- ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገር ሁሉ መከልከል ማለት ነው፡፡ ወይም ለሥጋ የሚመቸውን ነገር መተው ማለት ነው፡፡ ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ጾም አለ ጾም ከሃይማኖት ጋር ዘለዓለማዊ ዝምድና አለው፡፡ በብሉይ ኪዳን ጾም ከፍተኛ ቦታ ነበረው፡፡
- የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ጋር በሚገናኙበት ወራት እህል ውኃ ለአፋቸው አይገባም ነበር፡፡ ዘዳ 34፥28 በኃጢአታቸው ብዛት የመጣባቸው መዓት የሚመልሰው ቁጣውም የሚበረደው ሕዝቡ በጾም ሲለምኑትና ሲማልዱት ነበር፡፡ዮና 3፥5-10
- በአዲስ ኪዳንም ጾም ሰው ሠራሽ ሕግ ሣይሆን ራሱ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው መጀመሪያ አድርጎ የሠራው ሕግ ነው፡፡ ማቴ 4፥21 ጌታችን በስስት በፍቅረ ንዋይና በትዕቢት የሚመጣበትን ጠላት ዲያቢሎስ በጾም ድል እንድምንነሣው አሳየን፡፡ ይህም ብቻ ሣይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር ጠላት ስይጣንን በጾም የሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግሯል ማቴ 17፥21
- በጾም የተዋረደና ለጸሎት የተጋ ሰውነት ለእግዚአብሔር ለመታዘዝ የተዘጋጀ በመሆኑ እግዚአብሔር ያዘናል እኛም እንታዘዝለታለን፡፡
- ስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናትና ቀሳውስት የሚሾሙትም በጾምና በጸሎት ነበር፡፡
Monday, June 9, 2014
ጾመ ሐዋርያት
Saturday, June 7, 2014
Tuesday, April 22, 2014
ዘመነ ትንሳኤ ( የትንሳኤ ሳምንት)
- «ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡
- መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለው ግሥ ይሆናል፡፡
- «ትንሣኤ» ማለት ታዲያ = መነሣት፣ አነሣሥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡
- «ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም ዐምስት ክፍል አለው፡፡
1) አንደኛው «ትንሣኤ» ኅሊና ነው፡፡ ይህም ማለት ተዘክሮተ እግዚአብሔር ነው፡፡
2) ሁለተኛውም «ትንሣኤ» ልቡና ነው፡፡ የዚህም ምስጢሩ ቃለ እግዘብሔርን መስማትና በንስሐ እየታደሱ በሕይወት መኖር ነው፡፡
3) ሦስተኛው «ትንሣኤ» ለጊዜው የሙታን በሥጋ መነሣት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ድጋሚ ሞት ይከተለዋል፡፡
4) አራተኛው «ትንሣኤ» የክርስቶስ በገዛ የባሕርይ ሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣት ነው፡፡
5) ዐምስተኛውና የመጨረሻው «የትንሣኤ» ደረጃም የባሕርይ አምላክ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን «ትንሣኤ» መሠረት ያደረገ «ትንሣኤ ዘጉባኤ» ነው፡፡ ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላ ሰው ሁሉ እንደየሥራው ለክብርና ለውርደት፣ ለጽድቅና ለኩነኔ በአንድነት የሚነሣው የዘለዓለም ትንሣኤ ይሆናል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)


