- ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገር ሁሉ መከልከል ማለት ነው፡፡ ወይም ለሥጋ የሚመቸውን ነገር መተው ማለት ነው፡፡ ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ጾም አለ ጾም ከሃይማኖት ጋር ዘለዓለማዊ ዝምድና አለው፡፡ በብሉይ ኪዳን ጾም ከፍተኛ ቦታ ነበረው፡፡
- የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ጋር በሚገናኙበት ወራት እህል ውኃ ለአፋቸው አይገባም ነበር፡፡ ዘዳ 34፥28 በኃጢአታቸው ብዛት የመጣባቸው መዓት የሚመልሰው ቁጣውም የሚበረደው ሕዝቡ በጾም ሲለምኑትና ሲማልዱት ነበር፡፡ዮና 3፥5-10
- በአዲስ ኪዳንም ጾም ሰው ሠራሽ ሕግ ሣይሆን ራሱ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው መጀመሪያ አድርጎ የሠራው ሕግ ነው፡፡ ማቴ 4፥21 ጌታችን በስስት በፍቅረ ንዋይና በትዕቢት የሚመጣበትን ጠላት ዲያቢሎስ በጾም ድል እንድምንነሣው አሳየን፡፡ ይህም ብቻ ሣይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር ጠላት ስይጣንን በጾም የሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግሯል ማቴ 17፥21
- በጾም የተዋረደና ለጸሎት የተጋ ሰውነት ለእግዚአብሔር ለመታዘዝ የተዘጋጀ በመሆኑ እግዚአብሔር ያዘናል እኛም እንታዘዝለታለን፡፡
- ስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናትና ቀሳውስት የሚሾሙትም በጾምና በጸሎት ነበር፡፡
የሐዋ13፥3፤4፥25 እነ ቅዱስ ቆርኔሌዎስ ያላሰቡትን ክብር
ያገኙት በጾማና በጸሎት ፈጣሪያቸው ማልደው ነው የሐዋ 10፥20
ጾም እንኳን የጠበቅነውንና ያሰብነውን ቀርቶ ያላሰብነውንና
ያልጠበቅነውን ፈጽሞም የማይገባንን ጸጋና ክብር የሚየሰጥ ነው፡፡ ከሐዋርያት ቤተክርስቲያን በዓልና ትውፊት መሠረት የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከመጀመሪያዎቹ አብያተ ክርስቲያናት አንዷ ስለሆነች የጾም ሕግና
ሥርዓት አላት እነዚህም የፈቃድና የአዋጅ አጽዋማት ይባላሉ፡፡ ከሰባቱ
የአዋጅ አጽዋማት አንዱ የሐዋርያት (የሰኔ) ፆም ነው፡፡
ይህም ጾም በሕዝብ ዘንድ የወታደር ጾም ይባላል፡፡ ለስብከተ
ወንጌል ዘመቻ የተዘጋጀ በጾሙት ተምሣሌት በድሮ ዘመን ወታደሮች ለዘመቻ ሲነሱ ወይም ከዘመቻ ሲመለሱ በተሳተ በተገጸፈ ይቅር
በለን በማለት ይጾሙት ነበር፡፡ ይህም ጾም የሚፈሰክበትከሐምሌ 5 የማይለቅ ቢሆንም የሚጀመርበት ግን የተወሰነ ቀን
የለውም በዚህም ምክንያት የጾሙ ዕለት ቁጥር ከፍና ዝቅ ይላል አንዳንድ ጊዜ ከአርባ ይበልጣል አንዳንድ ጊዜ ከ30 ያንሣል
ያሁኑም ጾም ሰኔ 2 ገብቶ ለ 1 ወር ከ 3 ቀናት ይጾማል፡፡
ሐዋርያት መቼ
ጾሙ
ቅዱሳን ሐዋርያት የአምላካቸውን የመምህራቸውን አርአያ ተከትለው
እርሱ ወደ ማዳን ሥራው ማለትም ህሙማነ ሥጋን በተዓምራት ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት ከማዳን አስቀድሞ የስራውን መጀመሪያ
በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ 40 ቀን 40 ሌሊት እንደ ጾመና እንደጸለየ ሁሉ ቅዱሳን ሐዋርያትም አብነቱን ተከትለው ጾመዋል፡፡ ጸጋ
መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ዓለምን ዕጣ ተጣጥለው (ተከፈፍለው) ዞረው ከማስተማራቸው አስቀድመው የሥራቸው መጀመሪያን ጾምን
አድርገዋል፡፡
ሐዋርያትም ይህንን ጾም እንደሚጾሙ ጌታችን አስቀድሞ የዮሐንስ
ደቀመዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው በጠየቁት ጊዜ ተናግሮ ነበር፡፡ ‹‹ እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀመዛሙርትህ ግን
የማይጦሙት ስለምንድን ነው? አሉት ኢየሱስም እንዲህ አላቸው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉ? ነገር ግን
ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል በዚያን ጊዜም ይጦማሉ›› ማቴ 9፥15-16
የሰኔ ጾም የቄስ
ብቻ ነውን?
- ይህ ጥያቄ ከብዙ ሰዎች ዘንድ የሚነሣ ጥያቄ ነው ብዙ
ምፀመናን የሰኔን ጾም አዶደሙም ለመጾም የሚፈልጉትንም ሰዎች የቄስ ነው እያሉ ሲኒቅፉ ይታያሉ ነገር ግን ይህ ጾም ከሰባቱ
የአዋጅ ጾም አንዱ ነው ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታቸንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት እኛም እነርሱን አርአያ አድርገነው
ልንጾመው የሚገባ የበረከት ጾም ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ ግን ብዙ ሰዎች ትተውት ይወጣ ወደ (ቀሳውስት) ብቻ የሚጾሙት ነው
ይላሉ ለራስ የከበደን ነገር በሌላው ላይ መጫን ተገቢ አይደለም ካላወቁ ለማወቅ መማር ዐውቆ ከማጥፍት መቆጠብ ተገቢ መሆኑን
መዘንጋት አይገባም
-እኛ ይህን ጾም የምንጾመው የሐዋርያትን በረከት
ለመላበስ፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን በመሆኑ ይህንን ‹‹መሣሪያ›› አንጣለው
ጾሙም ለመላው ክርስቲያን የተሰጠ እንጂ የቀሳውስት ብቻ አይደለም ለቄስና ለምዕመናን ተብሎ በክህነት ደረጃ የተለየ ጾምም
የለም፡፡
እንዴትና ከምን
እንጹም?
- የጾም ሃይማኖታዊ ትርጉም ፈጣሪን መለመኛ ከኃጢአት ቁራኛ መላቀቂያ መሣሪያ ስለሆነ በጾም ወራት ለአምሮት ለቅንጦት የሚበሉ ወይም ለመንፈሳዊ ኋይል ተቃራኒ የሆኑ የአልኮል መጠጦች ሥጋና ቅቤ ወተትና እንቁላል ማራቅታዟል
- ባልና ሚስትም ከአንድ ላይ አይተኙም 1ኛ ቆሮ 6፥5
- ሥጋዊ ጉልበትን በጾም የማድከም ቅብአት ካላቸው ምግቦች መከልከልም መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ማስረጃ አለው ለምሳሌ ዳዊት በመዝሙር 108፥24
ጉልበቶቼ በጾም ደከሙ ሥጋዮም ቅቤ በማጣት ከሳ ብሏላ ፣ ሠለስቱ ደቂቅና ነቢዩ ዳንኤልም የቤተ መንግሥቱን ሥጋና የጸሎት ምግብ
ትተው በጥሬና በውኃ መቆየታቸው ተፅፎአል ት.ዳን 1፥8-21፣ት.ዳን10፥2 ዋናው ነገር ጾም እንጂ መብል ወደ እግዚአብሔር
አያቀረበንም ብንበላም የምናተርፈው ባንበላም የሚጎዳን ነገር የለም 1ኛ ቆሮ8 ፥8 ከአዳም ጀምሮ መብል ሲጥል እንጂ ሲያነሣ
አላየንምና ጾሙን ከኃጢአት በመራቅ ለራስ ያስብነውን ለነዳያን በመስጠት፣ ጾም ከፀሎት ጋር ሲሆን ጸጋን እንደ
ሐዋርያቱ ያሠጣልና በጸሎት በመትጋት በስግድት ወደ እግዚአብሔር በፍፁም ልብ በመመለስ ልንጾመው ይገባል፡፡
የጾም ጥቅም
ቅዱስ ኤፍሬም ‹‹ጾም የነፍስ ድግስ ፣ክብረ በዓልነው›› ብሎ ተናግሯል
ጾም ነፍስን ሐብታም ያደርጋታል፡፡ አዕምሮውን ንፁህ ከማድረጉም ባሻገር በጠላት ላይ መንፈሰ ጠንካራ ያደርጋል
ጾም ጥሩ ሥነ-ምግባራትን የሚያዳብር መንፈሳዊ ሕይወት ነው፡፡ይኸውም ንጽህናን፣ ትዕግስትን ድንግልናን፣ ደስታን ……ወዘተ
በተጨማሪም የታላቁ ንጉሥ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተመቅደስ የሆነውን አካላትንን ለንጽህና ለእርሱ እንድናስገዛ ያደርገናል፡፡
ጾም ወደ እግዚአብሔር እንድንመለስ ያደርገናል፡፡ት.ኢዩ 2፥12
አሁንስ ይላል እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁ በጾምም በለቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ ወደ እግዚአብሔር የምንመለስበትን የልብ
መነሳሳት እውነት ያደርግናል በጾማችን እግዚአብሔርን የምናደበት የቅድስና ሕይወት እንፈጥራለን ታላቁ ነቢዩ ኢሳይያስ በኃጢአቱ
ተፀፅቶ የጾመው ጾም ለኃጢአቱ ሥርየት ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርንም ክብር ለማየት አብቅቶታል ት.ኢሳ6፥1
በአጠቃላይ ጾም የመንፈሳዊ ሕይወታችን መሠረት ነው
የአገልግሎትና የቅድስናችንም መጀመሪያ ሊሆን ይገባል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ይህን ጾም ባርኮልን የቅድስና ሥራን
የምናበዛበት ያድርግልን አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፡- ሐመር መጽሔት
kalehiwet yasemalen tsegawen yabzaleh, mokshe
ReplyDeleteየበረከት ጾም ለኛም ላንተም የርግልን።በርታ!
ReplyDeleteWenedemachem Dn. Melaku KaleHiwot Yasemaleh,Amen
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡
ReplyDeleteQale hiywet yasemaln yebereket tsom yargln!!
ReplyDeleteqalehywet yasemalin!
ReplyDeletekalehiwot yasemalin
ReplyDelete