እግዚአብሔር ነብዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ምድር በኃጢአታቸው ምክንያት ሊያመጣው ካሰበው የእሳት ዝናም እንዲትርፉ ቢልከው የ እግዚአብሔርን ቸርነት ስለሚያውቀው ቸርነትህ ከልክላህ ሳታጠፋቸው ብትቀር እኔ የሐሰት ነቢይ እባል የለምን? ብሎ ሰግቶ ወደ ተርሴስ ሃገር ከነጋዴዎች ጋር ተሳፈረ።
እግዚአብሔርም ታላቅ ማዕበልን አስነሳ በመርከቧ ያሉ ሰዎችም እርስ በራሳቸው ዕጣን ተጣጥለው በዮናስ ላይ ወደቀ። እርሱም ያደረገውን ሰለሚያውቅ ሌሎቹ በውሰጥ ያሉት እንዳይጣል ብዙ ጥረት ቢያደርጉም የግድ መጣል ስለ ነበረበት ወደ ባሕር ተጣለ። እግዚአብሔርም ታላቅ ዓሣ አንበሪን አዘጋጅቶ በከርሠ ዓሣ አንበሪ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ቆይቶ በሦስተኛው ቀን በአንጻረ ነነዌ ተፍቶታል። በግድም ቢሆን ስለ ሚመጣባቸው መዓት አስተምሯል። ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 1 እና 2። ነብዩ ዮናስ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አሕዛብ ሀገር የተላከ ነቢይ ነው።