የጎንደር መንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም የአራቱ ጉባኤያት ት/ቤት በአዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አዳራሽ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሀዲስ በተገኙበት ሰኔ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ አዘጋጅቶላችኋል - ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
Friday, June 22, 2012
Wednesday, May 30, 2012
ጰራቅሊጦስ
ቤተ ክርስቲያናችን ከምታከብራቸው ዓበይት በዓላት መካከል አንዱ በዓለ ጰራቅሊጦስ ነው፡፡ ይህ በዓል ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ደቀመዛሙርቱን ‹አንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እሰከ ትለብሱ ኃይለ እም አርያም › ሉቃ 24፤49 ብሏቸው አርጎ ነበር፡፡ተናግሮ የማያስቀር ነውና ባረገ በ10ኛው በተነሣ በ50ኛው ቀን ጰራቅሊጦስን ሰዶላቸዋል ፡፡
ጰራቅሊጦስ ማለት ፡-
1/ ናዛዚ(አጽናኝ) ማለት ነው ከመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች አንዱ ያዘኑትን የተጨነቁትን በተለያየ ነገር ውስጥ ገብተው ግራ የተጋቡትን ሁለ ሰለሚያጽናና ናዛዚ ይባላል ፡፡
2/ከሣቲ (ምስጢር ገላጭ) ማለት ነው የተደበቀውን የሚገልጥ የረቀቀውን የሚያገዝፍ የተሰወረውን የሚያሳይ በመሆኑ ከሣቲ ( ምስጢር ገላጭ) ይባላል ፡፡
Wednesday, May 23, 2012
ዕርገት
“ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን” መዝ.46፥5
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማታ ማታ እየወጣ የሚያድርባት፣ሐሙስ ሌሊት በይሁዳ በኩል ለአይሁድ ተላልፎ የተሰጠባት፣ሐዋርያት ስለ ነገረ ምጽአት ጠይቀው የተረዱባት፣ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በአርባኛው ቀን ጌታችን ያረገባት ተራራ -ደብረ ዘይት።
ዐርገ የሚለው የግዕዝ ግስ ዐረገ፣ወጣ በሚሉት የአማርኛ ቃላት የሚፈታ ሲሆን ዕርገት የሚለው ስምም ማረግን፣ መውጣትን፣አወጣጥን ያመለክታል።(አ.ኪ.ክ መ.ቃ)
ዕርገት ማለት መውጣት ወይንም ከፍ ከፍ ማለት ነው። ይኸውም ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ መሄድን ይመለከታል። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ነቢይ የሆነው ኤልያስ ሳይሞት በሕይወት እያለ በእሳት ሰረገላ ላይ ተቀምጦ ወደ ሰማይ ማረጉን ይነግረናል። ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ በአርባኛው ቀን ወደ ሰማይ ማረጉን የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
Subscribe to:
Posts (Atom)


