Monday, April 9, 2012

ሰኞ (ሰኑይ) -ሰሙነ ሕማማት


              ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በዚህ ዓለም ሲመላለስ በሆሳዕና ማግሥት ጌታችን ከቢታንያ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ሁለት ነገሮችን አድርጓል፡፡
አንደኛ ከቅጠል በስተቀር ፍሬ ያልተገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፡፡
ሁለተኛ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡ /ማቴ.21÷12-17 ማር.11÷17 ሉቃ.19÷45-46፡፡/ በቅዱስ ማቴዎስ አገላለጥበማግሥቱ ተራበየሚል ቃል እንመለከታለን፡፡

              ነቢዩ ኢሳይያስእግዚአብሔር ለዘለዓለም አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም” /ኢሳ.46÷25/ ይላል፡፡ በቅዱስ ወንጌልምበመጀመሪያ ቃል ነበርይላል፡፡ ቃል ቀዳማዊ እንደ ሆነ፣ ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ነበር፣ ያም ቃል እግዚአብሔር ነው ተብሎ ተጽፏል፡፡ ዮሐ.1÷1-2፡፡ ጌታችንም በመዋዕለ ትምህርቱም ሲያስተምርየእኔስ መብል የላከኝን የአባቴን ፈቃድ አደርግ ዘንድ፡ ሥራውንም እንፈጽም ዘንድ ነው” /ዮሐ.4÷34/ ሲል ተናግሯል፡፡ ነቢዩ እግዚአብሔር እንደማይራብ ተናግሯል፡፡ ታዲያ ጌታችን ለምን ተራበ?


             ሰማያውያን መላእክት እንዳይራቡ አድርጎ የፈጠረ፣ እስራኤልን ገበሬ በማያርስበት፣ ዘር በሌለበት፡ ዝናብ በማይጥልበት ምድረ በዳ የመገበ ፤ድኅረ ሥጋዌ በአምስት አንጀራና በሁለት ዓሣ 5000 የሚበልጡ ሰዎችን የመገበ ተራበ! ተብሎ ሲነገር እጅግ ይደንቃል፡፡ በእርግጥ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው በመሆኑ አልተራበም አንልም፡፡ የጌታችን ረሃብ ንዴት ያለበትና የአንዲት የበለስ ዘለላ ረሃብ አይደለም፡፡ ረሃቡ የበለስ ፍሬ ሳይሆንበለስ ብሂል ቤተ እስራኤል እሙንቱእንዲል የሃይማኖትና የመልካም ሥነ ምግባርን ፍሬ የሻ መሆኑን ለማጠየቅ ነው፡፡ ጌታችን የፈለገውን ባለማግኘቱ ጉባኤ አይሁድን ረግሟል፡፡ በአይሁድ ጉባኤ የነገሠውን ኃጢአት፤ በበለስ አንጻር መርገሙን ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅበአንጻረ በለስ ረገማት ለኃጢአት፤በበለስ አንጻር ኃጢአትን ረገማትብሏል፡፡

             እስራኤልም በአንድ ወገን የተጠበቀባቸውን ፍሬ ባለማፍራታቸው ተረግመዋል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እስራኤል ከፍቅር ይልቅ እርግማን እንዳገኛቸው አሕዛብ ደግሞ የቃሉን ትምህርት ሰምተው የእጁን ተአምራት አይተው የአመኑበትን የእግዚአብሔር የጸጋ ልጁ ለመሆን መብቃታቸውን ሲመሰክር እንዲህ ይላል፡- “አሕዛብ አስተጋብኡ ጽጌሬዳ በኂሩቱ ወሶኩሰ ተርፈ ኀበ አይሁድ ዘውእቱ ሕፀተ ሃይማኖት፤ አሕዛብ በእግዚአብሔር ቸርነት አበባ ሰበሰቡ፤ በአይሁድ ዘንድ ግን እሾኹ ተረፈ፡፡ ይኽውም የሃይማኖት ጉድለት ነው፡፡ብሎ ተርጉሞታል፡፡ እሾኽ የእርግማን ምሳሌ ነው፤ አበባ የእግዚአብሔር ጸጋ ልጅነት ምሳሌ ነው፡፡ ዛሬ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ጌታችን ወደ መቅደስ ሕይወታችን ቢመጣ ምን ያገኝ ይሆን? ፍሬ ወይስ ቅጠል? የእግዚአብሔር ቃል ግን ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ ይለናል፡፡ ማቴ.3÷8፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገውን የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ እናፍራ፡፡ ገላ.5÷22፡፡ ጌታችን በዳግም ልደት ሲመጣ ከሰው ልጅ ሃይማኖት መገኘቱ አጠራጣሪ እንደሆነ ተናግሯል፡፡የሰው ልጅ ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ሃይማኖት ያገኝ ይሆንን?” ቀጣይ ሕይወታችንን በአምላካዊ ሥልጣኑ የቃኘ አምላክ በመጣ ጊዜ የእምነት ፍሬ አፍርተን ከእግዚአብሔር ዘንድ ዘላለማዊ ፍቅሩን ለማትረፍ እንትጋ፡፡

7 comments:

  1. Thank you my brother and good lesson

    ReplyDelete
  2. kalehiwot yasemaln diakon

    ReplyDelete
  3. Thank you and God bless, This is the truth. Kalehiwot yasemalin! Amen.

    ReplyDelete
  4. ቃለ ህሕወት ያሰማልኝ...

    ReplyDelete
  5. Egziabher Yirdan. GOD bless you Mele! Kale Hiwot Yasemalin.

    ReplyDelete
  6. May GOD bless U with more holly words

    ReplyDelete