Monday, February 18, 2013

ጾመ ነነዌ


እግዚአብሔር ነብዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ምድር በኃጢአታቸው ምክንያት ሊያመጣው ካሰበው የእሳት ዝናም እንዲትርፉ ቢልከው እግዚአብሔርን ቸርነት ስለሚያውቀው ቸርነትህ ከልክላህ ሳታጠፋቸው ብትቀር እኔ የሐሰት ነቢይ እባል የለምን? ብሎ ሰግቶ ወደ ተርሴስ  ሃገር  ከነጋዴዎች ጋር ተሳፈረ።
          እግዚአብሔርም ታላቅ ማዕበልን አስነሳ በመርከቧ ያሉ ሰዎችም እርስ በራሳቸው ዕጣን ተጣጥለው በዮናስ ላይ ወደቀ። እርሱም ያደረገውን ሰለሚያውቅ ሌሎቹ በውሰጥ ያሉት እንዳይጣል ብዙ ጥረት ቢያደርጉም የግድ መጣል ስለ ነበረበት ወደ ባሕር ተጣለ።  እግዚአብሔርም ታላቅ ዓሣ አንበሪን አዘጋጅቶ በከርሠ ዓሣ አንበሪ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ቆይቶ  በሦስተኛው ቀን  በአንጻረ  ነነዌ  ተፍቶታል። በግድም ቢሆን ስለ ሚመጣባቸው መዓት አስተምሯል። ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 1 እና 2 ነብዩ  ዮናስ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አሕዛብ ሀገር የተላከ ነቢይ ነው።

Tuesday, January 29, 2013

36ቱ ቅዱሳት አንስት



36 ቅዱሳት አንስት ስም ዝርዝርና የመታሰቢያ ቀናቸው
36 ቅዱሳት አንስት አንዷማርያም መግደላዊት
ተቁ
ስም
የመታሰቢያ ቀናቸው
1
  ኤልሳቤጥ            
የካቲት 16 
2
  ሐና
መስከረም 7 ቀን
3
  ቤርዜዳን ወይም ቤርስት
ታህሳስ 10 ቀን
4
  መልቲዳን ወይም ማርና
ጥር 4 ቀን 
5
 ሰሎሜ
ግንቦት 25 ቀን    
6
 ማርያም መግደላዊት
ነሐሴ 6 ቀን
7
 ማርያም እንተ እፍረት እህተ አልአዛር
የካቲት 6 ቀን
8
 ሐና ነቢይት