Thursday, July 5, 2012

ቤተክርስቲያን እንዴት ተመሠረተች ? ክፍል 1


ስለ ክርስትና ሃይማኖት ስለ ቤተክርስቲያን በምንናገርበት ጊዜ ሁሉ ትዝ የሚለንና የምናስተውለው የመጀመሪያው ሰው የአዳም ሁኔታ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እግዚአብሔር የሁላችንን አባት አዳምን በአርአያውና በመልኩ ከፈጠረው በኋላ ባረከው፡፡
ኹሉንም እንዲገዛ ሥልጣን ሰጠው፡፡ በረከቱን ሥልጣኑንና ሲሳዩን ከሰጠው በኋላ ፈጣሪውን የሚያስታውስበት ትእዛዝ አዘዘው፡፡ እሱ ግን በተሳሳተ ምክር ተመርቶ ከፈጣሪው ትእዛዝ ወጣ፡፡ በዚህ ጊዜ የሞት ፍርድ ተፈረደበት፡፡ ይህም የሞት ቅጣት ለርሱ ዐቅም ቀላል አልነበረም፡፡ በሱም ብቻ አልቀረም የልጅ ልጆቹ ይህን የሞት ቅጣት በውርስ ተካፈሉት፡፡ የዚህ የሞት ጽዋ ተካፋዮች ሆኑ፡፡ የአዳም ሕግን መተላለፍ የልጆቹም ተባባሪነት በእግዚአብሔርና በነሱ መካከል ያለውን ልዩነት እያሰፋው ሔደ፡፡ የፈጠራቸው እግዚአብሔርን ዘንግተው የሰማይና የምድርን ሠራዊት ማምለክ ጀመሩ፡፡ በጨረቃ፣ በፀሐይና በከዋክብት፣ በእሳት፣ በውኃ፣ በእንስሳትና በአራዊት፣ በዛፍና በተራራ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የሰውን ዘር ጨርሶ ለመደምሰስ ስላልፈለገ ይህን የሰው ልጅ መራራና አሰቃቂ ታሪክ ከመጀመሪያው ጀምረው ሲከታተሉ የነበሩ በአንድ አምላክ በማመን የታወቁ ጥቂት ሰዎችን አተረፈ፡፡ እነሱም ከአበው ሄኖክን፣ ኖህን፣ አብርሃምንና ሎጥን ሌሎችንም የመሳሰሉትን ነው፡፡ ከአብርሃም ይስሐቅ፣ ከይስሐቅ ያዕቆብ ተወለደ፡፡ ከያዕቆብም አሥራ ሁለት ልጆች ተወለዱ፡፡ አሥራ ኹለቱን የእሥራኤል ነገድ መሠረቱ፡፡

ለነሱም አንዳንድ ጊዜ ራሱ እግዚአብሔር እየተገለጠ አንዳንድ ጊዜም በነቢያትና በካህናት አማካይነት ሕጉንና ትእዛዙን ይሰጣቸው ነበር፡፡ መላልሶ ተአምራት ያደርግላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን በአካባቢያቸው በነበረው የአረማውያን ተጽዕኖ ምክንያት እነዚህ ሰዎች አልፎ አልፎ በየጊዜው ወደ አምልኮ ባዕድ ይወድቁ ነበር፡፡ በአንድ ወገን ይህ ሲሆን በሌላው ወገን ሲታይ ደግሞ ከእውነተኛው የአንድ አምላክ እምነት ያላፈነገጡ፤ በአምልኮ ባዕድ ያልተለወጡ ብዙ እሥራኤላውያን ነበሩ፡፡ እነዚህ አምልኮታቸው የጸና ነበር የሚባሉት እሥራኤላውያን ከኃጢአት ለመንጻትና የእግዚአብሔርን ምሕረትና ይቅርታ ለመጠየቅ ብዙ ወይፈኖችንና ጊደሮችን ይሠዉ ነበር፡፡ እግዚብሔርን ደስ ቢለው በማለት በወርቅ የተለበጠ በሐር የተጨመጨመ ቤተ መቅደስ በሰሎሞን ተሠርቶ ነበር፡፡
እግዚአብሔር በነቢያት እያደረ የሚመልሰው መልስ ይህን ሁሉ ደስ ብሎት የተቀበለው አለመሆኑን የሚገልጽ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ የሰው ልጅ የታሪክ ጉዞ በኋላ እግዚአብሔር በራሱ ፈቃድ የሰውን ልጅ ለማዳን የቀጠረው ቀን ሲደርስ ልጁን ሰው ይሆን ዘንድ ላከው፡፡ በልጁ በክርስቶስ ሞት ቤተክርስቲያን ተመሠረተች፡፡
ቤተክርስቲያን የተወለደችው ወይም የተመሠረተችው በፍልስጥዔም ምድር ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ከላይ እንደተገለጠው የሰውን ልጅ ትክክለኛ ታሪክና ሃይማኖት የያዙ የእግዚአብሔርንም የምሕረት ቀን በተስፋ ሲጠባበቁ የነበሩ በትዕግሥታቸው የተመሰገኑ ብዙ ደጋግና ቅዱሳን ሰዎች ስለነበሩባት ነው፡፡ የእግዚአብሔርንም የማዳን ሥራው ድንገተኛ ሳይሆን ለብዙ ዘመናት በተስፋ ሲጠበቅ የቆየ መሆኑን ለመግለጥ ነው፡፡ የክርስትና ሃይማኖት የታሪክ ሃይማኖት ነው መባሉም በዚህ ነው፡፡
 ክርስትና በተወለደበት ጊዜ የነበረውን የፍልስጥኤም ሁኔታ ለማጤን የሚቻለው ቀደም ካለው ሁኔታ የጀመርን እንደሆነ ነው፡፡ ፍልስጥዔም የአብርሃም የቃልኪዳን አገር ከነዐን ናት፡፡ በሌላም አነጋገር ምድረ ርስት ትባላለች፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን የያዕቆብ ልጆች በሙሉ ከዚች አገር ተሰደው በግብጽ በባርነት ይኖሩ ነበር፡፡ ዘመኑም 17ዐዐ-13ዐዐ ከጌታ ልደት በፊት መሆኑ ነው፡፡ ከጌታ ልደት በፊት 13ዐዐ ዓመት ገደማ በሙሴ መሪነት ወደዚች አገር ተመልሰዋል፡፡ በ1922 ዓመት ከጌታ ልደት በፊት አሥራ ኹለቱ ነገድ ባገዛዝ ተጣልተው ለሁለት ተከፈሉ፡፡ አሥሩ ነገድ በሰሜን ፍልስጥኤም በሰማርያ ተቀመጡ፡፡ ከተማቸው ሴኬም ነበረች፡፡ ኹለቱ ነገድ ደግሞ በደቡብ ፍልስጥኤም ሰፈሩ፡፡ ከተማቸውም ኢየሩሳሌም ነበረች፡፡
በ792 ዓመት ከጌታ ልደት በፊት ሰሜኑን ክፍል እስራኤላውያን በስልምናሶር መሪነት መጥተው አጠፏት፡፡ ሕዝቡም ተማረኩ፡፡ ይህ ሲሆን በደቡብ ክፍል የነበሩት የተማረኩትን አሥሩን ነገድ እንደ ጠላት ይቆጥሯቸው ስለነበር ሳይደሰቱ አልቀሩም፡፡ ነገር ግን በ586 ከጌታ ልደት በፊት የሴኬም ፅዋ በኢየሩሳሌምም ደረሰ፡፡ በናቡከደነፆር መሪነት ባቢሎናውያን መጥተው ኢየሩሳሌምን አጠፉ ሕዝቡንም ማርከው ወሰዱ፡፡ ሰባ ዓመት በምርኮ ቆይተው ከተመለሱ በኋላ ጥቂት እንደቆዩ በፋርስ ተወረሩ፡፡ አሁንም እንደገና በ33ዐ ከጌታ ልደት በፊት ግሪኮች በዚች ምድር ላይ ቅኝ ገዢዎች ሆኑ፡፡ በመጨረሻም 63 ዓመት ከጌታ ልደት በፊት ሮማውያን ተረከቧት፡፡ እንግዲህ በዚህ ረጅም የተፋልሶ ጊዜ ሕዝቡ ብዙ የባህልና የሃይማኖት ቀውስ ደርሶበታል፤ እስራኤላዊ ያልሆኑ ጠባዮችንም ሳያውቀው ሸምቷል፡፡ ክርስትና በፍልስጥኤም ሲመሠረት የነበረውን ሁኔታ ለማወቅ የሚቻለው ይህ ሲታይ ነው፡፡
ክርስትና ሲወለድ ምድረ ፍልስጥኤም እንደ ሌሎቹ የመካከለኛው ምሥራቅ የሰሜን አፍሪካና የታናሽ እሲያ አገሮች በሮም ቅኝ ግዛት ሥር ነበረች፡፡ በውስጥም የነበሩ ሕዝቦችም የተከፋፈለ የሃይማኖትና የፖለቲካ ቡድን ነበራቸው፡፡ ከነዚህም ዋናዎቹ የፈሪሳውያንና የሰዱቃውያን ቡድኑች ነበሩ፡፡
የሰዱቃውያን ቡድን የሀብታሞችና የካህናት ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን ለባሕል፣ ለሥነ ሥርዓትና ለሃይማኖት ግድ የሌለው ከቅኝ ገዢዎች ጋር ተስማምቶ በነሱ ሥልጣኔ መጠቀምን ብቻ እንጂ የነቢያትን ትንቢትና ሌሎችንም የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አይቀበሉም ነበር፡፡ የሙታንን ትንሣኤና የመሲሕንም መምጣት አያምኑም ነበር፡፡
 ሌላው ቡድን የፈሪሳውያን ቡድን ነው፡፡ ፈሪሳዊ “ፖርሽ” ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል የወጣ ነው፤ ትርጉሙም “የተለየ” ማለት ነው፡፡ እነዚህ ፈሪሳውያን ምንም የቅኝ አገዛዝ ቀንበር መላልሶ ቢያደቃቸውም ባህልና ልምዳችን አይነካ በሃይማኖትም የሙሴን ሕግና የነቢያትን መጻሕፍት የምንጠብቅ እኛ ብቻ ነን ባዮች ነበሩ፡፡ ስለዚህ ከአይሁድ ዘር ውጭ ከሆነ ከማንኛውም ጎሳና ዘር ጋር በባህልና በሥልጣኔ መቀራረቡን እንደ መርከስና ሕግን እንደመተላለፍ ይቆጥሩ ነበር፡፡ የመሲሕንም መምጣት ነቅተውና ተግተው ይጠባበቁ ነበር፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያታቸው ሀገራቸው ፍልስጥኤምን ከሮም ግዛት ነጻ ለማውጣት የቆየ ጉጉት ስላላቸው ነው፡፡ እንደነሱ አስተሳሰብ መሲሕ ሲመጣ የጦር ኃይል አቋቁሞ ራሱ የጦር መሪ በመሆን የሮማን የቅኝ ግዛት ቀንበር አውልቆ ጥሎ የዳዊትን ቤተ መንግሥት የሚያድስ መሲሕ ይጠባበቁ ነበር ማለት ነው፡፡ ምንም እንኳ ከትንሣኤ በኋላ ሥጋዊ ኑሮ አለ ብለው ቢያምኑም ትንሣኤ ሙታን መኖሩን ያውቁ ነበር፡፡
ፈሪሳውያን በዕለታዊ ኑሮአቸው ብዙ ሀብት ፍልስጥኤምን ነጻ ያወጣል የሚለውን የፈሪሳውያን እምነትና ተስፋ በመቃወም ሌላ ንኡስ ቡድን ከፈሪሳውያን ተከፍለው በሙት ባሕር አካባቢ ገዳም መሥርተው ይኖሩ ነበር፡፡ የእነሱም ዓላማቸው እንደ ፈሪሳውያን መሲሕን መጠባበቅ ነው፡፡ ኤሤይ በመባል የታወቁት እነዚሁ ክፍሎች ከፈሪሳውያን የሚለዩት ፈሪሳውያን በጦር ኃይል ነጻ እንወጣለን ሲሉ ኤሤይ የሚባሉት ደግሞ በተአምራት በእግዚአብሔር ኃይል ፍልስጥዔም ነፃ ትወጣለች ብለው ያምኑ ነበር፡፡ በቤተልሔም በስተደቡብ ልዩ ስሙ ኩምራን በሚባል ቦታ የሚኖሩ እነዚህ ሰዎች መጻሕፍትን በመጻፍ ጸሎትን በማድረስ ብዙ ጊዜ ቆይተዋል፡፡ ኤሤዎችና ፈሪሳውያን ባንድ አንድ አስተሳሰብ ቢለያዩም መሲሕ መምጣቱንና የተወሰኑ ምርጥ ጎሳዎችን ነጻ እንደሚያወጣ ዓለም አቀፋዊ መሲሐዊ መንግሥት እንደሚያቋቁምና እነሱም የመንግሥት ባለሟሎች እንደሚሆኑ ሁለቱም ቡድኖች ያምኑ ነበር፡፡ በእስራኤል የሃይማኖትና የነገድ ቤተሰብ ውስጥ ይህ ልዩነት ተፈጥሮ መከራቸውን ሲያዩ በፍልስጥኤምና ከፍልስጥኤም ውጭ የነበረው የሮማ መንግሥት ፖለቲካ ደግሞ ከቅኝ ግዛቱ የተነሣ ያነገንግ ነበር፤ የነጻ አውጭ ግንባሮች በየጊዜው የሕዝብ ቆጠራ እንዲደረግ ታዞ ነበር፡፡

11 comments:

  1. I am waiting for the next part eagerly. GOD bless you Mele!

    ReplyDelete
  2. Dear brother, you are doing a great job. Keep up teaching our christian history from the beginning up to the present to the new generation. This new generation has many challenges to know about his true identity. At this present time, foreign as well as their mercenary domestic elements are confusing this new generation about his true Ethiopian identity.
    So you are doing your a great job !

    ReplyDelete
  3. እግዚአብሔር አገልግሎትህን ይባርክልህ

    ReplyDelete
  4. Dear brother, you are doing a great job. Keep up teaching our christian history from the beginning up to the present to the new generation. This new generation has many challenges to know about his true identity. At this present time, foreign as well as their mercenary domestic elements are confusing this new generation about his true Ethiopian identity.
    So you are doing your a great job !

    ReplyDelete
  5. የብሎግህ ተጠቃሚ በመሆኔ በዚህኛው ጽሁፍ ለመሳተፍ የማስተካከያ ሃሳብ ልሰጥ ወሰንሁ ፡፡
    - “በ792 ዓመት ከጌታ ልደት በፊት ሰሜኑን ክፍል እስራኤላውያን በስልምናሶር መሪነት መጥተው አጠፏት፡፡” የሚለው በአሶራውያን ቢተካ

    በተረፈ ስለ ሰዱቃውያንና ፈሪሳውያን ካነበብኩት ላካፍል ፡-
    - ሰዱቃውያን ከሙሴ አምስቱ መጽሐፍ ውጭ ትንቢትንና ትውፊትን አይቀበሉም ፡፡ ለሰዎች ነጻ ፈቃድ ቅድሚያ በመስጠት እግዚአብሔርን በኑሮአቸው የዕለት ተዕለት መሪአቸው አድርገው አይቀበሉትም ፡፡ እንደተባለው ሃብታሞችና ለፖለቲካ ያደሉ ስለሆኑ በዘመናቸው የባላባት ያህል የገዥ መደብ አጋር ነበሩ ፡፡ ስለዚህም ምክንያት የቤተ መቅደስ ኃላፊዎች እነርሱ ነበሩ ፡፡ የሙሴን መጽሐፍ ጠብቀው ለትውልድ ያተረፉ እነሱ ናቸው ፡፡ የመላዕክትንና የደያብሎስን መኖርንና ትንሣዔ ሙታንን አያምኑም /ማቴ 22፡23 ፤ ማር 12፡18-27፤ ሥራ 23፡8/ ፡፡ ኢየሱስን ከሃይማኖት ይልቅ የፖለቲካ ችግር እንዳይፈጥር በመፍራት ከፈሪሳውያን ጋር አብረዋል ዮሐ 11፡48-5ዐ ፤ ማር 14፡53 ፣ 15፡1

    - ፈሪሳውያን ደግሞ የነቢያትንና የኦሪት መጽሐፍትን የእምነታቸው መሠረት አድርገው ይቀበላሉ ፤ ለአባቶች ወግና ትውፊትም ትልቅ ሥፍራ ይሰጣሉ ፡፡ ለሰዎች ነጻ ፈቃድ እንዳላቸው ቢቀበሉም የእግዚአብሔርነ መሪነት ያምናሉ ፡፡ ሚሽናህ የተባለውን የአይሁድ የቃል ህግጋት ወደ ጽሁፍ የቀየሩ እነርሱ ናቸው ፡፡ ከፖለቲካ ይልቅ ሃይማኖት ላር ያተኩራሉ ፡፡ በኢኮኖሚም ደረጃቸው መካከለኛ ስለሆኑ ወደ ብዙሃኑ ህዝብ በተሻለ ይቀርባሉ ፡፡ ኀብረተሰቡም ይበልጥ ይቀበላቸው ስለነበር ፣ የምኩራብ ኃላፊዎች ሆነው ከመሥራታቸው በላይ ኀብረተሰቡን በዳኝነት ጉባዔዎች መሪ ሆነው ያገለግሉት ነበር ፡፡ መላእክትንና ዲያብሎስ እንዳሉና ፣ ትንሣዔ ሙታንን ያምናሉ /ሥራ 23፡6/ ፡፡ ከኢየሩሳሌም /ቤተ መቅደስ/ መውደም በኋላም የሃይማኖት ሥራቸው ሳይስተጓጐል በየምኩራቡ ቀጥሏል ፡፡ ኢየሱስን በትንቢት የተነገረው መሲህ እንደዚህ አይደለም በማለት አልተቀበሉትም ፡፡ ስለዚህም ከሰዱቃውያን ጋር ለመግደል ኀብረት ፈጥረዋል ፡፡

    በተረፈ ሥራዎችህ ድንቅ ናቸው ፤ ያቀረብካቸው ትምህርቶች እንዲህ በአንድነት ተሰባስበው የሚገኙ ስላልሆኑ ብዙ ጠቅመውኛል ፡፡ እግዚአብሔር በበለጠ እንድታገለግለው ይርዳህ ፡፡

    ReplyDelete
  6. Here it go! this is a comprehensive beginning of the story of our church [ORTHODOX TEWAHIDO CHURCH ]. It makes sense when we understand how everything begun and ended up where we are. Most people think our Christianity is just an adjunct life of our culture that we inherited from our fathers and living traditionally. But when we learn that the trend of church history, we realize that we missed the core point.

    Here you are elaborating this point from the beginning of creation to where we are in a very precise and fast pace to reach your goal. It is very qualitative and informative for the person who needs to connect the dots across the time line that we rarely see. Keep writing. Let God keep his Grace upon you.

    Samuel Alemie
    Chicago , Illinois.

    ReplyDelete
  7. እግዚአበብሄር አገልግሎትህን ይባርክልህ እና የእድሜዘመንህንም ያርዝምልህ፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. ተሳታፊ በመሆኔ በጣም እድለኛ ነኝ

      Delete
    2. በርታልን ወንድማችን ብሎግህ የማይቀላቅል ፍጹም መንፈሳዊ ይዘት ያለው አስተማሪና ጠቃሚ ነው

      Delete
  8. ፍጻሜህን ያሳምርልን ወንድማችን

    ReplyDelete