Friday, October 25, 2013

ብሂለ አበዉ 1

·         ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው  ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ›› 
አባ እንጦንስ
·         ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል››     
  ቅዱስ አትናቴዎስ
·         ‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል››             
        ቅዱስ ሚናስ

Tuesday, October 15, 2013

በውኃ ላይ የታነፀው ይምርሐነ ክርስቶስ የ“ወርልድ ሞኑመንትስ ፈንድ የ2014 ተመራጭ መካነ ቅርስ” ሆነ





ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ

ከዛጒዌ ስመ ጥር ነገሥታት አንዱ በነበሩት በንጉሥ ይምርሐነ ክርስቶስ ዘመነ መንግሥት ከተሠሩት ኪነ ሕንጻዎች አንዱ የኾነው ይምርሐነ ክርስቶስ፤ የወርልድ ሞኑመንትስ ፈንድ 2014 ተተኳሪ መካነ ቅርስ (2014 World Monuments Watch) ሆኖ ተመረጠ፡፡
ፈንዱ መስከረም 28 ቀን 2006 .. ዋና /ቤቱ በሚገኝበት በኒው ዮርክ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው÷ .. 2014 ዓለም በትኩረት ሊያውቃቸው፣ ሊጠብቃቸውና ለትውልድ ሊያስተላለፍላቸው ይገባል ካላቸው 41 አገሮች ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች መካከል ልዩ የኪነ ሕንጻ ጥበብ የሚታይበት የይምርሐነ ክርስቶስ መካነ ቅርስ አንዱ ኾኖ መመረጡ ተገልጧል፡፡
ወርልድ ሞኑመንትስ ዎችበተሰኘው ፕሮግራሙ ለአደጋ የተጋለጡና ዝነኛ የቱሪስት መስሕብ የኾኑ ታሪካዊ ኪነ ሕንፃዎችንና ባህላዊ መካነ ቅርሶችን በማስተዋወቅ፣ የቴክኒክና የገንዘብ ድጋፍ በመለገሥ ዘመን ተሻጋሪ እንዲኾኑ ዓለም አቀፍ ቅስቀሳ የሚያደርገው ወርልድ ሞኑመንትስ ፈንድ፣ በዝርዝሩ ያካተታቸው የተመረጡ ቅርሶች ዓለም አቀፍ ትኩረት እንዲያገኙና በአግባቡ እንዲጠበቁ በዓለም ዙሪያ ያሉ ባለድርሻ አካላት ሁሉ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
በዩኔስኮ የተመዘገቡ በርካታ የዓለም ቅርሶች የፈንዱ ተጠቃሚ ሲኾኑ ከእኒህም መካከል ፈንዱ .. 1966 ሲቋቋም የክብካቤና ድጋፍ ሥራውን የጀመረባቸው የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ መቅደስ እንደሚገኙበት በመግለጫው ተመልክቷል።
የይምርሐነ ክርስቶስ መካነ ቅርስ በዓለም አቀፍ ፈንዱ ተመራጭ እንዲኾን በመጠቆምና ለምርጫው የሚያግዙ መረጃዎችን በማቅረብ ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ለአዲስ አድማስ የገለጸው የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ክብካቤና ልማት ማኅበር፤ መካነ ቅርሱ 2014 የወርልድ ሞኑመንትስ ፈንድ ተመራጭ መኾኑ ኪነ ሕንጻውን የበለጠ ለማስተዋወቅና ለማልማት ዕድል ይሰጣል ብሏል፡፡ ቅርሶች ዘላቂ ምጣኔ ሀብታዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ያበረክቱ ዘንድ ራእይ የሰነቀው ሀገር በቀል ማኅበሩን ጨምሮ በቅርስ ክብካቤ ዙሪያ የሚሠሩ ባለሞያዎች፣ የሥራ ሓላፊዎችና ድርጅቶች ከሚመለከታቸው የብዙኀን መገናኛና ሌሎች አካላት ጋራ በመተባበር እንንዲንቀሳቀሱም ምቹ ኹኔታ ይፈጥራል ተብሏል፡
ከዘጠኝ መቶ ዓመታት በፊት በሰሜን ወሎ ወግረ ስኂን በሚባል ቦታ ሰፊና ግርማ ሞገስ ባለው የተፈጥሮ ዋሻ ውስጥ በውኃ ላይ እንደታነፀ የሚታመነውና ልዩ የኪነ ሕንፃ ጥበብ የሚታይበት ይምርሐ ክርስቶስ÷ በአገራችን ረጅም ዕድሜ ያስቆጠረውን የቤተ መንግሥት ሕንጻ፣ በድንቅ ጥንታዊ ሥዕሎችና ንድፎች ያሸበረቀ ቤተ መቅደስ አሰናኝቶ የያዘ መካነ ቅርስ ነው፡፡ በተጨማሪም ልዩ ልዩ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች፣ ያልፈረሱና ዕድሜ ጠገብ የሰው ዐፅሞች፣ የሀገር በቀል ዕፀዋት ጥቅጥቅ ደንና ማራኪ መልክአ ምድር የሚገኙበት ነው፡
  

ይምርሃነ ክርስቶስ

ከዳንኤል ዕይታዎች የተወሰደ
 





ወደ ይምርሃነ ክርስቶስ ለመድረስ ከላሊበላ ወደ ሰቆጣ የሚወ ስደውን መንገድ ይዘን ለ30 ኪሎ ሜትር ከተጓዝን በኋላ ብል ብላ ከተባለችው ከተማ ደረስን፡፡ ከዚያም ዋናውን መንገድ ትተን ወደ ምሥራቅ ተገነጠልን፡፡ መንገዱ ወደ ይምርሃነ ክር ስቶስ ቱሪስቶችን ለማጓጓዝ እንዲረዳ በአካባቢው መስተዳድር የተጠረገ መንገድ ነው፡፡ ከብልብላ በኋላ 7 ኪሎ ሜትር እንደ ነዳን ጥንታዊውን የንጉሥ ይምርሃነ ክርስቶስ ከተማ ዛዚያን በሩቁ አየናት፡፡ አሁን ለምልክት ከሚታየው እና የኢያቄም ወሐና ማኅበር በብረት ፍርግርግ ለማስታወሻ ካሠራው አነሥተኛ ጎጆ እና በዙርያው ካለው ዐጸድ በስተቀር ሌላ ምልክት አይታይበትም፡፡ቀሪውን ስድስት ኪሎ ሜትር ስናጠናቅቅ ከፊታችን ጥቅጥቅ ያለው ደን ገጭ አለ፡፡

1526 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው እና በተራራው ላይ የተዘረጋው ጥንታዊ ደን በሀገር በቀል ጽድ እና ወይራ የተሞላ ነው፡፡መነኮሳቱ ደኑን የተከለው ንጉሥ ይምርሃነ ክርስቶስ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ከመኪና ወርደን ባሕል እና ቱሪዝም ባሠራው የእግረኞች መንገድ በኩል ተራራውን መውጣት ጀመርን፡፡ጸጥ ባለው አካባቢ የአእ ዋፍን ድምጽ ብቻ ነው የምትሰሙት፡፡1ኪሎ ሜትር ያህል እየተጠማዘዛችሁ ተራራውን ትወጣላችሁ፡፡