ቤተ ክርስቲያናችን ከምታከብራቸው ዓበይት በዓላት መካከል አንዱ በዓለ ጰራቅሊጦስ ነው፡፡ ይህ በዓል ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ደቀመዛሙርቱን ‹አንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እሰከ ትለብሱ ኃይለ እም አርያም › ሉቃ 24፤49 ብሏቸው አርጎ ነበር፡፡ተናግሮ የማያስቀር ነውና ባረገ በ10ኛው በተነሣ በ50ኛው ቀን ጰራቅሊጦስን ሰዶላቸዋል ፡፡
ጰራቅሊጦስ ማለት ፡-
1/ ናዛዚ(አጽናኝ) ማለት ነው ከመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች አንዱ ያዘኑትን የተጨነቁትን በተለያየ ነገር ውስጥ ገብተው ግራ የተጋቡትን ሁለ ሰለሚያጽናና ናዛዚ ይባላል ፡፡
2/ከሣቲ (ምስጢር ገላጭ) ማለት ነው የተደበቀውን የሚገልጥ የረቀቀውን የሚያገዝፍ የተሰወረውን የሚያሳይ በመሆኑ ከሣቲ ( ምስጢር ገላጭ) ይባላል ፡፡