Thursday, December 27, 2012

ታኅሣሥ ገብርኤል


ገብርኤል ማለትእግዚእ ወገብር” -የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው። ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው  መላእክትምመኑ ፈጠረነ፡ ማን ፈጠረንሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜየፈጠረንን አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም”  ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ ነው። በዚህም ምክንያት ጌታበእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያምእንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል። ከዚህም በኋላ ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል።ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡
በዚህም ዕለት በታህሳስ 19 እግዚአብሔር አገልጋይ የሆኑትን አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ከእቶነ እሳት አድኗቸዋል። (ትንቢተ ዳንኤል ዕራፍ 3)
ነገሩ እንደዚህ ነው -
አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ተማርከው ፋርስ ባቢሎን ሲኖሩ ንጉሡ ናቡከደነጾር ዳንኤልን አራተኛ አድርጎ ጥበበ ባቢሎን ይማሩ ብሎ ከቤተ - መንግሥት  አስቀመጣቸው። መጋቢያቸው ሜልዳር ሥጋ በገበታ ጠጅ በዋንጫ አቀረበላቸው።ይህንን አንበላም ጥቂት ጥሬ እና ጥሩ ውኃ ስጠንአሉት።ንጉሥ ከስታችሁ ቢያይ ይቆጣልአላቸው።ቀን ስጠንቢሉት 10 ቀን ሰጣቸው። ጥሬ እየቆረጠሙ ውኃ እየጠጡ ሰንብተው ጮማ ከሚበሉት ጠጅ ከሚጠጡት ይልቅ አምረው ደምቀው ተገኙ።
በዚሁ ሲማሩ ቆይተው ጌታ ጥበቡን ገልጾላቸው ጠቢባን ሲሆኑ ይልቁንም ዳንኤል ርእሱ ዘወርቅን ለንጉሱ ከተረጎመለት በኋላ በሦስት አውራጃዎች ሾማቸው። ባቢሎናውያን ቀንተው ለማጣላት ምክንያት ይሆነናል ብለውንጉሥ እንዳየኸው ምስል አድርገህ አሰርተህ አቁም ወዳጅ ጠላትህን በሱ ትለያለህአሉት። 70  ክንድ ቁመት፣ 6 ክንድ ስፋት ያለው የወርቅ ምስል አሰርቶ በአዱራን ሜዳ አቁሞያልሰገደ ይቀጣልብሎ አዋጅ ነገረ። ሁሉ ሲሰግዱ ሠለስቱ ደቂቅአንሰግድምአሉ። ሄደው ነገሩት። አስጠርቶአንሰግድም አላችሁን?” አላቸው።አዎንአሉት።መኑ ያድኅነክሙ እምእዴየ፤ ማን ያድናችኋል?” አላቸው።ሀሎነ አምላክነ ዘፈጠረ ኪያከ ወኪያነ፤ እኛንና አንተን የፈጠረ አምላካችን ያድነናልአሉት። ነበልባሉ 49 ክንድ የሆነ እሳት አስነደደ።
ከዚህ በኋላ ኃያላኑን መርጦ የኋሊት አሳስሮ ከእሳቱ አስጣላቸው። እኒያን ወላፈኑ ገድሏቸዋል። እነርሱን ግንወወረደ መልአከ እግዚአብሔር ምስለ እለ አዛርያ ውስተ እቶን ወዘበጦ ለነበልባለ እሳት ወረሰዮ ከመ ማይ ቆሪር ዘጊዜ.ጽባሕይላል ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ በዘንጉ ቢነካው ውኃ ሆኗል። ባቢሎናውያን የቀደመው  ሲጠፋ ጨማምረው አነደዱባቸው። 

እነርሱ ግን ምንም ሳይሆኑ ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ፤ ስቡህኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም። እያሉ ሲያመሰግኑ አድረዋል።
በጧት ናቡከደነጾር ከሰገነቱ ሆኖ ሲመለከት አራት ሆነው በእሳቱ ውስጥ ሲመላለሱ አይቶ ትናንት ሦስት ሰዎች አስረን ከእሳቱ እቶን ጥለን ነበር፤  ዛሬ ግን አራት ሆነው ከእሥራታቸው ተፈትተው በእሳቱ ውስጥ ሲመላለሱ አያለሁ።  እንደውም አራተኛው የእግዚአብሔር ልጅ ይመስላልአለ።ወዲያውም ከእቶኑ ሔዶአንትሙ ሲድራቅ ወሚሳቅ ወአብደናጎ አግብርተ.እግዚአብሔር ንዑ ፃዑ ዝየ፤ እናንተ ሲድራቅ ሚሳቅና አብደናጎ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ውጡ።አላቸው። ምንም ሳይሆኑ ወጥተዋል።በልብሳቸው ላይ ጥላት እንኳን አልተገኘም።
ናቡከደነጾር ይህን አይቶይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ ሲድራቅ ወሚሳቅ ወአብደናጎ ዘፈነወ መልአኮ ወአድኀነ አግብርቲሁ፤ መልአኩን ልኮ ባለሟሎቹን ያዳነ የሲድራቅ የሚሳቅ የአብደናጎ አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን።አለ።ንጉሥ እውነት መሰለህ በሥራያቸው ነውአሉት ባቢሎናውያኑ።በሥራይ ከሆነማ ከእናንተ የሚበልጥ የለም በሥራያችሁ ዳኑብሎ ከእሳቱ ጨምሯቸው ተቃጥለዋል። ንጉሡምከሲድራቅ ከሚሳቅ ከአብደናጎ አምላክ ከእግዚአብሔር በቀር ማዳን የሚቻለው የለምና እሱን አምላኩ ብሎ አዋጁን በአዋጅ መልሶታል። እነሱንም በሹመት ላይ ሹመት በክብር ላይ ክብር ጨምሮላቸዋል። (.ዳን .3)
የነደደ እሳት ውስጥ ገብቶ ከመውጣት ባልተናነሰ መከራ ውስጥ ገብተው በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ከሞተ ሥጋ ነፍስ ድነው እውነተኛ ምሥክርነታቸውን የሚሰጡ ብዙዎች ናቸው፡፡ በመልአኩ ሥም በፈለቀው ጠበል ተጠምቀው ደዌ የራቀላቸው እጅግ በርካታ ናቸው፡፡ በየዓመቱ በቁልቢና በሌሎች በቅዱስ ገብርኤል ስም በታነጹ አብያተ ክርስቲያናት የሚሰበሰበው ምዕመናን ሥዕለቱ የሰመረለት ልመናው የተሰማለት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ገብርኤል የተሰጠውን ጸጋ ተረድተን የመልአኩን አማላጅነት በመጠቀም ልናከብረው  ይገባል፡፡


የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ጠባቂነቱ፣
 በሁላችን ላይ ለዘለዓለም ይኑር።
 አሜን።
8 comments:

 1. Kale Hiwot Yasemalin

  ReplyDelete
 2. Amen! Ye hiwot qal yasemalin! Ke'melaku kidus Gabriel bereket yasatifilin!

  ReplyDelete
 3. Amen!!! Kale hiwot yasemalin. Betena behiwot yitebikilin.

  ReplyDelete
 4. Amen kale hiwot yasemaln

  ReplyDelete
 5. Ykdusan amlke agelgeloton ybark. Kalhiwet yasmaln

  ReplyDelete