እግዚአብሔር ነብዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ምድር በኃጢአታቸው ምክንያት ሊያመጣው ካሰበው የእሳት ዝናም እንዲትርፉ ቢልከው የ እግዚአብሔርን ቸርነት ስለሚያውቀው ቸርነትህ ከልክላህ ሳታጠፋቸው ብትቀር እኔ የሐሰት ነቢይ እባል የለምን? ብሎ ሰግቶ ወደ ተርሴስ ሃገር ከነጋዴዎች ጋር ተሳፈረ።
እግዚአብሔርም ታላቅ ማዕበልን አስነሳ በመርከቧ ያሉ ሰዎችም እርስ በራሳቸው ዕጣን ተጣጥለው በዮናስ ላይ ወደቀ። እርሱም ያደረገውን ሰለሚያውቅ ሌሎቹ በውሰጥ ያሉት እንዳይጣል ብዙ ጥረት ቢያደርጉም የግድ መጣል ስለ ነበረበት ወደ ባሕር ተጣለ። እግዚአብሔርም ታላቅ ዓሣ አንበሪን አዘጋጅቶ በከርሠ ዓሣ አንበሪ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ቆይቶ በሦስተኛው ቀን በአንጻረ ነነዌ ተፍቶታል። በግድም ቢሆን ስለ ሚመጣባቸው መዓት አስተምሯል። ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 1 እና 2። ነብዩ ዮናስ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አሕዛብ ሀገር የተላከ ነቢይ ነው።
ዮናስ ማለት ርግብ ማለት ነው። ርግብ የዋህ እንደሆነች እሱም የዋህ ነውና ይህ ቅጽል ተቀጽሎለታል። የርግብ የዋህነት እንደምን ነው ቢሉ በማየ አይኅ (በጥፋት ውሃ )ጊዜ በእባብ አፍ ውስጥ እንቁላል ጥላለች። ጌታም በወንጌል “እንድ ርግብ የዋኃን ሁኑ” ብሎ ተናግሯል። ማቴ 10፥16 ዮናስም እግዚአብሔር የሰማይ እና የምድር የቀላያት እና የአብርሕት ፈጣሪ መሆኑን እያወቀ እያስተማረ ከእርሱ ዓይን እይታ ለመራቅ እግዚአብሔር በፈጠረው ባሕር ላይ በመርከብ ተሳፍሮ ሊሸሽ መሞከሩ በራሱ የዋህ ያስብለዋል። በተጨማሪም አብረውት የነበሩ ነጋድያን ከየት ወገን እና ከየት እንደመጣ ሲጠይቁት የሚመልሰው መልስ በራሱ የዋህነቱን ያሳያል የመጀመርያው “ዕብራዊ ነኝ” ሲል መልሷል ዕብራዊ መሆን ሃይማኖት አዋቂ እና ሃይማኖተኛ መሆንን ያሳያል። ሁለተኛው ደግሞ “ባሕሩን እና የብሱን የፈጠረን አመልካለሁ” ብሎ ከ ባህር ፈጣሪ ዐይን እይታ ለመራቅ ወደ ተርሴስ ለመሄድ መሞከሩ በእርግጥም የዋህ የሚያሰኘው ነው።
ሌላው ደግሞ ዮናስን ያስጨንቀው የነበረው የራሱ ቃል (ትንቢት) ተፈጻሚነት አለማግኘቱ እንጂ የነነዌ ሰዎች በእነርሱ ላይ ሊደርስ ከነበረው መዓት መዳን አለመዳናቸው አልነበረም። የሚያስደንቀው ደግሞ በእግዚአብሔር ቸርነት የእርሱ ቃል (ትንቢት) ተፈጻሚነት እንደ ማይኖረው አውቆ ወደ ተላከበት ላለመሄድ አጥብቆ መጠየቁ ነው። ዮና 4፥2
የእግዚአብሔር ነቢይ ለራሱ ቃል ተጨንቆ እንዲህ ያለ የተማጽኖ ቃል ቢያሰማ በእርግጥም ከየዋህነት እንጂ ሳያውቅ ቀርቶ አደለም።”አቤቱ እለምንሃለሁ በሀገሬ ሳለሁ የተናገርኩት ይህ አልነበረም? አንተ ይቅር ባይ ታጋሽ ምሕረትህም የበዛ ከክፉው ነገር የምተጸጸት አምላክ እንደሆንክ አውቄ ነበርና᎐᎐᎐” ብሎ የእግዚአብሔር ቸርነት ማድረግ አሳዝኖት፣ የርሱ ታማኝነት የሚያሳጣ መስሎት አዘነ።
ዮናስ ያዘነው ሰብአ ነነዌ በመዳናቸው ሳይሆን የእርሱ ቃል በእግዚአብሔር መሸፈኑ ነው። ነገር ግን ይህ በራሱ የዮናስን የዋህነት ያሳያል ይኸውም ሰብዓ ነነዌ ገና የርሱን ቃል ሰምተው እንደዚያ ያለ ለውጥ ማምጣታቸው በራሱ የእርሱን ታማኝነት ያሳያል። ምክያቱም ገና አንድ ዐረፍተ ነገር ተናግሮ እንዲያ ለመዳን መንቀሳቀሳቸው የቱን ያህል ቃሉን እነዳመኑትና እንደተቀበሉት ያሳያል! ይህንንም አለማስተዋሉ የዋህነቱን ይመሰክራል።
እግዚአብሔርም የዋህነቱን ስለሚያውቅ ሲያባብለው እና በተለያየ ሁኔታ እና ምሳሌ ሲያስተመረው እናያለን። “ በውኑ ትቆጣ ዘንድ ይገባሃልን” እያለ ይናገረው ነበር ዮና 4፥9 እሰከ መጨረሻ። በእውነት በፍጹም ክፋት አስቦት ቢሆን ኖሮ ሲጀመር እግዚአብሔርም እንዲያስተምርለት አያዘውም ነበር። “᎐᎐᎐ በዓይኑ ትዕቢተኛ የሆነውን እና ልቡ የሚሳሳው ከእኔ ጋር አይተባበርም” እንዲል መዝ 100፥ 5
ሌላው የነነዌ ሰዎች በንስሓ ሕይወት በመለወጥ እንደምሳሌ የሚጠቀሱ ናቸው። ይኸውም ገና በከተማዋ ገብቶ “በሦስት ቀን ወስጥ ትገለበጣለች” ስላለ ብቻ ሀገሩም አመነው አዋጅን አውጀው ፍጹም ጾምን ጾሙ፤ የእግዚአብሔርን መዓት በምሕረት መልሰዋል። የነነዌ ሰዎች ነቢዩ ዮናስ ገና “ ትገለበጣለች “ ስላለ ብቻ ሀገሬው ሙሉ ከንጉሥ እስከ ገረድ ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ሆነው ለለውጥ መነሳታቸው በራሱ ሙሉ በሙሉ የንስሓ ሕይወታቸውን የሚያረጋግጥ ነው።
በአሁኑ ጊዜ መምህራን ሁሉ ትምህርተ ሃይማኖትን እያስተማሩ የንስሓ ሕይወትን እየሰበኩ ለውጡ ግን የትምህርቱን ያህል አለመሆኑ የሰሚውን ጉድለትና ደካማነት ያሳያል “᎐᎐᎐ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሓደ አልጠቀማቸውም”ዕብ 4፥2 እንዲል። ልብ እንበል! ነቢዩ ዮናስ ለሰብአ ነነዌ የተናገረው “ በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች” የሚል አምስት ቃልን ብቻ ነው ። በዚህች ቃል ብቻ ይህን የመሰለ ለውጥ ማምጣት መቻል በራሱ ፍጹም የእግዚአብሔርን ሥራ እንድናደንቅ ይረዳናል።
ስለ ነነዌ ሰዎች የንስሓ ሕይወት ጌታ ራሱ በወንጌሉ መስክሯል። ለሕዝቡም መፈራረጃ አድርጓቸዋል። ሉቃ 19፥32 “᎐᎐᎐በዮናስ ስብከት ንስሓ ገብተዋልና” እንዲል። በተጨማሪም የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ይፈርዱበታ ይላል ማቴ 12፥41
ሌላው እግዚአብሔር መቼም ቢሆን ሰው የተመኘውን አያስቀርም። አዳም አምላክነትን ተመኘ ዘመኑ ሲፈጸም አምላክ ሰው ሆኖ ተምኔቱን (ምኞቱን) ፈጽሞለታል። ዮናስም ምንም እንኳን በቀጥታ እንዲጠፉ ባይፈልግም ውሸታም እንዳይባል ስለሚፈልግ ቀድሞ በተናገረው ቃል መሠረት ትንቢቱ ተፈጽሟል። ። ዮናስ በሦስት ቀን ውስጥ እንዳለ በሦስተኛው ትውልድ ተወግታ ጠፍታለች።
የመጨረሻው ዮናስ ለክርስቶስ ምሳሌው ሆኗል። ይኽውም በሉቃ 11፥30 “ ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደሆናቸው እንዲሁ ደግሞ የሰው ልጅ ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናል” እንዲል። በጌታ ሞትም ምሳሌውሆኗል “ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክትን ይሻል ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀን እና ሦስት ሌሊት እንደ ነበር እንዲሁ የ ሰው ልጅ በምድር ልብ ውስጥ ሦስት ቀን እና ሦስት ሌሊት ይኖራል” እንዲል ማቴ 12፥39።
ሰለዚህ እንዲህ ያሉትን ነገር እያሰቡ የነነዌን ሀገር ሰዎች ተግባር ማየት ከእነርሱም መማር ያስፈልጋል ። እግዚአብሔር ዕድሜ ለንስሐ ዘመን ለፍሥሃ ያድለን
ለንስሐ ሞት
ያብቃን!!
Amen
ReplyDeleteamen, kale hiwoten yasemalen
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማልን። ለመሆኑ እኛ ኢትዮጵያውያን (ከአባቶቻችን ጀምሮ) በእግዚአብሔር ላይ ለፈጸምነው ወንጀል ሁሉ በጋራ ንስሐ የምንገባው መቼ ነው? እግዚአብሔር የሰጠንን የበኩርነት ፀጋ ሁሉ እንደ ኢሳው ለሆድ ስንል አላስልፈን የሰጠን፤ የተቀደሰውን ሁሉ ለውሻ የጣልን ከንቱዎቹ እኛ መቼ ነው እግዚአብሔር አምላክን በአንድ ላይ ሆነን ይቅርታ የምንጠይቀው? ሃገራችን ኢትዮጵያ በአመፀኝነታችንና በሃጢአታችን ብዛት ሳትጠፋ አምላክ ይቅርታ ያደርግልን ዘንድ የተዋህዶ አስተማሪዎች የሆናችሁ ሁሉ ይቅርታ እንጠይቅ ብላችሁ በውን እኛን መሃይምናንን ለቅርብ የንስሃ ቀን የምታዘጋጁን መቼ ነው?
ReplyDeletethank you for your current information!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteamen
ReplyDeletewhat you have done is very appreciable so keep it up
ReplyDeleteAmen!!! Kale hiwot yasemalin! Betene behiwot yitebikilin!
ReplyDeleteAmen
ReplyDeleteAmen. Kale hiwot yasemalin. Egizabhare ragem edemana tena yesteline.
ReplyDeleteቃለ ሄወት ያሰማልን ።ለኛም የሰማነውን አንድንተገብር ዓይ ነ ልቦናችንን ያብራልን።
ReplyDeleteለሕዝበ ክርስቴያን በሙሉ የበረከት ጾም እንዲሆንልን እመኛለሁ።
ከንጉሥ እስከ ገረድ do not use this word ገረድ hulachu bekrestose eyesus andnachu selemil kalu . eventhough nice and excellent sebeket
ReplyDeleteKale hiwot yasemalin
ReplyDeleteDn. Melaku dehina aleh?
Ke 4Killo jemiro ejig awkehalew
Yihin ke ejachin wedko yeneberewin ye ilet migib (Sinkisarun)Alem mayet enditchil bemechalih fetari yimesgen.
Melkam Subae
ፍሬንድ...ገረድ እኮ ስድብ አይደለም.....በዚህ አገባቡ ደግሞ ፍጥሞ ለስድብ አልተጠቀመበትም...አሽከር፣ ሎሌ፣ አገልጋይ፣ ደንገጡር እንደማት ነው.....
ReplyDeleteAMEN!!!
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን
ReplyDeletekindest regards
Daniel from Maryland
ReplyDeletethank
you
thank you
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን
ቃለ ሕይወት ያሰማልን።የአባቶቻችን ፀጋ እግዚአብሔር ይሰጠን
AMEN..AMEN.AMEN
Kalehiwot yasemalen. Amen!!
ReplyDeletebest
ReplyDeleteዲ/ን መላኩ እንዄን አደረሰሕ!!!
ReplyDeleteአሜን!!!
Amen! Amen! Amen! Kale Hiwot Yasemalin!!
ReplyDelete