚት ደብረሊባኖስ ተብላ በነገሥታቱ ዘመን የዕጨጌው መቀመጫ ይኽው ደብር ነበር፤ የደብሩ አለቃ የማዕረግ ስምም እንደ ደብረሊባኖስ ገዳም ፀባቴ ነው፡፡ አፄ ፋሲልና አፄ ሱስንዮስ የተቀበሩትም በዚሁ ደብር ሲሆን መቼና እንዴት አጽማቸው ፈልሶ እንደሔደ የጽሑፍ ማስረጃ ማግኘት ባልችልም በአሁኑ ሰዓት ግን ከጣና ገዳማት አንዱ በሆነው በዳጋ እስጢፋኖስ የሁለቱ ነገሥታት አጽም ይገኛል፡፡ (ስለ እጨጌ፣ አዘዞ ተ/ሃይማኖት እና ዳጋ እስጢፋኖስ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ፡፡)
በዳጋ እስጢፋኖስ የሚገኘው የአጼ ሱሲኒዮስ እና የልጃቸው አጼ ፋሲል አጽም

መተዳደሪያቸው
በነገሥታቱ እና በመሣፍንቱ የተሠሩት አብያተ ክርስቲያናት አገልጋዮች ተተክለውባቸው ወይም ተመድበውላቸው ለመተዳደሪያ የአካባቢው ቀበሌ እየተከፋፈለ ይሰጣቸዋል፡፡ ይህም ሪም ይባላል ይህም ማለት የዚያ አካባቢ ነዋሪ በዓመት እህል እየሠፈረ ለካህናቱ መተዳዳሪያ እንዲያመጣላቸው ነገሥታቱ አካባቢያዎቹን እየከፋፈሉ ይሠጣሉ፡፡ ለምሳሌ የአደባባይ ተ/ሃይማኖት ሪም በበለሳ ወረዳ ሰፊ መሬት፣ የአደባባይ ኢየሱስ ሪም በጐርጐራ፣ በቡቻራ፣ በብችኝ፣ በማንጌ፣ በዋርሄ ነበር፤ የአጣጣሚ ሚካኤል ሪም በደንቢያ ነበር፡፡
አካባቢው ነዋሪ እና በባላባት የተተከሉት አድባራት ግን ምዕመናን አሥራት በማውጣት የመቀደሻ ንዋያተ ቅድሳቱን ፤ዕጣን ፤ ጧፍ እና ሌሎችንም ለቤተክርስቲያን በማበርከት አገልግሎት ይሰጡ ነበር ፡፡ ዛሬ በገጠር እንዳሉት ካህናት አብዛኛዎቹ አራሾች እና ገበሬዎች ስለሆኑ እያረሱ የሚቀድሱ፤ እየቀደሱ የሚያርሱ አገልጋዮች ነበሩ ዛሬም አሉ ፡፡

የአድባራት የማዕረግ ስም
እስከ አፄ አድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመን የተሰሩት አብያተ ክርስቲያናት የማዕረግ ስም ሳይኖራቸው በተሰሩበት አካባቢ በሚተከሉበት ወቅት ባጋጠመ ክስተት እና በታቦቱ ስም ይጠሩ ነበር፡፡  ለምሳሌ፡- ቀሐ ኢየሱስ፣ አበራ ጊዮርጊስ፣ አባ እንጦንስ፣ ፊት አቦ፣ ግምጃቤት ማርያም
ከአፄ ኢያሱ አድያም ሰገድ በኋላ ግን ለጎንደር አድባራት ሥርዓተ አስተዳደር ወጥቶ ደብሮችን በደረጃ መለየትና የማዕረግ ስም መስጠት ስለተጀመረ በነገሥታት የተሠሩት የማዕረግ ስም እየተሰጣቸው በነበራቸው ላይ ተጨምሮ ይጠሩበት ጀመር፡፡ ለምሳሌ፡- መካነ ነገሥታት ግምጃ ቤት ማርያም፣ ርዕሠ አድባራት አደባባይ ኢየሱስ እና ሌሎችም ፡፡


የአርባ አራቱ ታቦታተ ጎንደር ዝርዝር

ተ.ቁ
የደብሩ ስም
የተካዩ ስም
የደብሩ አለቃ ስም
1
አዘዞ ተ/ሃይማኖት
አፄ ሱስንዮስ
ፀባቴ
2
ፊት አቦ
አፄ ፋሲል
ሊቀ ዲያቆን
3
ፊት ሚካኤል
አፄ ፋሲል
ሊቀ ዲያቆን
4
አደባባይ ኢየሱስ
አፄ ፋሲል
ጽራግ ማሠሬ
5
ግምጃ ቤት ማርያም
አፄ ፋሲል
ሊቀ ማእምራን
6
እልፍኝ ጊዮርጊስ
አፄ ፋሲል
ሊቀ ማእምራን
7
መ/መ/መድኃኔዓለም
አፄ ፋሲል
ሊቀ ማእምራን
8
አቡን ቤት ገብርኤል
አፄ ፋሲል
መልአከ ምህረት
9
ፋሲለደስ
አፄ ሰሎሞን
ሊቀ ድማህ
10
አባ እንጦንስ
ፃድቁ ዮሐንስ
መልአከ ምህረት
11
ጠዳ እግዚአብሔር አብ
ፃድቁ ዮሐንስ
መልአከ አርያም
12
አርባዕቱ እንስሳ
አቤቶ አርምሐ

13
ቀሐ ኢየሱስ
የአገሬው ትክል

14
አበራ ጊዮርጊስ
የአገሬው ትክል

15
አደባባይ ተክለሃይማኖት
አዲያም ሰገድ ኢያሱ
ቄስ አፄ
16
ደብረ ብርሃን ሥላሴ
አዲያም ሰገድ ኢያሱ
መልአከ ብርሃናት
17
ዳረገንዳ ኤዎስጣቴዎስ
አድባር ሰገድ ዳዊት
ሊቀ ጉባዔ
18
አጣጣሚ ሚካኤል
አድባር ሰገድ ዳዊት
መልአከ ገነት
19
ጐንደር ሩፋኤል
አፄ በካፋ
መልአከ ፀሐይ
   20
ደፈጫ ኪዳነ ምህረት
አፄ በካፋ
መልአከ ህይወት
   21
ቅ.ዮሐንስ መጥምቅ
ራስ ወልደ ልዑል
መልአከ ጽጌ
   22
ጐንደር ልደታ ማርያም
አፄ ዮስጦስ
አለቃ
   23
ሠለስቱ ምዕት
አፄ ቴዎፍሎስ
መልአከ ሰላም
   24
ጎንደር በአታ ለማርያም
መናኔ መንግሥት ተ/ሃይማኖት
መልአከ ኃይል
   25
ወ/ነጐድጓድ ዮሐንስ
መናኔ መንግሥት ተ/ሃይማኖት
መልአከ ተድላ
   26
ጐንደር ቂርቆስ
መናኔ መንግሥት ተ/ሃይማኖት
ሊቀ አእላፍ
   27
ጐንደር ሐዋርያት(ጴጥሮስ ወጳውሎስ )
መናኔ መንግሥት ተ/ሃይማኖት
አለቃ
   28
ፈንጠር ልደታ
መናኔ መንግሥት ተ/ሃይማኖት
አለቃ
   29
ሰሖር ማርያም
መናኔ መንግሥት ተ/ሃይማኖት

   30
ወራንገብ ጊዮርጊስ
መናኔ መንግሥት ተ/ሃይማኖት
አለቃ
   31
ምንዝሮ ተ/ሃይማኖት
አፄ ሠርፀ ድንግል
አለቃ
   32
ደ/ፀሐይ ቊስቋም
እቴጌ ምንትዋብ
መልአከ ፀሐይ
   33
ደ/ምጥማቅ ማርያም
ፈፃሜ መንግሥት ተ/ሃይማኖት
ዐቃቤ ሰዓት
   34
አባ ሳሙኤል
ፈፃሜ መንግሥት ተ/ሃይማኖት
አለቃ
   35
ጐንደሮች ማርያም
የአገሬው ትክል
አለቃ
   36
ጐንደሮች ጊዮርጊስ
የአገሬው ትክል
አለቃ
   37
አባ ጃሌ ተ/ሃይማኖት
ደጃች ወንድወሰን
አለቃ
   38
ዐቢየ እግዚእ.ኪ/ምህረት
ራስ ገብሬ

   39
ብላጅግ ሚካኤል
የአገሬው ትክል

   40
አሮጌ ልደታ
የአገሬው ትክል

   41
ጫጭቁና ማርያም
የአገሬው ትክል

   42
ጋና ዮሐንስ
የአገሬው ትክል

   43
ራ ሚካኤል
የአገሬው ትክል

   44
ዳሞት ጊዮርጊስ
የአገሬው ትክል


ጎንደር ደብረብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን በስተጀርባ ዕይታ

ከዚህ በላይ ያለው ሠንጠረዥ የ44ቱን ታቦታተ ጎንደር ዝርዝር የያዘ ሲሆን ከ44ቱ አድባራት መካከል በአሁኑ ሰዓት የሌሉ ስድስት ናቸው፡፡
የአድባራቱ የኪነ ሕንፃ ውበት ምን ይመስላል? አድባራቱ ምን ችግር ገጠማቸው? እነዚህ የጠፉት አድባራት እነማን ናቸው? በአሁኑ ሰዓት ባለው የከተማ ክልል የት ቦታ ላይ ይገኙ ነበር ? የሚለውን ጥያቄ ሚቀጥለው ክፍል እንመለከተዋለን፡፡
ይቆየን

36 comments:

  1. BERTULIN. AMLAK YABERTACHIHU.

    ReplyDelete
  2. BRAVE.KEEP IT UP!!!!!!!!

    ReplyDelete
  3. Bewunetu tilik jimaro new fitsamewun yasamirilin !!

    ReplyDelete
  4. ዲ.ን መላኩ….ለጽሁፍህ እግዚአብሄር ይስጥልን…የልደታ አለቃ መልዓከ ስብሃት አይደለም እንዴ የሚባለው…አንተ ግን …አለቃ ይባላሉ ብለሃል…በጊዜ ሂደት ተቀይሮ ይሆን እንዴ

    ወልደ ኤስድሮስ ዘልደታ

    ReplyDelete
  5. እስካሁን ከምከታተላቸው ብሎጎች ተጨማሪ ይህን በማዬቴ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል።
    እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን። በርታ።

    ReplyDelete
  6. I like it ,need to get reporters and and if you include refences(live references too -Abatoch) that will be nice and will be library in the future. Share websites to each other.


    http://debelo.org/

    http://www.zeorthodox.org/

    http://www.melakuezezew.info/

    http://www.kesisyaredgebremedhin.com/

    http://www.adebabay.com/

    http://www.betedejene.org/

    http://www.aleqayalewtamiru.org/

    http://www.mahletzesolomon.com/

    http://degusamrawi.blogspot.com


    http://www.tewahedomedia.org

    http://www.eotc-mkidusan.org/site/

    http://suscopts.org/

    http://www.dejeselam.org/

    http://mosc.in/

    ReplyDelete
  7. omg thanks to God and diacomn melaku kale hiwet yasemalin fitamehn yasamre ageliglothn yibark
    selam
    u.s.a

    ReplyDelete
  8. Thank you for your all your help and I able to know a little bit the gonder spritual and historical facts.
    I appreciate the blessed duty which is to promote holy places of Gonder and other parts of the country.

    ReplyDelete
  9. Thank u for this historical post
    God bless you

    ReplyDelete
  10. I also like www.debelo.org it is one of the wide resource our church need to have.

    ReplyDelete
  11. This is a great starting.Let God give you his grace and keep your effort to maintain it. The sight has a good organization and brief message which is an excellent lay out. Let God help you your spirit. I am willing to help in what ever way I can.

    Samuel Negash from Chicago USA

    ReplyDelete
  12. Oh I have seen lots of blogs today and really feel happy.
    Thank u Dn. Melaku, God give u long life.Kele Hiwot yasemaln, gena sintun tasawkun yihon kemalet wuchi min elalehu.

    Tesfahun, North America

    ReplyDelete
  13. ፊልጶስ እምቤተ ኤስድሮስAugust 2, 2011 at 9:13 AM

    ዉድ ወንድሜ ዲ/ን መላኩ በየሳምንቱ የምትፅፍልን ነገር ታሪክን አንዲሁም ሃይማኖታዊ ትዉፊትን በደንብ እንድንረዳ ስላደረገን አጅጉን ላመሰግንህ አወዳለሁ። በተረፈ ደግሞ መሰረታዊ የቤተክርስቲያናቺን ትምህርቶች ለምሳሌ ስለ አአማደ ቤ/ን ብፅትፍልን የሚል አስተያየት አለኝ አግዚአብሔር ፀጋዉን አብዝቶ ረጅም እድሜን ይስጥልኝ።

    ReplyDelete
  14. thanks dn engineer Melaku keep it up by introducing the history of our mom EOTC
    GOD BLESS U

    ReplyDelete
  15. ዲያቆን መላኩ እግዚያብሄር ያበርታህ።

    ReplyDelete
  16. as time passes by those truth preached by our forefathers where on the verge of being forgotten.on our era ,the nation is consumed with western beliefs esp .the past twenty years or so this is being a chronic problem to the existence of we who believe on the truth .beyezemenu amlake hulun ehdeyechelotaw yasenesawalena antefam.EGEZIABEHARE AGELGELOTACHUN YEBAREKAN HULACHENM ENDAN !

    ReplyDelete
  17. kalhiwoten yasemalene

    ReplyDelete
  18. Best Please keep it up!!

    ReplyDelete
  19. በቅድሚያ ሰላም ለአንተ ለወንድሚ እንዲሆን እመኛለሁ። ምንም ከቆሚ የአምድህ ተከታታይ አንዱዋ ብሆንም 44ቱ ታቦት የሚለው ጽሑፍህ በጣም አስደስቶኛል ብዙ ትምህርትም አግንቸበት አለሁ። የአድባራቱ ጥንታዊ ታሪካቸው እንዳለ ተጠብቆ ቢታደሱ እና አብያተ ክርስትያናትም ውስጥ ያለው ቅርሳቅርስ መልክና ወግ በአለበት ሁኒታ ቢያዝ እንዲት መልካም ነበር :: በይበልጥ ያሳዘነኝ ግን የሥላሲ በተክርስትያን ፎቶ ሳይ ነው:: ያን የመሰለ ታሪካዊ ገዳም በኛ ዘመን እድሳት አጥቶ የዘመኑን ምእመን በትዝብት የሚያይ ሽማግሊ አባት ይመስላል:: ምን አለ በዚህ በስደት ያለነውም በአገር ቢት ያላችሁትም ተጣጥፈን አሰባሳቢ ኮሚቲ ቢቋቋም እና መላ ቢባል።
    በስራህ ሁሉ እግዝአብሒር ይከተልህ::

    ReplyDelete
  20. betame gondar tarecane ende bemadreg eg/zare wagahen ykefale betame now dase yalenemelekame ray now g/zare yaberta!!!!!!!!!!!!!!..........

    ReplyDelete
  21. ዲቆን መላኩ ቸሩ እግዚአብሔር ቃለ ህይዎት ያሰማልን ትልቅ ትምህርት ነው ያነበብኩት ::

    ReplyDelete
  22. wede wendemachen diacon melaku ejeg betame yekber mesgana akerbalewe awoo beteley begonder ye 44 tun tabotat setezekereln betame ejeg betame desta newe eytesmage gonder Lethiopia bale weleta nat be haymanotachen entena wendemachen egezeyabeher yebarkelen enamesegenale mimi.tesfaye

    ReplyDelete
  23. thank u dn. but what does the word in bracket(in the name of kings) mean???
    your site is very intersting!!! keep it up!!!

    ReplyDelete
  24. Dn.melaku yeagelgelot zemnhin yarzm fesamewn ayasamerlhi
    thank u so much
    Genet
    U.S.A

    ReplyDelete
  25. አንድ ነገር ታወሰኝ::እምነት ማለት እንዲህ ነው::በጉንደር ከተማ አካባቢ 92 የሚሆን በተክርስትያን እንዳለ በጽሑፍህ አስምረህልናል እናመሰግንህ አለን:: ስመ ጐንደሪየ ሁሉ ይህን ማሰብ ተስኖት በአሜሪካ ምደር ከአንድ በተክርስትያን ውስጥ 700 ምእመን እንዲታጓር የሜፈልገው ጥቄት እንዳይመስልህ:: የበተክርስትያን በየአቅራቢያው መኖር ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል ብየ አምናለሁ:: 1)የበተክርስትያን እርቀት ከለለ ምእመን በሃይማኖት ይጕለብታል በየግዜው የመሄድ እድል ስለሜያገኙ
    2)የአባቶችን ሥራ ያቃልላል መድከም መሰላቸት አይኖርም ለምሳሌ መስቀል 500 ሰው በአንድ ግዚ በማሳለም
    3) አባቶችና ምእመን ለይተው ለመተዋወቅ ግዚ ተገኝቶ ምክርም ተግሳጽም ከአባቶች ለማግኘት
    4) የሩጫ ዘመን በመሆኑ ግዚ ለመቆጠብም
    5) የአባቶች ደሞዝ በተለያዩ መክንያቶች በቄ ስላልሆነ አገልግሎታቸውም ተመጣጣኝ እንዲሆን
    6) ሰው በዛ ነገር በዛ ይባላል:: ምእምን በፍቅር ተዋውቀው እና ተከባብረው እንዲጸልዩ ወዘተ በመሰለ ምክንያት በውጭ አገር በተለይ የኣርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ምእመን በሜበዛበት አካባቢ ያላችሁ ምእመናንም ሆነ ያገባናል ባዩች አባቶች በጸብ ሳይሆን በስምምነት የበተክርስትያን መስፋፋት እንድታስቡበት በ44 ታቦት እማጸን አለሁ::የጉንደር ከተማ ከ44 ታቦት በላይ መኖር ለDC ቤተክርስትያን ትልቅ አርዓያ ነው ብየ አምናለሁ::
    እግዚአብሔር ስራችሁን ይባርክ

    ReplyDelete
  26. wondmachin hoyi yagelglot idmehin yarzmln, tnx for sharing.

    ReplyDelete
  27. Dn Melaku, God bless u!It is realy show how ur knowledgeble about ur faith.Good job!KEEP IT UP!

    ReplyDelete
  28. kale hieot yasemalin.yihin blog yagegnehut be daniel kibret blog amakagnet new antem yelelochin blog bitasgeba.

    ReplyDelete
  29. Egzabehier yebarikeh !!

    ReplyDelete
  30. Medhane'Alem Yabertah!!!!!!!!
    It is my pleasure to such a very significant descriptions on religious and cultural aspects of our city. I hope you will enable us to know more about the Churches and castles of Gondar and its surroundings in the future.

    ReplyDelete
  31. WE ARE HAPPY BY GONDER

    ReplyDelete
  32. God Bless You! Keep it up!

    Mebratu: From Minziro Tekle-Haymanot

    ReplyDelete
  33. የሰራዊት ሁሉጌታ እግዚአብሔር ይሰጥልን አመሰግናለሁ

    ReplyDelete