በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን፤ ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን። በዛፎችዋ ላይ መሰንቆቻችንን ሰቀልን።የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን፥ የወሰዱንም የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን አሉን ። የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን? ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ብረሳሽ፥ ቀኜ ትርሳኝ። ባላስብሽ፥ ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ። መዝሙር 137:1-6
የጽዮንን በዓል በምናከብርበት በዚህ ሰሞን በታቦተ ጽዮን መገኛ ፤ በግማደ መስቀሉ ማረፊያ ፤ መድኃኔዓለም በስደቱ በጎበኛት ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ የግብረሰዶማውያን ጉባኤ ሊዘጋጅ መሆኑ ሰሞኑን ይነገራል፡፡
መላእክት ሎጥን ከከተማው ካወጡ በኋላ እግዚአብሔር ሰዶምና ገሞራን በእሳትና በዲን አጠፋ የሎጥ ሚስት የጨው ሀውልት ሆነች |
በዘመናት ታሪክ ውስጥ በእግዚአብሔር ዘንድ መጸጸትን፣ የቁጣ ጅራፍን፣
መዓትንና እጅግ መራራ ቅጣትን ካስከተሉ እኩያን ተግባራት መካከል ተፈጥሮ ከሚያዘው ውጪ ወንዶች ከወንዶችና ሴቶች ከሴቶች ጋር
የሚያደርጉት ግንኙነት ወይም ግብረ ሰዶማዊነት አንዱ ነው፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት ስያሜውን ያገኘው ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ
ድርጊቱን በፈጸሙ ሕዝቦች አገር ስም ነው፡፡ ይህ ኃጢአት በተለይ በሰዶም ይበዛ ስለነበር ግብረ ሰዶም ተብሏል፡፡ ሰዶምና
ጐረቤቷ ገሞራ በዮርዳኖስ ሸለቆ አካባቢ የተቆረቆሩ ከተሞች ነበሩ፡፡ በእነዚህ ከተሞች ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ተግባር ከሞራልና
ከተፈጥሮ ሕግ የወጣ አስጸያፊ ስለነበረ እግዚአብሔር የቁጣ በትሩን አሳርፎባቸዋል፡፡ /ዘፍ. 18-20/ ሁለት መላእክት ሎጥን
ከከተማው ካወጡ በኋላ እግዚአብሔር ሰዶምና ገሞራን በእሳትና በዲን አጠፋ፡፡ ዘፍ.12-10-26፡፡ በነዋሪዎቿ ጥፋት በእሳትና
በዲን የተለበለበችው ሰዶም ዛሬ ሕይወት አልባ በሆነው ሙት ባሕር ተሸፍና እንደቀረች ይነገራል፡፡