Friday, August 10, 2012

ፅንሰታ ለማርያም

እንኳን ለፅንሰታ ለማርያም በዓል ነሐሴ 7 በሰላም አደረሳችሁ
ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ 
አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ

ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም ፤ 
በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ
አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም
ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር: እነዚህም በእግዚአብሄር የሚያምኑ የተወደዱጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ:፡ እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሄርም በሰውም ዘንድ የተመሰከረለላቸውባለጸጎች ነበሩ::ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅአልነበራቸውምና መካን ነበሩ:

 አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለንልጅ የለን የሚወርሰን: አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት:እርሱአም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለእኔልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚህ ያለ ነገር እንኩአንስላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት እሱአም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምትላንትና ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለድሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋም ፀሃይን ስትወልድ አየሁ አለችው::
እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው:ያም ህልም ፈቺ እግዚአብሄር በምህረቱ አይቶአቹሀል በሳህሉመግቡአችሁአል 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ የፀሃይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው: እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶነገራት እርሱአም እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች:፡
ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች:ስሙአንም ሄሜን ብለው አወጡላት፤ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኑአም ዴርዲ ብለው ስም አወጡላት ፤ ዴርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና ቶና አለቻት፤ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት ሲካርምእንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት ;ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት ፤ ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህትቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደውን ሃናንወለደች:: ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢትአልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆጠረላቸውምና አልተፃፈም:ይህቺም ሃና በስርዓት በቅጣት አደገች፡፡ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠንስትደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ እያቄም ጋር አጋቡአት::
 እነዚህቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፤ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑዋሉ:፡ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ ፡-
ኢያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ:፡
ሃናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ:ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋየምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች:፡      እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላአለቀሰች:፡እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተእግዚአብሄርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ(ውሃ) ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትንአገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ:: ዘካርያስም እግዚአብሄር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላችሁ ብሎ አሳረገላቸው
 ከዚያም በሁአላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄምዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ:ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት ፤ ወፍ የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባህሪው ነው ፤ ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱ ፤ የኢያቄምን ( የሰውን) ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው እወቅ ሲል ነው ፤ 7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባህርይው:ምልአቱ:ስፍሃቱ:ርቀቱ:ልእልናው:ዕበዩ መንግስቱ ናቸው:፡
 ሃናም እኔም አየሁ አለችው:ምን አየሽ ቢላት:ነጭ ርግብ መጥታበራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ አለችው::ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት:ነጭነቱ ንጽህናዋ : ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው:ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁማለቷብስራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መጽነሷን ነው:ይህንኑም ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው::
እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየንነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፤ፈቃደ እግዚአብሄር ቢሆን ብለው አዳምንናሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡ነሃሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረችደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሎአቹሃል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሃና ነገራትበፈቃደ እግዚአብሄር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች፡:
እመቤታችን ከተፀነሰች በኋላ አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ:ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት ፤ የሃናም የአጎቷ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቿ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ቆዩአት ፤ እርሷም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበትመግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነስቶ ስብሃት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሃየ ጽድቅ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱለመንፈስቅዱስ ጽርሃ ቤቱ ተፈስሂ ደስ ይበልሽ ብሎ ሰገደላት፤አይሁድ ከዛ ነበሩና ምነው ሳሚናስ ምን አየህ? ምን ትላለህ? ቢሉት ከዚች ከሃና ማህፀን የምትወለደው ህፃን ሰማይ ምድርንእመቅ አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኑአት ሰማሁአቸው እኔንም ያነሳችኝ የፈወሰችኝ ያዳነችኝ እርሷ ናት አላቸው ፤ በል ተወው ሰማንህ ብለው ቅናት ጀመሩ::
እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች::
ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች ዕመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ ጾሙን ጾመ ሥርየት ፤ጾመ መድኃኒት ያድርግልን- አሜን ፡፡
ዋቢ
 • ቅዳሴ ማርያም ወውዳሴ ማርያም ንባቡና ትርጓሜው
 • ነገረ ማርያም
 • ተአምረ ማርያም
 • ስንክሳር27 comments:

 1. Kale Eywot yasmalin. dengel tetbekeln!!

  ReplyDelete
 2. ቃለ ህይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 3. ቃለ ህይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete
 4. ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ
  አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ

  ReplyDelete
 5. "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ
  አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ

  ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤
  በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ"

  አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም

  ዲ/ን መላኩ ቃለ ሕይወት ያሰማልን እግዚአብሔር ረዥም የመንፈሳዊ አገልግሎት እድሜን ከሙሉ ጤና ጋር ያድልህ፤ ጸጋውንም ያብዛልህ፡፡

  እንግዲህ ምን እንላለን? እጹብ እጹብ ድንቅ ድንቅ ከማለት ውጭ፡፡ ስለ እመቤታችን ለመናገር ቅዱሳን አበውም እኮ ቃላት አጥሯቸው እነ አባሕርያቆስ በአጭር ቃል «እመቤቴ ሆይ በምንና በምን እመስልሻለሁ? . . . ምሳሌ የለሽም» አይደል ያሏት፡፡


  መጣዓለም አማረ
  ኮምቦልቻ ደቡብ ወሎ

  ReplyDelete
 6. ቃለ ሕይወት ያሰማልን። ጅምሩ ግን በቂ ዝግጅትና አቅም ያለው አይመስልም፤ እናም ተገቢው የሰው፣ የመረጃና የማጣቀሻ ዝግጅት ስለመደረጉ ጥንቃቄ ብታደርጉ ጥሩ ነው። አለዚያ አያዛልቅም።

  ReplyDelete
 7. thankyou
  teshome abuhay

  ReplyDelete
 8. ዲያቆን መላኩ እግዚአብሔር ይስጥልን

  ReplyDelete
 9. እመቤታችን ፍቅሯን ጣዕሟን በልቡናችን ትሣልብን ታሳድርብን በረድኤቷና በአማላጅቷ አትለየን! አጥንትን የሚያለመልም ነፍስን የሚያረካ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን!

  ReplyDelete
 10. degu wendmachin Egziabher Elet Elet Ewqtune Yistihi

  ReplyDelete
 11. Thank U for sharing. Interesting.Yemi

  ReplyDelete
 12. "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ
  አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ
  ቃለ ሕይወትን ያሰማልን!

  ReplyDelete
 13. እመ በርሀን ሳሊተ ምሕረት አቁራሪተ መዓት ቅድሰት ንግስት ሰማያዊት እናት ድንግል ማርያም ከልጁዋ ከወዳጅዋ ቅዱስ ኤልሻዳይ ያህዌ እየሱስ ክርስቶስ ምራ ታስምረን አሜን።ቃለ ሕይወትን ያሰማልን!

  ReplyDelete
 14. ዲ/ን ቃለ ህይወት ያሰማህ። ሰባቱ የጌታ ባህሪያት ብለህ ስድስ ብቻ ነው የጻፍከው። ካልተሳሳትኩ "እዘዙ" ይጎድላል መሰለኝ (ሀሳቡን ግን ያመጣሁት በሰሞነ ህማማት ጊዜ "ለእዘዙ፥ ለመኩናኑ፥ ለስልጣኑ፥ ለዕበዩ ይደሉ የሰማው ስለመሰለኝ ነው። ከተሳሳትኩ እታረማለሁ። ይህንን ፖስት ማድረግ አይጠበቅብህም ግን የሚጨመር ካለ እንድትጨምር ነው። ባለፈውም ይእመቤታችን እድሚ 3 ወር ይጎድለዋል መሰለኝ።
  ሰላመ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን
  እግዚአብሔር ሲጻፍ ደግሞ "ሔ" ነው

  ReplyDelete
 15. ቃለ ሕይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 16. ፊልጶስ እምቤተ ኤስድሮሥAugust 17, 2011 at 9:34 AM

  ወንድም ዲ/ን መላኩ አግዚአብሔር ፀጋዉን ያብዛልህ

  ReplyDelete
 17. Ruth ke SouthDakotaAugust 18, 2011 at 12:06 PM

  kale hiywet yasemalin AMEN!

  ReplyDelete
 18. gobez! ,say more ,do more yebel beyealehu Egziabehair yebarkachu yebareken !

  ReplyDelete
 19. ቃለ ሕይወት ያሰማልን የአገልግሎት ዋጋህን አምላክ ይክፈልህ

  ReplyDelete
 20. Kalehiwot Yasemalen! Be'edme betsga yetebikilene!

  ReplyDelete
 21. Kale Hiwot Yasemalin! Egziabher yitebikilin! Kalun endemitiseten Egziabher yistih!

  ReplyDelete
 22. ዲያቆን መላኩ
  የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዕውቀቱን ያብዛልህ።
  ሥራህን ይባርክ።
  ቃለ ሕይወት ያሰማልን።

  የእናቱ የቅድስት ድንግል ማሪያም አማላጅነት አይለይህ።
  አይለየን።
  አሜን።

  ReplyDelete
 23. ዲያቆን መላኩ
  የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዕውቀቱን ያብዛልህ።
  ሥራህን ይባርክ።
  ቃለ ሕይወት ያሰማልን።

  የእናቱ የቅድስት ድንግል ማሪያም አማላጅነት አይለይህ።
  አይለየን።
  አሜን።

  ReplyDelete
 24. kale hiowt yasemalen, edme tena yestelen

  ReplyDelete
 25. ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ 1 ጥያቄ አለኝ ይህውም እመቤታችን ከዳዊት ወገን ስለመሆኗ መረጃ የለም ለሚሉ አይሁድ ከቤ/ክ አዋልድ መጽሐፍ ሌላ በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጠቀሰ ብታሳውቁኝ፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡

  ReplyDelete