በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
በእግዚአብሔር አጋዥነት ጦማር ( ጽሕፈት ) እንጀምራለን
ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ ካላደረጉ
ልማር ላስተምር ፤ አነብ እተረጉም ፤ እጽፍ እደጉስ ቢሉ አይቻልምና
ልማር ላስተምር ፤ አነብ እተረጉም ፤ እጽፍ እደጉስ ቢሉ አይቻልምና
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማደግ በሰዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚከናወኑ ድርጊቶችን በመረጃ መረብ (Internet) አማካይነት ከአንዱ ክፍለ ዓለም ወደ ሌላው ክፍለ ዓለም ሀሳቦች ፣ አመለካከቶች እና አስተሳሰቦች ይንሸራሸራሉ፡፡
በሀገራችን በኢትዮጵያ ይህ ቴክኖሎጂ ከሌሎች ሀገሮች ጋር ሲነፃፀር በእጅጉ ያደገ ባይሆንም ቁጥሩ አነስተኛ የማይባል ተጠቃሚ በሀገር ውስጥ ይገኛል፡፡ በውጭው ዓለም ደግሞ በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች መኖራቸው የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡
በዚህ ዘመን የበርካታ ሰዎች ዓይኖች ከኮምፒውተር መስኮት (Monitor) ፊት ለፊት ተደቅነው፣ በወገባቸው ደግሞ ተንቀሳቃሽ ስልክ (Cell Phone) ታጥቀው እንደመኖራቸው እነኚህ የቴክኖሎጂ ግኝቶችን ለመንፈሳዊ ሕይወት ጥንካሬ በመጠቀም ዘመኑን የመዋጀት ሥራ መሥራት ግድ ይለናል፡፡
በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች የጡመራ መድረኮች (Blogging Sites) ቢኖሩም ከ50 ሚሊዮን በላይ ለሚደርሰው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመን ግን ከ5 ወይም ከ6 በጣት የሚቆጠሩ የጡመራ መድረኮች ይገኛሉ፡፡ እነዚህም በማኅበራዊ ሕይወት፣ በግዕዝ ቋንቋ፣ በትምህርተ ሃይማኖት፣ ዜና ያተኮሩ የቤተክርስቲያኒቱ ፍሬዎች በሆኑ ልጆች የሚዘጋጁ ናቸው፡፡
በሀገራችን ኢትዮጵያ ከ36,000 በላይ ገዳማትና አድባራት፣ እንዲሁም በርካታ ታሪካዊ ቦታዎች ከመኖራቸው በተጨማሪ አኩሪ ሥራ ሠርተው ያለፉ ስማቸው በወርቅ ቀለም የተፃፈ ፤ ከመቃብር በላይ የገዘፈ የታሪክና የእውነት ባለቤት አባቶች እና እናቶች ነበሩን፣ አሉን ወደፊትም ይኖራሉ፡፡ የእነኚህን ቅዱሳን መካናት እና ቅዱሳን ሰዎች ሕይወት በመዘከር ትውልዱ ከእኔ ምን ይጠበቃል? ብሎ እንዲጠይቅና ታሪካዊ ኃላፊነቱን በመረዳት ይህም ትውልድ በተራው ታሪክ ሠሪ ትውልድ እንዲሆን የቀደሙ አባቶችን ሥራ እና ሕይወት መካፈል እንችል ዘንድ ይህ ስንክሳር የተባለው የጡመራ መድረክ (Blogging Site) ተከፈተ፡፡
በዚህ የጡመራ መድረክ ገዳማት፣ አድባራት፣ አብያተ ክርስቲያናት፣ የአብነት ት/ቤቶች፣ የፀበል ቦታዎች፣ ታሪካዊ ቦታዎች ፤ ቤተ መዘክሮች፣ አብያተ መፃሕፍት፣ ሰንበት ት/ቤቶች እና ሌሎችም መካነ ታሪኮች እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን መዓዛ የሆኑ የቅዱሳን፣ ፃድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግል፣ መነኮሳት፣ ነቢያት ሐዋርያት፣ አበው ወእማት፣ መምህራን፣ ሊቃውንት፣ ጳጳሳት፣ ወንድሞችና እህቶች አርአያነት ያላቸው ሰዎች ዜና መዋዕል፣ ገድል፣ ትሩፋት፣ ብሒል የሚዘከርበት የሀገራችን የሚንቀሳቀሱ እና የማይንቀሳቀሱ ቅርሶች ፤ በዓላት፤ ዕሴቶች እና ሌሎችም የሚዳሰሱበት ይሆናል፡፡
በዚህ የጡመራ መድረክ (Blogging site) የሚወጡትን የተለያዩ ጽሁፎችን፣ ሥዕሎችን፣ ቪዲዮዎችና የተለያዩ መረጃዎች የጡመራ መድረኩ ባለቤት በተለያየ ጊዜ ታትመው የወጡ መጻሕፍት፣ መጽሔት፣ ጋዜጣ፣ ዜና መዋዕሎች፣ በራሪ ወረቀቶች እና ድረ ገጾች (websites) በዋቢነት ከመጠቀሙም ባሻገር የተለያዩ ቦታዎችን በአካል በመሔድ የሚያደርጋቸው ቅኝቶች ግብዓቶች ናቸው፡፡
የጡመራ መድረኩ ተሳታፊዎች ወደፊት በሚሰጡት፣ የነቃ፣ የጎላ፣ እና የሰላ ምክር እና አስተያየት ለሁላችንም መልካም የትምህርት መድረክ እንደሚሆን ተስፋዬ ነው፡፡ የጅማሬም የፍፃሜም ባለቤት እግዚአብሔር ሁላችንም ያጽናን፡፡
የአባቶቻችን ዕምነታቸው ፀጋ በረከት ረድኤታቸው
ጥርጥር የሌለባት ንጽሕት ተዋሕዶ ዕምነታቸው በእኛ ዘንድ ፀንታ ትኑር
ዲያቆን መልአኩ እዘዘው የኔነህ
Cell Phone +251-918-774646
ጎንደር መንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን
በእውነቱ ከሆነ የዘመኑን ቴክኖሎጂ መሰረት በማድረግ የቀደሙት አባቶቻችንን የቅድስና ስራቸው፣ገድላቸው፣ ታሪካቸውን………..ልታሳውቀን በመነሳትህ በጣም የሚያስደስት ነውና አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን.እኛም ለመኮምኮም ተዘጋጅተናል፡፡
ReplyDeleteYou are blessed, I am inspired and appreciated this God gifted beautiful mind.
ReplyDelete+++
ReplyDeleteለመጀመር እንደተነቃቃህ በርታ ብለህ በተለይ ዓይን ስንክሳሩን እንደምታስኮሞኩመን ተስፋ አደርጋለሁ።
መክ.
እግዚአብሄር ያበርታህ የኔ ወንድም!
ReplyDeleteሕሩይ
Good beginning, God be with you !!!!
ReplyDeleteየጅማሬም የፍፃሜም አምላካችን እግዚአብሄር እርሱ ይርዳህ!
ReplyDeleteሼቦ ንሁላጥ
ReplyDeleteየአዳም እና የሔዋን ዘር በሙሉ ለነፍስ ለስጋው የሚሆን መልካም ነገር ተምሮ እራሱን እና ወገኑን ከጥፋት መንገድ መልሶ እግዚአብሄርን የሚያስደስትበት መግባር እንዲኖረው የሚያደርግ የጡመራ ገፅ ይሆንልን ዘንድ አምላከ ቅዱሳን ይርዳን:: አንተን ለመጀመር ያነሳሳህ አምላክ ይህን የጡመራ ገፅ ለታስበለት ዓላማ መዳረሻ ያበቃልን ::
ከቤልቪዩ ዋሽንግተን ሰሜን አሜሪካ
ይህንን ቴክኖሎጂ ውጤት ለመንፈሳዊ አገልግሎት እንድንጠቀም ያደረገን አምላከ-ቅዱሳን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን። ዘመን የማይሽረውን የሕይወት ቃል (ቃለ እግዚአብሔርን)ለባለዘመኑ ትውልድ በዘመኑ የቴክኖሎጂ ውጤት ለማቅረብ በመነሳትህ ይበል የሚያሰኝ ነውና መድኃኔዓለም ከአንተ ጋር ይሁን። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ። በርታ።
ReplyDeleteዲ/ን አብርሃም ጤናው.... ከጎንደር
Egziabher yabertah. Ye Qidusan amlak ayleyih.
ReplyDeleteKe Germany
Egziabher fitsamhen yasamirew ena berta wendimachin.
ReplyDeleteSenkesaru Lay Berta Wendemachen Dengle Tasebehe.
ReplyDeleteThanks Dn Melaku for teaching and sharing us this teaching of our church.It's time to use this medium as an instructional tool for about church teachings...so God Bless You my brother.
ReplyDeleteIt is nice start for our church !
ReplyDeleteFrom Italy
Great job! dear brother, keep it up! stay blessed.
ReplyDeleteZelalem Berihun
WHEREFORE seeing we also are compassed about with so great a cloud witnesses, let us lay aside every weight and the sin which doth so easily beset us and let us run with patience the race that is set before us.
ReplyDeleteLooking unto jesus the author abnd finisher of our faith;who for the joy that was set before him endured the cross.despising the shame,and is set down at the right hand of the throne of God. HEBREWS 12;1-2
IT is agood job diacon melaku keep it up thanks to God .
God bless ur serve
selam.A
FROM NORTH AMERICA
Greetings in the name of the Loving Mother of God !
ReplyDeleteKeep the good job up Diaqon Mel'aku.
wow diaqon melaku its nice start for us .
ReplyDelete10q selamye for sharing this blog .
bruk las vegas
Bizu tebazu temariwochachin egnam selasa:silsa:meto fire yeminaferabet nibab yihunilin AMEN!!!
ReplyDeleteIt is a Great job.This is one of the best way to introduce our country culture and religion to the world and lesson for other ETHIOPIANS.may god bless you!!
ReplyDeletekumssa CHERENET
It is an honer to be your brother,& what a great job you are doing for the Ethiopian Orthodox followers, and the church itself, to keep up with the latest technology, may god be with you for the rest of your journey, to fulfill what you have started.
ReplyDeleteMay god bless you Brother
Ambachew
I always proud on your work and strategic thinking i also pray to make your dream true
ReplyDeleteKEEP IT UP
Dawit Gondar
Dear Dik. Melaku
ReplyDeleteThank you for sending me this great news. God bless you and be with you in all your en-devours.I am at your disposal to support this great work with my very little knowledge of our wonderious heritages.
God bless Ethiopia.
Dear Dn Melaku,
ReplyDeleteIt`s a good start and all Ethiopians (0rthodox Tewhdo) will support you and stand with you in praying to the Almighty God to give you strength and guidance.
God bless you.
በል እግዚአብሔር ያበርታህ!!!
ReplyDeleteYekidusan Amlak Egziabeher yabertah !!
ReplyDeleteOh I am very happy I want to say THANK YOU please give a time to this it was my dream
ReplyDeleteYekidusan Amlak Yabertah
yekidusan amlak birtatun yistih.
ReplyDelete'የጅማሬም የፍፃሜም ባለቤትአምላካችን እግዚአብሄር እርሱ ይርዳህ:: Good job bro!
ReplyDeleteHG, Addis Ababa
good start!!!!!!!!!!
ReplyDeleteበርታ!
ReplyDeleteበል እግዚአብሔር ያበርታህ!!!
ReplyDeleteየሚያስተምሩ ወንድሞችን ቁጥር የጨመረ፣ የማስተማሪያውን ዘዴ የፈጠረ እኛም እንድንማር እድሉን የሰጠን የቅዱሳን አምላክ የተመሰገነ ይሁን፡፡ እግዚአብሔር መልካም ነገርን ሁሉ ይፈቅዳልና አንተ በርታ፡፡ ቃለ ህይወት ያሰማለን መንግስተ ሰማያትን ያዋርስልን
ReplyDeleteI found it interesting and encouraging to know more about our historical back and to induce our individualistic religious knowledge etc. Though I may be late in browsing this blog, thanks to God, I could reach almost all of the literature which are blessing and blessing!
ReplyDeleteDn. melaku, let God put his blessing on your fingers who provides the spiritual dying table ( menfesawi maed) for those who are hungry of it that I am amongst of them.
Hoping, in the coming, you will also deliver for us the live preaching of our church professors( liqauwnt)besides you there.
Stay blessed!
Amlak bebereketu Ayileyh!!
Edmena Tena setito legnam menfesawiwene ewket endiniyiz lantem birtatun endisetih Yeleoul Egziabher cherinetu Yemebetachin amalajinet yeqedusan redietna bereket ayileyen.
ReplyDeleteterfo kemiker edme ayinfegen
Amlake yetabekeh
ReplyDeleteamen Egziabher yatsnah!
ReplyDeleteI appreciate your commitment to help us by providing a very crucial things. And I specially very interested and pleased to read saints history. I see some of the highlights and I will read all And it gave me strength please keep on adding saints history And it is interesting to know their holy works and life!!!
ReplyDeleteThank you!!!
from Finland
ወንድሜ ሆይ ፤ ይሕን ቅዱስ ሐሳብ እንድታስብ እና እንድትጀምር ያሳሰበሕ አምላክ እንደወላጅ አባትሕ እስከመጨረሻው ዘሌቄታውን እንዲሰጠጥሕ ምኞቴ ነው። በርታ ጅምርሕ ወርቅ ነው። የድንግል ልጅ አይለይሕ።
ReplyDelete