Wednesday, November 30, 2011

ግብረሰዶማዊነት - ሊወገዝ የሚገባው ተግባር



በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን፤ ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን። ዛፎችዋ ላይ መሰንቆቻችንን ሰቀልን።የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን፥ የወሰዱንም የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን አሉን ። የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን? ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ብረሳሽ፥ ቀኜ ትርሳኝ። ባላስብሽ፥ ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ። መዝሙር 137:1-6


የጽዮንን በዓል በምናከብርበት በዚህ ሰሞን በታቦተ ጽዮን መገኛ ፤ በግማደ መስቀሉ ማረፊያ ፤ መድኃኔዓለም በስደቱ በጎበኛት ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ የግብረሰዶማውያን ጉባኤ ሊዘጋጅ መሆኑ ሰሞኑን ይነገራል፡፡

መላእክት ሎጥን ከከተማው ካወጡ በኋላ እግዚአብሔር
ሰዶምና ገሞራን በእሳትና በዲን አጠፋ የሎጥ ሚስት
የጨው ሀውልት ሆነች
በዘመናት ታሪክ ውስጥ በእግዚአብሔር ዘንድ መጸጸትን፣ የቁጣ ጅራፍን፣ መዓትንና እጅግ መራራ ቅጣትን ካስከተሉ እኩያን ተግባራት መካከል ተፈጥሮ ከሚያዘው ውጪ ወንዶች ከወንዶችና ሴቶች ከሴቶች ጋር የሚያደርጉት ግንኙነት ወይም ግብረ ሰዶማዊነት አንዱ ነው፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት ስያሜውን ያገኘው ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ድርጊቱን በፈጸሙ ሕዝቦች አገር ስም ነው፡፡ ይህ ኃጢአት በተለይ በሰዶም ይበዛ ስለነበር ግብረ ሰዶም ተብሏል፡፡ ሰዶምና ጐረቤቷ ገሞራ በዮርዳኖስ ሸለቆ አካባቢ የተቆረቆሩ ከተሞች ነበሩ፡፡ በእነዚህ ከተሞች ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ተግባር ከሞራልና ከተፈጥሮ ሕግ የወጣ አስጸያፊ ስለነበረ እግዚአብሔር የቁጣ በትሩን አሳርፎባቸዋል፡፡ /ዘፍ. 18-20/ ሁለት መላእክት ሎጥን ከከተማው ካወጡ በኋላ እግዚአብሔር ሰዶምና ገሞራን በእሳትና በዲን አጠፋ፡፡ ዘፍ.12-10-26፡፡ በነዋሪዎቿ ጥፋት በእሳትና በዲን የተለበለበችው ሰዶም ዛሬ ሕይወት አልባ በሆነው ሙት ባሕር ተሸፍና እንደቀረች ይነገራል፡፡


የቀድሞዋ ሰዶምና ገሞራ ከተማ የአሁኑ ሙት(ጨው) ባህር -
The Dead Sea

በዘመነ ኦሪት ይህን ኃጢአት ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ የተገኙ ያለ ምንም ርኅራኄ እንዲገደሉ ታዟል፡፡ «ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋልና ፈጽመው ይገደሉ ደማቸው በላያቸው ነው» /ዘሌ.20-13/ ግብረ ሰዶማዊነት የተጠቀሰውን ዓይነት የከፋ ቅጣት ቢያስከትልም ሰዎች ድርጊቱን ከመፈጸም አልተቆጠቡም፡፡ እስራኤላውያን በተደጋጋሚ ከላይ የተጠቀሰው አምላካዊ ትዕዛዝ ቢነገራቸውም አጸያፊው ተግባር ግን በእነርሱ ዘንድ የተለመደ ነበር /መሳ. 19-22/ 

ይህ በቅዱስ መጽሐፍ የተግባሩ እኩይነት የቅጣቱ አስከፊነት በተጨባጭ የተነገረለት ግብረ ሰዶማዊነት ሳይቋረጥ የዘመናትን ድንበር ተሻግሮ ነውርነቱ እንደ መልካም ተግባር ተቆጥሮ በአራቱ መአዘነ ዓለም እየተፈጸመ ይገኛል፡፡ በተለይም በሥልጣኔ ወደፊት ተራምደዋል የሚባሉት ምዕራባውያን ድርጊቱን ከ1980ዎቹ አጋማሽ ጀምረው በምስጢርና በድብቅ መፈጸማቸውን ትተው ወደ አደባባይ ካወጡት ሰነባብቷል፡፡ የድርጊቱም ፈጻሚዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እጅግ እያሻቀበ መጥቷል፡፡ አንዳንድ ምዕራባውያን አገሮች በሕጋቸው ያጸደቁት ግብረ ሰዶማዊነትን እኩያን የሆኑ አንዳንድ የኪነ ጥበብ ሰዎች የኪነ ጥበብን ሙያ ለወሲብ ንግድ ማስፋፊያ በማዋል በፊልም በሲኒማ እየተወኑ በእርስ በእርስ ጦርነት፣ በረሐብ፣ በኤች አይ ቪ/ኤድስ ቁምስቅላቸውን ለሚያዩ አፍሪካውያን ጭምር እንካችሁ እያሉ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ ምዕራባውያኑ ፈሪሐ እግዚአብሔርን አሽቀንጥረው ጥለው ሕጋዊ ዕውቅና በመስጠት ጭምር ገቢራዊ ያደረጉት የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በእኛይቱ አፍሪካዊ አገር ደቡብ አፍሪካም ገቢራዊ እየተደረገ ነው፡፡ 
ግብረ ሰዶማዊነት ወደ አገራችን የገባው ለተለያየ ጉዳይ ወደ አገራችን በሚመጡ የወጭ አገር ዜጐች እና ለብዙ ዓመታት በምዕራቡ ዓለም ኑረው በተመለሱና በሚመለሱ አንዳንድ ኢትዮጵያውን ጭምር መሆኑን ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች የዚህ አጸያፊ ድርጊት ሰለባ የሆኑትና ሰለባ የሚያደርጉት ቀደም ሲል በእነርሱ ላይ ካለፈቃዳቸው በግብረ ሰዶማውያን ተገደው በመደፈራቸው በመሆኑ ይነገራል፡፡ በተለያዩ ጥቅማጥቅም በመታለል በተፈጸመባቸው ወሲባዊ ጥቃት የእነርሱን የሕይወት መስመር ለመከተል እንዳበቃቸው ከግብረ ሰዶማውያኑ የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙ በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ ግብረ ሰዶማውያኑ ዛሬ በመዲናችን በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች ኅቡዕ ድርጅት በማቋቋም፣ በካፌዎች እና በተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎች ድርጊቱን እያስፋፉ ይገኛሉ፡፡ 
ወደ ሀገራችን በእነዚህ ወገኖች ታዝሎ በገባው የግብረ ሰዶም ተግባር በተለይም ዕድሜያቸው ከ10-14 በሚደርሱ የጐዳና ተዳዳሪዎች፣ በአንዳንድ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እገዛ በሕፃናት ማሳደጊያ ማዕከል በሚኖሩ አዳጊዎች ላይ ሳይቀር ድርጊቱ እየተፈጸመባቸው ነው፡፡ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ሕፃናትንና ወጣቶችን ለማማለል የተለያዩ አደንዛዥ ዕፆችን፣ ከረሜላ፣ ቸኮላት መሳይ ማደንዘዣ፣ ጫት፣ አልኮል እና የሚጤስ ነገር በመጠቀም ካደነዘዙአቸው በኋላ ድርጊቱን ይፈጽሙባቸዋል፡፡ እንዲሁም ጐልማሶችን በተለያዩ መሣሪያዎች በማስፈራራት እንደሚደፍሯቸው አንድ የጥናት ወረቀት ያስረዳል፡፡ /በላይ ሐጎስ፣«euቷለ Aue ቷነደ Eአፐለoፀተቷተፀo o ምቷለe ችሀፀለደረe ፀነ Aደደፀሰ Aበቷበቷ» 2007/
ዓለም በቴክኖሎጂ ምጥቀት ወደ አንድ መንደር እየተለወጠች በመምጣቷ በዓለም ላይ የሚከሰት ሠናይም ሆነ እኩይ ለሆነ ነገር ሁሉ አገራት ተጋለጭ ናቸው፡፡ ከአንድ አገር ወደሌላ በሚደረግ ዝውውር፣ የቴክኖሎጂ የኢንፎርሜሽን እና ከዚሁ ጋር አብሮ በተለያዩ መንገዶች በሚደረጉ የእኩይ ልማድ ልውውጥ ምክንያት የምዕራባውያንን ፈለግ ለመከተል ደፋ ቀና የሚሉ አንዳንድ ወገኖች በአገራችን ብቅ ማለታቸው እየተሰማ ነው፡፡ በመንፈሳዊ ሥነ ምግባር በፈሪሐ እግዚአብሔር እየተጓዘች በኖረችው አገራችን እንደዚህ ዓይነት ድርጊት ለመፈጸም የሚንቀሳቀሱ ሰዎች መነሳታቸው እጅግ ያሳዝናል፤ ያሳስባልም፡፡ በቅድስት አገር ኢትዮጵያ የድርጊቱ ፈጻሚዎች እንቅስቃሴ ከተሰማበት ወዲህ ድርጊቱ ያሳሰባት እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 13 ቀን 2001 ዓ.ም «ጋነፀተeደ ፈoረ ልፀፈe Eተሀፀoፐፀቷ» በተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት አስተባባሪነት «ግብረሰዶማዊነት መብት ወይስ የዝሙት ከፍታ ጫፍ» በሚል ርዕስ ከሃይማኖት ከባሕል፣ ከታሪክ እና ከሳይንስ አኳያ በአፍሪካ ኅብረት በመከረበት ወቅት ድርጊቱን በማውገዝ አቋሟን ገልጻለች፡፡ ከተላለፈው የአቋም መግለጫ የሚከተለው ይጠቀሳል፡፡ «በሀገራችን ሕገ መንግሥት ውስጥ እንደተመለከተው ጋብቻ ክቡር መሆኑን ለቤተሰብም ጥበቃ የሚደረግለት መሆኑን እና በሀገራችን ካሉ የሃይማኖት እሴቶች ተቃራኒ የሆኑ ጉዳዮች በማንኛውም መስፈርት ግብረሰዶማዊነት መብት ተደርጎ ተቀባይነት ማግኘት የማይገባው በመሆኑ ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ይህንን አውቆ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን፡፡» ይላል፡፡
በኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 629 ግብረ ሰዶምና ለንጽሕና ክብር ተቃራኒ የሆኑ ሌሎች ድርጊቶች ድንጋጌዎች አሉት፡፡ ማንም ሰው ከእርሱ ጋር አንድ ዓይነት ጾታ ካለው ከሌላው ሰው ጋር ግብረ ሰዶም ወይም ለንጽሕና ክብር ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነውን ሌላ ድርጊት የፈጸመ እንደሆነ በቀላል እስራት ይቀጣል፡፡ ይኸውም በ630-631 ወንጀሉን የሚያከብዱ ሁኔታዎች ተዘርዝረዋል፡፡ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግም አንቀጽ 13 መሠረት ይህ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕግ የተከለከለ መሆኑ ተደንግጓል፡፡ ከሕግና ከሃይማኖት ከባሕል ከታሪክ አኳያ ድርጊቱ አስጸያፊ በመሆኑ መንግሥትም ቤተ ክርስቲያንም በጋራ ድርጊቱን መከላከል ይጠበ ቅባቸዋል፡፡



ግብረ ሰዶማዊነት ፈሪሐ እግዚአብሔር ተዘንግቶ ከሞራልና ከመንፈሳዊ ሥነ ምግባር ዝቅጠት የሚመነጭ እኩይ ተግባር በመሆኑ ምእመናንም ይህን ሕገ እግዚአብሔርን የጣሰ፣ ከሕዝቡ መልካም ባሕል፣ ማኅበራዊ ትስስር፣ መልካም ሥነ ምግባራዊ አመለካከትና እምነትን የሚቃረን ድርጊትና የድርጊቱን ተዋናዮችን አጥብቀው ሊኮንኑ፣ ራሳቸውንም ሆነ ልጆቻቸውን ጠብቀው በሕገ እግዚአብሔር ጸንተው ሊኖሩ ይገባል፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት የሥነ ምግባርና የሃይማኖት ሕግ ከመጣስም በላይ ከኢትዮጵያዊው ማኅበረሰብ ባሕልና አመለካከት ጋር በተቃርኖ የሚጋጭና ያልተለመደ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም ከጥንት ጀምሮ በሃይማኖት የምትታወቀው የሀገራችን ቀጣይ ትውልድ እና ሁኔታ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ግብረ ሰዶማዊነት በአገራችን እንዳይስፋፋ የበኩላቸውን ይወጡ እንላለን፡፡


የአኩሪ ባሕል ባለቤት እየተባለች የምትጠራው አገራችን በመልካም ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር በፈሪሐ እግዚአብሔር የሚታወቀው ስሟ እንደተከበረ እንዲቀጥል፤ በምዕራባውያን እየተፈበረከ የሚላከው የእኩይ ባሕል ልውውጥ ቁጥጥር በማድረግ መንግሥትም የበኩሉን መወጣት አለበት፡፡ የነገይቷን ኢትዮጵያ እና ቤተ ክርስቲያንን ሊረከብ የሚችል ብቁ ዜጋ በአገራችን እንዲኖር መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሥነ ምግባር መምህራን፣ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ወገባቸውን ታጥቀው ማስተማር አለባቸው፡፡
መንፈሳዊ መነቃቃትን እያጐለበቱ የመጡ ወጣቶችም በዘንድሮ የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ እንደታየው ለሃይማኖታቸው ለመንፈሳዊ ሥነ ምግባር ቅድሚያ በመስጠት መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ማሳደግና ከእኩይ ተግባራት ራሳቸውን ማራቅ ይጠበ ቅባቸዋል፡፡ የምእመናንን ሕይወት በመንፈሳዊ ሥነ ምግባር ለመቅረጽ «በጐቼን ጠብቅ» የሚለውን የአደራ ቃል ከአምላክ የተቀበሉ አባቶች ካህናት ለንስሐ ልጆቻቸው ግብረ ሰዶማዊነት ሊያስከትል ስለሚችለው መንፈሳዊና ሞራላዊ ክስረት አበክረው ቢያስተምሩ ግብረ ሰዶማዊነትን ሳይርቅ ከቅርቡ ሳይደርቅ በእርጥቡ መከላከል ይቻላል፡፡
በአንዲት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር ታቅፈው የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፤ በመንፈሳዊ መርሐ ግብራቸው ላይ «ግብረ ሰዶማዊነት» ከጥንት ጀምሮ እስከ ዛሬ እያስከተለ ያለውን የሞራልና የመንፈሳዊ ሕይወት ዝቅጠት በተመለከተ ትኩረት ሰጥተው ማስተማር አለባቸው፡፡
ሠልጥነናል የሚሉት ምዕራባውያን «ግብረ ሰዶማዊነትን» የሰብአዊ መብት ጥያቄ አድርገው ስላቀረቡ የእነርሱን ድምፅ እንደ ገደል ማሚቱ በሀገራችንም እንዳያስተጋባ ከእያንዳንዱ ቤተሰብ ጀምሮ የሚመለከተው አካል ሁሉ ከወዲሁ የበኩሉን ሊወጣ ይገባል እንላለን፡፡ ለነገው ትውልድ የምትጨነቅ እናት ቤተ ክርስቲያንም ግብረ ሰዶማዊነትን፣ በአጠቃላይም የመንፈሳዊ ሥነ ምግባር መርሆዎችን የሚፈታተኑ ተግባራትን የማውገዝና የማስተማር ተግባሯን አጠናክራ መቀጠል አለባት፡፡

የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር በቸርነቱ ይጎብኘን ፤ በምህረቱ ይማረን አሜን ፡፡
ዋቢ ፡ የማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ ( www.eotcmk.org)


10 comments:

  1. tebarek !! egzabher zemnehen hulu yebarek

    ReplyDelete
  2. Well written. Let's GOD and HIS HOLY MOTHER be with you! Amen.

    ReplyDelete
  3. Dear Melaku
    Egziabhere Ageliglotihin yebarkilihe,
    I always read ur Article it is very educational pls keep it up, we have learned alot.
    ግብረ ሰዶማዊነት ፈሪሐ እግዚአብሔር ተዘንግቶ ከሞራልና ከመንፈሳዊ ሥነ ምግባር ዝቅጠት የሚመነጭ እኩይ ተግባር በመሆኑ ምእመናንም ይህን ሕገ እግዚአብሔርን የጣሰ፣ ከሕዝቡ መልካም ባሕል፣ ማኅበራዊ ትስስር፣ መልካም ሥነ ምግባራዊ አመለካከትና እምነትን የሚቃረን ድርጊትና የድርጊቱን ተዋናዮችን አጥብቀው ሊኮንኑ፣ ራሳቸውንም ሆነ ልጆቻቸውን ጠብቀው በሕገ እግዚአብሔር ጸንተው ሊኖሩ ይገባል፡፡
    May GOD bless u and ur family.
    EGZIABHERE tsegawon yabzalihe
    Cher Yaseman

    ReplyDelete
  4. EGZIABHERE bechrntu yimarne tslote becha new yemiyiseflgwe Ethiopian bechrnto yigobgnte

    ReplyDelete
  5. dn.kale hiwot yasemalin

    ReplyDelete
  6. ዲያቆን መልአኩ
    ፈጣሪ ዕውቀቱን ያብዛልህ።

    “ሠልጥነናል የሚሉት ምዕራባውያን ግብረ ሰዶማዊነትን የሰብአዊ መብት ጥያቄ አድርገው ስላቀረቡ የእነርሱን ድምፅ እንደ ገደል ማሚቱ በሀገራችንም እንዳያስተጋባ ከእያንዳንዱ ቤተሰብ ጀምሮ የሚመለከተው አካል ሁሉ ከወዲሁ የበኩሉን ሊወጣ ይገባል እንላለን፡፡ ለነገው ትውልድ የምትጨነቅ እናት ቤተ ክርስቲያንም ግብረ ሰዶማዊነትን፣ በአጠቃላይም የመንፈሳዊ ሥነ ምግባር መርሆዎችን የሚፈታተኑ ተግባራትን የማውገዝና የማስተማር ተግባሯን አጠናክራ መቀጠል አለባት፡፡”

    መንግሥትም በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩርት ሰጥቶ የሕዝቡን የልብ ትርታ ማዳመጥና ሕገ መንግሥቱ የሚያዘውን የሕግ አንቀጽ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅበታል።

    አምላካችን በምህረቱ ይጎብኘን።
    የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማሪያም አማላጅነት አይለየን።

    ReplyDelete
  7. Well said, protesting an issue with reason like this is appreciated.

    Have you ever thought about citing or giving credit to the sources of your pictures. I think you have to state where you find your pictures to be professional, otherwise it could be viewed as copying from others and discredit them, pillager.

    ReplyDelete
  8. ቃለ ህይወት ያሰማልን ከዚህ አስነዋሪና አስጸያፊ ተግባር እግዚአብሄር ይጠብቀን
    በውነት በጣም ትኩረት ከሚሰጣችው የወቅቱ አንገብጋቤ ጉዳዮች አንዱ በመሆኑ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድናደርግ እግዚአብሄር ይርዳን የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን አሜን::

    ReplyDelete
  9. qalehywetn yasemaln!

    ReplyDelete
  10. በጣም የሚገርመው እኮ መንግስት ይህን ተግባር ወደ ሃገራችን ሲገባ ዝም ያለበት ምክኒያት ኮሚሽን የሚያገኝ እና የሚመለከታቸውም እኛ ምን አገባን የሚል ስሜት እና ጥቅም መሰለኝ ግን እንዲጋባ ሲደረግ የተባበረ እንደ ሶዶም እና ጋሞራ ፍርዳቸውን እግዜር ይሰጣቸዋል ተውልድን ሁሉ እንዲህ አይነቱን ተግባር የሚጸየፍ ያድርግልን እላለሁ፡፡

    ReplyDelete