Tuesday, January 31, 2012

ቅዱስ ቶማስ እና የሰማዩ ቤተ መንግሥት


ሐዋርያው  ቅዱስ  ቶማስ
በህንድ ሀገር ታከሻሊላ በተባለ ከተማ ጎንዶፓረስ የተባለ ንጉሥ ነበር፡፡ ይህ ንጉሥ በኢየሩሳሌም ስለ ነበረው የንጉሥ ሰሎሞን ቤተ መንግሥት ዝና እየሰማ እርሱም በሀገሩ ማሠራት ይፈልግ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ነጋዴዎች በየሀገሩ ሲጓዙ የታወቀ ግንበኛ  እንዲያመጡለት አዘዛቸው፡፡

ይህንን መልእክት ከሰሙት ነጋዴዎች መካከል አንዱ ፋርስ ወደሚባለው ሀገር ተጓዘ ከዚያም ያ ነጋዴ አንዱ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስን አገኘው፡፡ ነጋዴው ቶማስ ከኢየሩሳሌም እንደመጣ ሲሰማ የግንበኝነት ሙያ ይችል እንደሆነ ጠየቀው፤ ሐዋርያው ቶማስ ወደ ህንድ ሄዶ ማስተማር ይፈልግ ነበር፡፡ ስለዚህም ይህንን ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ለመሔድ “በኢየሩሳሌም ሳለሁ ህንፃ በመገንባት እኖር ነበር፡፡” አለው፡፡

Wednesday, January 25, 2012

አባ መቃርዮስ


በአንድ ወቅት አባ መቃርዮስ ይህንን ታሪክ ተናግሮ ነበር። ወጣት ሆኘ በአንዲት በዓት ውስጥ ስኖር መንደሩ ጸሐፊ ሊያደርጉኝ ፍለጉ። ይህንን ክብር መቀበል ስላልፈለኩ ሸሽቼወደ ሌላ መንደር ገባሁ። ሸሽቼ ስሔድም አንድ ሰው አብሮኝ ነበረ። ያም ሰው እኔ በእጄየምሰራውን እየሸጠልኝ ያገለግለኝ ነበር። በዚህ መሐል በዚያ መንደር የምትኖር አንዲትድንግል የነበረች ሴት ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ አርግዛ ተገኘች። ማርገዟም በታወቀ ጊዜከማን እንደጸነሰች ቤተሰቦቿ አጥብቀው ጠየቋት። እሷም የደፈረኝ እና የጸነስኩትም ከዛመናኝ ሰው ጋር  ብላ ነገረቻቸው። ቢዚህን ጊዜ መንደርተኞችም ሲሰሙ በፍጥነትመጥተው ያዙኝ። በጣም ጥቁር የመሰለ ማሰሮ እና ሌሎችንም የወዳደቁ ነገሮች በአንገቴዙሪያ አጠለቁብኝ ከዛም ወደ መንደሮችና አደባባዮች እያዳፉ ወሰዱኝ። በጣምምአብዝተው ይደበድቡኛል። ደግሞም « ይህ መነኩሴ ልጃችንን አበላሸ፤ ያዙት፤ በሉትእያሉ ይቀጠቅጡኛል» ብዙም ክፉ ቃላትን ይናገሩ ነበር።

Wednesday, January 18, 2012

ስለጥምቀት የሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ቃለ ምልልስ



ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ
የጎንደር መንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም ደብር አስተዳዳሪና የአራቱ ጉባኤያት /የብሉያት፣ የሐዲሳት፣ የሊቃውንትና የመጻሕፍተ መነኮሳት/ የጉባኤ መምህር ከሆኑት ከሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ጋር የጥምቀትን በዓል አስመልክቶ የዛሬ ዓመት ጥር 9 2003 ዓ.ም. አጭር ቃለ ምልልስ በስልክ ከማህበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ ጋር አድርገው ነበር ፡፡ ለሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ከፍተኛ ምስጋናችንን እያቀረብን ለአንባቢዎቻችን የታላቁን ሊቅ ቃለ ምልልስ በማቅረብ እንኳን አደረሳችሁ እንላለን፡፡ መልካም ንባብ፡፡ 
ጥያቄ ፡- ሊቀ ሊቃውንት እንኳን አደረስዎት?
ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ፡- እንኳን አብሮ አደረሰን።
ጥያቄ ፡- ጤናዎት እንዴት ነው?
ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ፡- ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ።
ጥያቄ ፡- የጥምቀትን በዓል ለምን እናከብራለን? ለክርስቲያኖች ያለው ፋይዳ ምንድን ነው?

Sunday, January 1, 2012

ነገረ ልደቱ ለክርስቶስ



እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ
በገባው አምላካዊ ቃል መሠረት አዳምን ለማዳን የዘመናት መቆየት' የወር መጉደል ማለፍ' የቀናት መዛነፍ ሳይኖርበት፤ በቃሉ መሠረት በልበ ሥላሴ ታስባ በኖረች ጥንተ አብሶ (የቀደመ በደል) ካላገኛት፣ በንጽሕናና በቅድስና በድንግልናም ተጠብቃ ትኖር ከነበረችው፣ በሕሊና ሥላሴ የማይቆጠር ዕድሜ ካላት በሥጋ ግን 15 ዓመት ብላቴና ከሆነች ከንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ያለወንድ ዘር በብሥራተ ገብርኤል ተጸነሰ፡፡እንደ ሰው ሥርዓት 9 ወር 5 ቀን በኋላ ንጉስ ነኝ ብሎ ዙፋን ሳይዘረጋ፣ ቤተ መንግስት ሳያሠራ፣ ክቡር ነኝ ብሎ ወርቅ ሳይለብስ፣ ሰው በሚኖርበት ሳይሆን ከብቶች በሚኖሩበት በበረት ውስጥ በቤተልሔም አውራጃ ተወለደ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያንም ይህንን የጌታን ልደት ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት በመመደብ በድምቀት ታከብራዋለች፡፡