Friday, August 22, 2014

ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር

እንኳን  አደረሳችሁ



ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ መካነ ፍሥሐ ምጡቀ ፤ በአእባነ ባህርይ ዘተነድቀ ፤ ማርያም ደብተራ እንተ ኢትትከደኒ ሠቀ

እመቤቴ ማርያም ሆይ ምጡቅና ሩቅ ወደሚሆን የደስታ ቦታ ላረገ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል ፡፡ ይኸውም ኅብሩ ሊመረምሩት በማይቻል ዕንቊ የታነፀ ሕንፃ ይገኝበታል፡፡
               መልክአ ማርያም


ፍልሰታ ማለት ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ማዛወር የነበሩበትን ሀገር ለቆ ወደ ሌላ ሀገር መሰደድ መፍለስ ማለት ነው፡፡ ጾመ ፍልሰታ ሲባልም የእመቤታችን ሥጋ ከጌቴሰማኒ ወደ ገነት መፍለስን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱን ለማመልከት የሚነገር ነው፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 64 ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ በሞት ከተለየች በኋላ እንደ አንድ ልጅዋ ሞታ መነሣቷንና ዕርገቷን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት ከነሐሴ 1 እስከ 16 የጾሙት ጾም ነው፡፡ ጾመ ፍልሰታ ከሰባቱ ዐበይት አጽዋማት አንዱ ሆኖ በቀኖና እንዲጾም ከተወሰነበት ጊዜ ጀምሮ ምእመናን ይጾሙታል፡፡ 
እመቤታችን 5485 . ከአባቷ ከኢያቄም ከእናቷ ከሐናእም ሊባኖስ ትወጽዕ መርዓት፡፡ ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለችተብሎ በተነገረው መሠረት ነሐሴ 7 ቀን ተጸነሰች፡፡ ግንቦት አንድ ቀን ሊባኖስ በምትባል ወረዳ በብጽአት እንደተወለደች የቤተክርስቲያን ታሪክ በሰፊው ያስረዳል፡፡ በጾም በጸሎት በአስተብቁዖት የተገኘች ናት፡፡ ንጽሕት በመሆኗም ማኅደረ እግዚአብሔር ሆናለች፡፡
እመቤታችን ከእናትና ከአባቷ ዘንድ ሦስት ዓመት፣ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፣ መድኃኔዓለምን በማህጸንዋ ጸንሳ ዘተኝ ወር ፤ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ 33 ዓመት ከሦስት ወር፣ ከዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ዘንድ 14 ዓመት ከዘጠኝ ወር ጠቅላላ ድምር 64 ዓመት ሲሆናት ጥር 21 ቀን 49 ዓመተ ምሕረት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡
ነቢያት አስቀድመው ስለ እመቤታችን እረፍትና ትንሳኤ በምሥጢር ተናግረዋል፡፡ ነቢዩ ዳዊት በመዝሙር /መዝ 136¸8/ “አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦትብሎአል፡፡ ፈጣሪዬ ሆይ ምእመናንን ወደምታሳርፍበት ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህን ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ ሲል ነው፡፡ ይህም እመቤታችን እንደ ልጅዋ ትንሣኤ መነሣቷን የሚያመለክት ነው፡፡ ታቦት ያላትም ማደሪያው ስለሆነች ነው፡፡
ጠቢቡ ሰሎሞንወዳጄ ሆይ ተነሺ ውበቴ ሆይ ነይ እነሆ ክረምት አለፈ ዝናቡም አልፎ ሄደ አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፡፡ የዜማም ጊዜ ደረሰ የቀረቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጐመራ ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውንም ሰጡ፡፡ ወዳጄ ሆይ ተነሺ ውበቴ ሆይ ነይሲል ስለ እመቤታችን በምሳሌ ተናግሮአል፡፡ /መኃ 2¸1-13/
ወዳጁን ውበቱን ተነሺ ነይ እያለ የተጣራው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ተጠሪዋም እመቤታችን ናት፡፡ እነሆ ክረምት አለፈ ማለት በስደት በአይሁድ የዘወትር ጠላትነት በልጅዋ መከራና ስቅላት ስምዖን በቤተ መቅደስ እንደተናገረ ልቧ በሀዘን ሠይፍ የተከፈለበት በሀዘን ፍላጻ የተወጋበት የመከራ ክረምት /ወቅት/ አልፎ የክርስቶስ ሕማሙ ሞቱ፣ ቤዛነቱ ተፈጽሟል፡፡ ትንሣኤው በምድር ላይ ተገልጧል፣ ተሰብኳል ማለት ነው፡፡ በምድራችን አበባ ታይቷል ማለት የሐዋርያት ድምፅ በምድር ሁሉ ደርሷል ማለት ነው፡፡ ነቢዩ ዳዊት ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ ብሎ ስለ ሐዋርያት የተናገረው በዓለም ያለውን መከራ ስድት ሲገልጽ ነው፡፡ /መዝ 18¸4/
የዜማም ጊዜ ደረሰ ያለው የመከራን ጊዜ ነው፡፡ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ በደስታ ይጮሃሉ፣ ይዘምራሉም ተብሏል፡፡ /መዝ 14¸13/ የመከር ጊዜ ደረሰ የተባለው መከር የፍሬ ጊዜ በመሆኑ ክርስትና አፍርቷል ማለት ነው፡፡ በለሱ ጐመራ ማለት ደግሞ በጐ ምግባረ ፍሬ ሳያፈሩ የነበሩ ሰዎች በጐ ምግባር መሥራት መጀመራቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ በመጨረሻም ወይኖች አብበዋል፣ መዓዛቸውንም ሰጥተዋል እንደተባለ በመላው ዓለም አብያተ ክርስቲያናት በሃይማኖት ማበብ መዓዛ ምግባራቸውን ማቅረብ ከጀመሩ በኋላ እመቤታችን ዐረፈች፡፡
እመቤታችን ጥር 21 ቀን ዕረፍት በሆነበት ዕለት ሐዋርያት የእመቤታችንን ሥጋ ለማሳረፍ ወደ ጌቴሰማኒ መካነ ዕረፍት /የመቃብር ቦታ/ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ በቅንዓት መንፈስ ተነሣሥተውቀድሞ ልጅዋን በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሳ፡፡ በአርባኛው ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ እንደገናም ተመልሶ ይህን ዓለም ለማሳለፍ ይመጣል፡፡ እያሉ በማስተማር ሕዝቡን ፈጽመው ወስደውታል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷንም እንደ ልጅዋ ተነሣች ዐረገች እያሉ በማስተማር ሲያውኩን ሊኖሩ አይደለምን; ተሰብሰቡና በእሳት እናቃጥላት ብለው ተማክረው መጥተው ከመካከላቸው ታውፋኒያ የተባለው ጐበዝ አይሁዳዊ ተመርጦ ሄዶ የእመቤታችንን ሥጋ የተሸከሙትን አልጋ ሽንኮር ያዘ፡፡ የአልጋውን ሽንኮር በያዘ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሠይፍ ሁለት እጁን ስለ ቆረጣቸው ከአልጋው ሽንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ ታውፋንያ በፈጸመው ድርጊት ተጸጽቶ ወደ እመቤታችን ስለተማጸነ በኅቡዕ ተአምር የተቆረጡ እጆቹን እንደ ቀድሞ አድርጋ ፈውሳዋለች ፡፡
የእግዚአብሔር መልአክ የእመቤታችን ሥጋ ከሐዋርያው ዮሐንስ ጋር ተድላ ደስታ ወደ አለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቁ፡፡ ጌታም የእመቤታችንን ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው፡፡ እነርሱም ትወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት፡፡ ያን ጊዜም ከዕፅ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን የማርያም ሥጋዋ ወጣ፡፡ ጌታችንም ዘላለማዊ ወደሆነ መንግሥተ ሰማያት መላእክት እና ሰማዕታት እየሰገዱላት አሳረጓት፡፡ ንጉሥ ዳዊትበወርቅ ልብስ ተጐናጽፋ ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለችእንዳለ፡፡ /መዝ 44¸9/
ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ተመልሶ ከሰማይ ወረደ፡፡ ሐዋርያት ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው፡፡ እርሱም እንዳየ እንደሰማ ሥጋዋም በታላቅ ክብር ማረጉን ነገራቸው፡፡ ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ፡፡ የነሐሴም ወር በባተ /በገባ/ ቀን ዮሐንስ እንዲህ አላቸው፡፡ የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት ኑ፤ ሁለት ሱባኤ በመጾም እንለምን አለ፡፡ በጾም በጸሎት ሱባኤ ያዙ፤ ጌታም የእመቤታችንን ሥጋ አምጥቶ ስለሰጣቸው በታላቅ ዝማሬ፣ በውዳሴና በጽኑ ምሕላ ወስደው ቀድሞ በተዘጋጀው መካነ እረፍት በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡
የእመቤታችን የቀብር ሥነ ሥርዓት በተፈጸመ ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ቶማስ አልነበረምና ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ እመቤታችን በተቀበረች በሦስተኛው ቀን እንደ ልጅዋ ትንሣኤ ተነሥታ ስታርግ ያገኛታል፡፡ ትንሣኤዋን ሌሎቹ ሐዋርያት አይተው ለእርሱ የቀረበት መስሎት ተበሳጭቶበመጀመሪያ የልጅሽን ትንሣኤ አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁብሎ ከማዘኑ የተነሣ ከደመናው ተወርውሮ ሊወድቅ ቃጣው፡፡ እመቤታችንም ከእርሱ በቀር ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሳኤዋን እንዳላዩ ነግራው አጽናንታው ሄዶም ለሐዋርያት የሆነውን ሁሉ እንዲነግራቸው አዝዛው ምልክት ይሆነው ዘንድ ሰበኗን /መግነዟን/ ሰጥታው ዐረገች፡፡
                                      እመቤታችን ለቶማስ ሰበን /መግነዟንሰጥታው ዐረገች
ሐዋርያው ቶማስም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን እኮ ቀበርናት ብለው ነገሩት እርሱምሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንዴት ይሆናል?” አላቸው፡፡አንተ እንጂ የጌታን ትንሣኤ ተጠራጠርክ አሁንም አታምንምን;” ብለው በቅዱስ ጴጥሮስ መሪነት ወደ እመቤታችን መካነ መቃብር ይዘውት ሄደው መቃብሩን ቢከፍቱ ሥጋዋን አጡት፡፡ ደነገጡም፡፡ ቶማስምአታምኑኝም ብዬ እንጂ እመቤታችን ተነሥታ ዐርጋለችብሎ የሆነውን ሁሉ ነገራቸው፡፡ ለማረጋገጫ ምልክት እንዲሆን የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው፡፡ ሰበኗን /መግነዟን/ ለበረከት ቆራርጠው ከተከፋፈሉ በኋላ ወደየአህጉረ ስብከታቸው ሄደዋል፡፡
ሐዋርያትም ትንሣኤሽን ቶማስ አይቶ እኛ እንዴት ይቀርብናል ብለው ከነሐሴ አንድ ቀን ጀምረው ሱባኤ ገቡ፡፡ በሱባኤው መጨረሻ በነሐሴ አሥራ ስድስት ቀን ጌታችን ጸሎታቸውን ተቀብሎ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቅ /ረዳት/ ቄስ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ /ዋና/ ዲያቆን አድርጐ ቀድሶ ሁሉንም ከአቆረባቸው በኋላ የእመቤታችንን ዕርገቷን ለማየት አብቅቷቸዋል፡፡
ቤተክርስቲያናችንም ሥርዓት ሠርታ ከሰባቱ ዓበይት አጽዋማት ተርታ አስገብታ ይህን ታላቅ የበረከትና የምሥጢር መግለጫ ጾም እንድንጾም አድርጋናለች፡፡ ሐዋርያት ያዩትን ድንቅ ምሥጢር የእመቤታችንን ትንሳኤና ዕርገት ለማየትና ከሐዋርያት አበው በረከት ለመሳተፍ ጌታችንልጆቼይላቸው ለነበሩ ሐዋርያት አምሳል ሕፃናትና ወጣቶች፣ ሴቶችና ወንዶች፣ አረጋውያንም የጻመ ፍልሰታን መድረስ በናፍቆት እየጠበቁ በየዓመቱ በጾም በጸሎት ያሳልፉታል፡፡
የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት መታሰቢያ /በጾመ ፍልሰታ/ ወቅት ብዙዎች ከቤታቸው ተለይተው በመቃብር ቤት ዘግተው፣ አልጋና ምንጣፍ ትተው፣ በመሬት ላይ ተኝተው ዝግን ጥሬ እፍኝ ውኃ እየቀመሱ በጾምና በጸሎት በመትጋት በታላቅ ተጋድሎ ይሰነብታሉ፡፡ በሰሙነ ፍልሰታ ምእመናን ለእመቤታችን ያላቸውን ጽኑና ጥልቅ ፍቅር የሚያሳዩበት ነው፡፡
ጌታችን ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሰ መቃብር ቆይቶ ሙስና መቃብር ሳያገኘው፣ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በሥልጣኑ እሑድ በመንፈቀ ሌሊት እንደተነሣ ሁሉ እርሷም በተቀበረች በሦስተኛው ቀን ማኅደረ መለኮት ናትና ሙስና መቃብር ሳያገኛት መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳትል የልጅዋ ሥልጣን ኃይል ሆኗት መነሣቷን ትንሣኤዋከመ ትንሣኤ ወልዳ፤ እንደ ልጅዋ ትንሣኤነው ተብሎ ሲከበርላት ይኖራል፡፡

ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች ዕመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ ጾሙን ጾመ ሥርየት ፤ጾመ መድኃኒት ያድርግልን- አሜን ፡፡

ዋቢ
  • ንክሳር
  • ወላዲተ አምላክ በመጽሀፍ ቅዱስ
  • ሐመር መጽሔት


57 comments:

  1. ርብቃ ከጀርመንAugust 7, 2011 at 12:41 PM

    ቃለሂወት የሰማልን ወንድማችን ዲያቆን መልአኩ እዘዘው ወቅታዊና ጣፈጭ የመቤታችንን ታሪክነው ያስነበብከን እኛንም በማንበባችን አንተንም አዘጋጅተህ በማቅረብህ እመቤታችን በበረከቱዋ ታስበን ላንተም ብርታቱንና ጥበቡን ትስጥልን አሜን

    ReplyDelete
  2. ቃለ-ሕይወት ያሰማልኝ!! ዲ/ን መልአኩ፤ ወቅታዊ እና ጣፋጭ የሆነ የነፍስ ምግብን መገብከን!!! ከማር ከስኳር የሚጣፍጠውን የእመቤታችንን የፍልሰቷን ታሪክ ስላስተማርከን እመቤታችን ፍቅሯን የበለጠ ታሳድርብህ!!! አሜን!!
    አሥራት
    ከሀላባ ቁሊቶ

    ReplyDelete
  3. Kale Hiwot yasemalen Deacon!!!!

    ReplyDelete
  4. May Lord give you strength and persistence for your spirituality.
    Welete kidan, Gondar

    ReplyDelete
  5. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲ፧ን

    ReplyDelete
  6. ቃለ-ሕይወት ያሰማልኝ!!የእመቤቴ ምልጃና ጥበቃ አይለይህ፡፡

    ReplyDelete
  7. ረዝም ዕድሜ ይስጥልን

    ReplyDelete
  8. ቃለ ህይወት ያሰማልን

    ReplyDelete
  9. Kalehiwot Yasemalen.

    ReplyDelete
  10. kale hiwot yasemalin DN.keep it up as DN daniel kibret i think he is model for most.

    ReplyDelete
  11. yigermal mechem ayin ayaneb yele. Deke estifanos siletebalut kidusan esti terik. silenesu ewnetun tenager. lisemah feligeyalehu

    ReplyDelete
  12. dinq new bewunet qale hiwot yasemalin!

    ReplyDelete
  13. Kale Hiwot Yasemalin D/n Melaku. Egziabiher Tsegawun yabzalih. Leqedemit Abew Mistirun yegeletselachew Amlake Kidusan Abizto Mistirun Yigletsilih. Woqtawina Ejig betam yemimesit Timhirt new. Berta.

    Metalem A. Kombolcha Wollo.

    ReplyDelete
  14. ፊልጶስ እምቤተ ኤስድሮሥAugust 10, 2011 at 3:28 PM

    ንኢ ሐቤየ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትባርኪ ላእሌነ
    አመቤታቺን ፍቅሯን በልባቺን ጣእሟን ባንደበታቺን ታሳድርብኝ ቃለ ሕይዎትን ያሰማልን

    ReplyDelete
  15. kale hiwat yasemalene!!! rajeme edmane yestelen!!!

    ReplyDelete
  16. Kale hiwot Yasemalen f.

    ReplyDelete
  17. ቃለ ህይወት ያሰማልን::
    በእድሜ በጸጋ ያሰንብትልን::
    የድንግል በረከት አይለየን::

    መ/ር ያለሜ

    ReplyDelete
  18. Kal Yeuhat Yasmale Yentecn Yedngl Maryam Berket Bulcen Lay yederben ...Yeselam yebrket yadent yefker Sume Yunela Amen

    ReplyDelete
  19. Kal Yeuhat Yasmale Yentecn Yedngl Maryam Berket Bulcen Lay yederben ...Yeselam yebrket yadent yefker Sume Yunela Amen

    ReplyDelete
  20. Kal Yeuhat Yasmale Yentecn Yedngl Maryam Berket Bulcen Lay yederben ...Yeselam yebrket yadent yefker Sume Yunela Amen

    ReplyDelete
  21. ye emebetachin bereket ena rediet behulachinim lay yideribin AMEN! wendimachinin betsega yitebikilin

    ReplyDelete
  22. እግዚአብሔር በአገልግሎትህ ያፅናህ

    ReplyDelete
  23. ሰይፈሚካኤል አማረSeptember 15, 2011 at 5:16 PM

    እግዚአብሔር አገልግሎትህን ይባረክ፡፡

    ReplyDelete
  24. kale hiwot yasemalin!!!

    ReplyDelete
  25. ቃለሂወት የሰማልን ወንድማችን ዲያቆን መልአኩ እዘዘው ወቅታዊና ጣፈጭ የመቤታችንን ታሪክነው ያስነበብከን እኛንም በማንበባችን አንተንም አዘጋጅተህ በማቅረብህ እመቤታችን በበረከቱዋ ታስበን ላንተም ብርታቱንና ጥበቡን ትስጥልን አሜን:በተጨማሪም ለምእመን ሰለ አገራችንና ስለሕዝባችን እንድንጸልይ በዚህ አጋጣሜ በድንግል ማርያም ስም እጠይቃለሁ::

    ReplyDelete
  26. Ye Egziabherin kal leswe joro ayinina lib yemiadersu sewoch minigna amlak yiwedachew. GOD bless you Mele! Kale hiwot yasemalin! Kebereketua tadilen!

    ReplyDelete
  27. Amen. GOD Bless You and May Holy Virgin Marry with you ...our beloved brother.

    ReplyDelete
  28. kale hiwote yasemalen Emebetachen yagelglote zemenhen tebarkleh

    ReplyDelete
  29. Let the blessings of Saint Virgin Mary Our Mother be with you always
    Thanks Dn Melaku
    Belaineh, your old Brother

    ReplyDelete
  30. Dn Melaku may God Bless You and may Our mother with you. now I have got clear information about tsome- feleseta. Thank you brother

    ReplyDelete
  31. በመጀመርያ ለሰጠኸን ትምህርት እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ፡፡



    እኔ አንድ ጥያቄ አለኝ ይኸውም ወንጌላዊው ዮሀንስ ከሰማይ ከወረደ በኋላ ነሀሴ በገባ ቀን/ማለትም ነሀሴ 1 / ሱባዔ እንያዝ ስጋዋን ለማየት አላቸውና ከሁለት ሱባዔ በኋላ ጌታችን የእመቤታችንን ስጋ አምጥቶ ሰጣቸው እነሱም በጌቴ ሰማኔ ቀበሯት እመቤታችንም በሶስተኛው ቀን እርሷም እንደ ልጇ ስታርግ ቶማስ አገኛትና ለሀዋርያት ነገራቸው ፡፡ አሁን የኔ ጥያቄ ሀዋርያት እርገቷን ለማየት ነሀሴ 1 ቀን በዓመቱ ነው በድጋሚ ሱባዔ የያዙት ወይስ መቼ ነው ?

    ሱባኤ የያዙት ሁለት ጊዜ ነው ማለት ነው?

    ጌታችን በመጀመርያው ሱባዔ የእመቤታችንን ስጋ ለሀዋርያት የሰጣቸውስ ነሀሴ 16 ነው?

    ReplyDelete
    Replies
    1. Yes ሱባኤ የያዙት ሁለት ጊዜ ነው !

      Delete
    2. ሱባኤ የያዙን አንዴ ብቻ ነው ከዛም ክርስቶስ ሰጋዋን አቅርቦ አቆረባቸው እንጂ ነሐሴ ላይም ደግሞ አልቀበሯትም
      የኔ ምንጭ ስንክሳር እና ተአምረ ማርያም ናቸው የላይኛው ታሪክ ግን ምንጩ አይታወቅም

      Delete
    3. yeman siga new yakorebachew? ye emebetachin new? meg yaqerebut hasab gilts yadrgulign

      Delete
  32. እባክህ ተጨማሪ አዎልድ መጸሀፍ ምንጭ ጥቀስልን ከስንክሰሳር ጋር ታሪኩ ስለሚምታታ

    እግዘዚአብሐሔር ይስጥልን

    ReplyDelete
  33. አሜን በረከቱዋ ይደርብን!!!

    ReplyDelete
  34. ቃለ ህይወት ያሰማልን እግዚያብሔር አብዝቶ ይባርክህ

    ReplyDelete
  35. ''በ49 ዓመተ ምሕረት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች''arfalech bibal yishalal. yetsadqan mot ireftachew
    ''እመቤታችን በ5485 ዓ.ዓ ከአባቷ ከኢያቄም ከእናቷ ከሐና'' be 15 ዓ.ዓ new.

    ReplyDelete
  36. ቃለ ህይወት ያሰማልን

    ReplyDelete
  37. መጀመሪያ ቃለ ህይወት ያሰማልን

    ግን እባክህ ተጨማሪ አዎልድ መጸሀፍ ምንጭ ጥቀስልን ከስንክሰሳር እና ከተአምረ ማርያም ጋር ታሪኩ ስለሚምታታ

    ያንተን ምንጭ ጥቀስልን

    እግዘዚአብሐሔር ይስጥልን

    ReplyDelete
  38. kale hiwot yasemalegn

    ReplyDelete
  39. እግዚአብሔር ይባርክህ!!!

    ReplyDelete
  40. Amen! Amen! Amen!
    Kale hiwot yasemalin.

    ReplyDelete
  41. ቃለ-ሕይወት ያሰማልኝ ! ዲ/ን መልአኩ

    ReplyDelete