Saturday, February 27, 2016

ዐቢይ ጾም



በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት ባሕልና ትውፊት  መሠረት በዘንድሮው ዓመት  ሰኞ የካቲት  28 2008 ( ማርች 7   2016 ) የሚጀመረው የጾም ወራት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱና ዋነኛው፣ ጌታ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው፡፡ ምእመናን ጌታቸው ያደረገውን ምሳሌ ተከትለው ይጾሙታል፡፡





   ይህ ታላቅ የሆነው የጾማችን ወራት በተለያየ ስያሜ  ይጠራል፡፡
1. ዐቢይ ጾም ይባላል፡፡

ሌሎች አጽዋማት ከቅዱሳን አበው የወረስናቸው የኑሮአቸው ፍሬዎች (ዕብ.13፤7) ሲሆኑ ይኼኛው ግን በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተመሠረተ በመሆኑ ዐቢይ (ታላቅ) ይባላል፡፡ የጌታ ጾም ስለሆነ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች (አርእስተ ኃጣውእ) ድል የተነሡበት፣ ድል የሚነሡበት ጾም ስለሆነም ዐቢይ ጾም ይባላል፡፡

2. ጾመ ሁዳዴ ይባላል፡፡

ሁዳድ ማለት የመንግሥት መሬት፣ የመንግሥት ርስት ማለት ነው፡፡ የመንግሥት ሁዳድ በሚታረስበት ጊዜ፣ አዝመራው በሚሰበሰብበት ጊዜ ልጅ ዐዋቂ ሳይባል የመንግሥቱ ዜጋ ሁሉ ለሥራ ታጥቆ እንደሚነሣ ይህንንም የጌታ ጾም የጌታ ወይም የጌታ ሁዳድ የክርስቶስ ዜጎች የሆኑ ምእመናን ሁሉ ይጾሙታልና ጾመ ሁዳዴ ይባላል፡፡

3. የካሣ ጾም ይባላል፡፡

አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን ከገነት የተባረሩት ለውርደት ሞት$ ለሲዖል ባርነት የበቁት በመብል ምክንያት ነበር፡፡ በሆዳምነቱ የወደቀውን የሰው ልጅ በፈቃዱ በጾመው ጾም ካሠው$ እንዲሁም አዳም ከገነት ሲባረር ረሃበ ጸጋ (መንፈሳዊ ረሃብ) ደርሶበት ነበርና ረሃቡን በረሃብ ካሠለት፡፡ የኛን ረሃብ እርሱ ተራበ፡፡

4. የድል ጾም ይባላል፡፡

ጌታችን ተጠምቆ ዕለቱን ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ በመሔድ ከሰው ተለይቶ አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት በመጾም አዳምና ሔዋንን በመብል የረታቸውን ዲያብሎስን እርሱ ድል አደረገላቸው፡፡ ዲያብሎስን ድል ያደርግ ዘንድ ከዚህ ዓለም ርቆ ወደ ገዳም መሄዱ አዳም ከዚህ ዓለም ርቃ በምትገኘው ገነት ድል ሆኖ ነበርና እርሱም ዲያቢሎስን በገዳም$ በዚህ ዓለም ርቆ ድል አደረገልን ለእኛም ፈቃደ ሥጋችንን የምናሸንፍበተ ኃይል ሰጠን፡፡ ይህ ጾም ጠላት ዲያቢሎስ የተሸፈነበት ነው፡፡

5. የመሸጋገሪያ ጾም ይባላል፡፡

ሊቀ ነቢያት ሙሴ ሕዝቡን ከሕገ ልቡና ወደ ሕገ ኣሪት ሲያሸጋግር አርባ መዓልትና ሌሊት በደብረ ሲና እንደ ጾመው ሁሉ ጌታችንም እኛን ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል ሲያሸጋግረን አርባ መዓልትና ሌሊት ጾመ፡፡ ስለዚህም የመሸጋገሪያ ጾም እንለዋለን፡፡

6. ጾመ አስተምህሮ ይባላል፡፡

ሁሉን ነገር በቅጽበትና ያለ ድካም ማድረግ የሚችለው አምላክ እኛን ልጆቹን ያስተምረን ዘንድ ራሱን ዝቅ አደረገ፡፡ መልካም መምህር ተማሪዎቹ ይገባቸው ዘንድ ዝቅ ብሎ በነርሱ ቋንቋ እየተናገረ በሚችሉት እየመሰለ እንዲያስረዳ ጌታችንም እኛን ወደርሱ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እርሱ ወደ እኛ መጣ፡፡ ረሃባችንን ተራበ ፤ ድካማችንን ደከመ ፤ ፈተናችንን ተፈተነ ለእኛም አርአያ ሆኖ ትሕትናን ፤ ትዕግሥትንና ፈተናን በጾም ማሸነፍን አስተማረን፡፡

7. የቀድሶተ ገዳም ጾም ይባላል፡፡

እነ መጥምቁ ዮሐንስ እነ ነቢዩ ኤልያስ የኖሩትን የብሕትውና ኑሮ ጌታ ባርኮ ሰጠን፡፡ ከከተማ ወጥቶ ከሰው ርቆ በበረሃ ከአራዊት ጋር እየኖረ በዲያብሎስ ተፈትኖ ድል አደረገ፡፡ ዛሬም ልጆቹ በየገዳማቱ ድምፀ አራዊትን ግርማ ሌሊትን ተግሠው ዓለምን ንቀው ፤ ከሰው ርቀው በጾም በጸሎት ከአጋንንት ጋር ይታገላሉ$ ድልም ያደርጋሉ፡፡

8. የመዘጋጃ ጾም ይባላል፡፡

ለእሥራኤላውያን ስለ በዓለ ፋሲካ አከባበር ሲነገራቸው የፋሲካውን በግ ሥጋ ከመራራ ቅጠል ጋር እንዲበሉት ታዘው ነበር (ዘጸ.12፤18)፡፡ ይኽም መራራ ቅጠል በግብፅ ይኖሩት የነበረውን የመከራ ኑሮ የሚያሳስባችውና ደግም ወደ ግብፅ (ምድረ ፋይድ) እንዳይመለሱ ከኃጢአተ ይርቁ ዘንድ የሚያስተምራቸው ነበር፡፡ የፋሲካው በግ ደግሞ እግዚአብሔር በፍቅሩ የሰጣቸውን ነፃነት ያሳስባቸዋል፡፡

ዛሬም በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከበዓለ ትንሣኤው በፊት የጾም ወራት ያስቀደምነው ለዚህ ነው፡፡ ከመብል ስንከለከል ለአዳምና ሔዋን የተሰጠውን ሕግ እናስባለን$ ረሃብ ሲሰማን በሰው ልጅ ላይ ደርሶ የነበረው የጸጋ ረሃብ$ የመንፈስ ረሃብ ይታወሰናል$ ስንደክም ስንጐሰቁል በአዳምና ሔዋን የደረሰው የመንፈስ ጉስቁልና$ የበደልን የዕዳ ቀንበር ተሸክመው የደረሰባቸው ድካም ይታሰበናል፡፡ እኛም በነርሱ የደረሰችው ሞት በእኛ እንዳትደርስ ዳግም ወደ ኃጢአት እንዳንመለስ ይመክረናል ያሳስበናል፡፡

በጾሙም መጨረሻ የሐዲስ ኪዳንን በግ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋና ደም እንቀበላለን፡፡ ያን ጊዜም ሞትን ካሸነፈው አምላክ ጋር አንድ እንሆናለን (ዮሐ.6፤55-58)፡፡ ሞታችን በሞቱ እንዳለፈ እናስባለን (1ቆሮ.11፤26)፡፡ በመሆኑም ይህ ወቅት በዓለ ትንሣኤ- የሐዲስ ኪዳን ፋሲካን ለማክበር$ ሥጋ ወደሙን ለመቀበል ራሳችንን የምናዘጋጅበት የምንፈትንበት ነው (1ቆሮ.11፤27)፡፡

9. የሥራ መጀመሪያ ጾም ነው፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማስተማር ሥራውን ከመጀመሩ$ የመንግሥተ ሰማያትን አንቀጽ ከማስተማሩ በፊት በገዳመ ቆሮንቶስ አርባ መዓልትና ሌሊት ጾመ፡፡ ይህም ለእኛ የማንኛውም ነገር መጀመሪያው ጾም መሆኑን ሲያሰተምረን ነው፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያት ጾምን የሥራቸው መጀመሪያ ያደረጉት፡፡

እንዲሁም ይህ የጾም ወቅት፡-

የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡ ተኩላዎች እንድንጠነቀቅ ያስተምረናል፡፡ ጠላት ዳያብሎስ ጌታችንን ሲፈትን ከመጽሐፍ ቅዱሰ እየጠቀሰ ነበር (መዝ 2ዐ፤11)፡፡ የእግዚአብሔርን ስም የጠራ፣ ጥቅስ የጠቀሰ ሁሉ መንፈሳዊ ሰው ፤ እውነተኛ ክርስቲያን ሊባል አይችልም፡፡ መጥቀስማ ዲያብሎስም ይጠቅሳል ሕይወቱን አይኖረውም እንጂ፡፡

እንዲሁም በዚህ የጾም ሰሞን ጠላታችን ዲያብሎስ ያዘጋጀልንን ወጥመድ አስበን ለገድል የምንዘጋጅበትም ነው፡፡ ጌታን ወደ መቅደስ ጫፍ አውጥቶ ወደ ታች ተወርወር እንዳለው ሁሉ እኛንም በትዕቢትና በከንቱ ውዳሴ ወደ ላይ አውጥቶ በኃጢአትና በውርደት በኃፍረትና ከመንፈስ በማራቆት ሊወረውረን ይሻል፡፡

ስለዚህ ትሕትናን በምታለብስ ጾም ድል እንንሣው፡፡

እንግዲህ ዐቢይ ጾም ማለት፡-
·        ጌታ ስለኛ ባየው መከራ የምናዝንበት፣

·        በሰጠን ኃይል ከሰይጣንና ከፈቃደ ሥጋ የምንዋጋበት፣

·        በበደልነው ተገብቶ የካሠልንን እያሰብን ዳግም ወደ ኃጢአት ላንመለስ ቃል የምንገባበት ፤
·        አርአያ ሆኖ ከሠራልን ሥርዓት፣ ከኖረልን ሕይወት የምንማርበት፣

·        ራሳችንን ለፋሲካው በግ ለሥጋ ወደሙ የምናዘጋጅበት ሰሞን ነው፡፡


በመሆኑም በሰላም፣ በፍቅር፣ በትሕትና ጾመን ለበዓለ ትንሣኤው በሰላም እንድንደርስ  ጾመን ለማበርከት እንዲያበቃን እግዚአብሔር በቸርነቱ ይጠብቀን አሜን፡፡

21 comments:

  1. Kele hiwotin yasemalin! Egziabher beselam betena yitebikilin!

    ReplyDelete
  2. Kalehiwot Yasemalin

    ReplyDelete
  3. kale hiwot yasemalin........will be better if we are allowed to know the sunday holidays of ABIY TSOM ahead of time

    ReplyDelete
  4. kale hiwoten yasemalen, tsomun beselam asfetsemo lebrihane tnsaewu yadrsen amen amen amen !!!!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  5. ቃለ ሔይወት ያሰማልን :: እባክህን ትምህርቱ እንዳይቋረጥብን አደራ ::

    ReplyDelete
  6. Kalehiwot Yasemalin

    ReplyDelete
  7. egizeabher lezelealem enanten yitebikilin.

    ReplyDelete
  8. Replies
    1. ቃለ ሕይዎት ያሰማልን፣ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን።

      Delete
  9. ቃለ ህይወት ያሰማልን

    ReplyDelete
  10. ቃለ ሕይዎት ያሰማልን፣ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን።

    ReplyDelete
  11. ቃለ ሕይዎት ያሰማልን፣ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን።

    ReplyDelete
  12. ቃለ ሕይዎት ያሰማልን፣ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን።

    ReplyDelete
  13. Qale Hiwetin Yasemalign Mengiste semayatin yawarsilin Amen ... Ye Kalu Balebete Ye enatachin Yekidist Dingile Mariam Lij Medhanialem Kef Kef Yibel ....

    ReplyDelete
  14. Kale Hiywetin Yasemalin....

    ReplyDelete
  15. kale hiwet yasamalen!!

    ReplyDelete