Monday, June 9, 2014

ጾመ ሐዋርያት




  • ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው  ነገር ሁሉ መከልከል ማለት ነው፡፡ ወይም ለሥጋ የሚመቸውን ነገር መተው ማለት ነው፡፡ ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ጾም አለ ጾም ከሃይማኖት ጋር ዘለዓለማዊ ዝምድና አለው፡፡ በብሉይ ኪዳን ጾም ከፍተኛ ቦታ ነበረው፡፡
  • የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ጋር በሚገናኙበት ወራት እህል ውኃ ለአፋቸው አይገባም ነበር፡፡ ዘዳ 34፥28 በኃጢአታቸው ብዛት የመጣባቸው መዓት የሚመልሰው ቁጣውም የሚበረደው ሕዝቡ በጾም ሲለምኑትና ሲማልዱት ነበር፡፡ዮና 3፥5-10
  • በአዲስ ኪዳንም ጾም ሰው ሠራሽ ሕግ ሣይሆን ራሱ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው መጀመሪያ አድርጎ የሠራው ሕግ ነው፡፡ ማቴ 4፥21 ጌታችን ስስት በፍቅረ ንዋይና በትዕቢት የሚመጣበትን ጠላት ዲያቢሎስ በጾም ድል እንድምንነሣው አሳየን፡፡ ይህም ብቻ ሣይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር ጠላት ስይጣንን በጾም የሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግሯል ማቴ 17፥21
  • በጾም የተዋረደና ለጸሎት የተጋ ሰውነት ለእግዚአብሔር ለመታዘዝ የተዘጋጀ በመሆኑ እግዚአብሔር ያዘናል እኛም እንታዘዝለታለን፡፡
  • ስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናትና ቀሳውስት የሚሾሙትም በጾምና በጸሎት ነበር፡፡

Saturday, June 7, 2014

በዓለ ሃምሳ

ቤተ ክርስቲያናችን ከምታከብራቸው ዓበይት በዓላት መካከል አንዱ በዓለ ጰራቅሊጦስ ነው፡፡ ይህ በዓል ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ደቀመዛሙርቱን አንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እሰከ ትለብሱ ኃይለ እም አርያም ሉቃ 2449 ብሏቸው አርጎ ነበር፡፡ተናግሮ የማያስቀር ነውና ባረገ በ10ኛው በተነሣ በ50ኛው ቀን ጰራቅሊጦስን ሰዶላቸዋል ፡፡