Tuesday, September 10, 2013

የዘመን አቆጣጠር ባሕረ ሐሳብ -ክፍል 3 - ሰባቱ አዕዋዳት

አዕዋዳት
አዕዋዳት የሚለው ዖደ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲሆን ዞረ ማለት ነው። አዕዋዳት ደግሞ በብዙ እየዞረ የሚመጣ ማለት ነው። የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ጥንት ይጀምራል። ጥንትነቱም ከፍጥረተ ዓለም፣ ከፍጥረተ ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ነው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሳድሲቱ ዐምሲት፣ ዐምሲቱ ራብዒት፣ ራብዒቱ ሳልሲት፣ ሳልሲቲ ካልዒት፣ ካልዒቱ ኬክሮስ፣ ኬክሮሱ ሰዓታት፣ ሰዓታቱ ሳምንታት፣ ሳምንታቱ  ወራት፣ ወራቱ ዓመታት፣ ዓመታቱ አዝማናት እየሆኑ ዛሬ ካለንበት ላይ ደርሰል።
ሳድሲት፣ ሃምሲት፣ ራብኢት … ወዘተ ተብለው የተገለጹት በዘመናዊው አነጋገር ማይክሮ ሰከንድ፣ ሚሊ ሰከንስ፣ ሰከንድ … ወዘተ እንንደሚባሉት እጅግ በጣም ደቃቅ የሆኑ የጊዜ መለኪያዎች ናቸው። ጊዜያቸው ወይም ቆይታቸው ከዓይን ቅጽበት ያነሰ በመሆኑ አንጠቀምባቸውም፤ በዚህም ምክንያት የተለመዱ አይደሉም። ዓለምከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ በፀሐይ 5005 ዓመተ ዓለም ነው። ይኸውም 
. ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት የነበረው 5500 ዘመን ዓመተ ፍዳ ዓመተ ኩነኔ ይባላል።በሐሙስ ዕለት ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ - አምስት ቀን ተኩል ሲፈጸም ከልጅህ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለው” /ቀሌምንጦስ/ እንዳለው አምስት ቀን ተኩል የተባለው ይህ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ማለት ነው። ይህ ሲተነተን  
             ከአዳም እስከ ኖህ ያለው ዘመን 2250                                                   
             ከኖህ እስከ ሙሴ               1588
             ከሙሴ እስከ ሰሎሞን           599
             ከሰሎሞን እስከ ልደተ ክርስቶስ 1063 ድምር 5500 ይሆናል።

Sunday, September 8, 2013

የዘመን አቆጣጠር ባሕረ ሐሳብ -ክፍል 2 -ቅዱስ ድሜጥሮስ

እንኳን ለዘመነ ማርቆስ 2006 ዓ.ም. በሰላም አደረሳችሁ  
ዕንቁጣጣሽ
አዲሱ ዓመት የንስሐ ፤ የቅድስና ፤ የደስታ ፤ የፍስ ፤ የፍቅር ያድርግልን

ቅዱስ ድሜጥሮስ ተካሌ ወይን

ድሜጥሮስ መስታወት ነው-በመስታወት ከዓይን ጉድፍ ከጥርስ እድፍ አይተው እንደሚያጸዱበት ሁሉ ባሕረ ሐሳብንም የተማረ ሰው ዓለም ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ እስከ ምጽአት ድረስ የሚሆነውን ቁጥር ያውቃልና፡፡ ባሕረ ሐሳብ ማለት ቁጥር ያለው ዘመን ማለት ነው፡፡ አንድም ሐሳብ ባሕር ይለዋል ዘመን ያለው ቁጥር ሲል ነው፡፡

ድሜጥሮስ መነጽር ነው፡- መነጽር የራቀውን አቅርቦ፣ የረቀቀውን አጉልቶ፣ የተበተነውን ሰብስቦ እንዲያሳይ እርሱም የተበተኑ አጽዋማትን በዓላትን አቅርቦ ያሳያልና፡፡
ድሜጥሮስ ጎዳና ነው፡- በጎዳናው ተጉዘው ከቤት እንደሚደርሱ ሁሉ፣ ባሕረ ሓሳብም ወደ ኋላ ያለፉትን ወደፊትም የሚመጡትን አጽዋማት በዓላትን ለይቶ ያሳውቃልና፡፡
 ድሜጥሮስ ተራራ ነው፡- በተራራው ጫፍ ላይ በወጡ ጊዜ ምንጩ ሜዳው፣ ግጫው፣ ኮረብታው እንደሚታይ ሁሉ ድሜጥሮስም የአጽዋማት በዓላትን ኢየዓርግ ኢይወርድ ጠንቅቶ ጽፏልና፡፡
ድሜጥሮስ መስተገብረ ምድር (በግብርና የሚተዳደር) ነው፡- 
ይህስ ጥንተ ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ፡-

Sunday, April 7, 2013

ገብር ኄር - የአብይ ጾም 6ኛ ሳምንት



 ይህ ሳምንት የዐብይ ጾም ስድስተኛው ሳምንት ሲሆን እንደሌሎቹ ሰንበታትና ሳምንታት ሁሉ ይህም ሳምንት የራሱ የሆነ መጠሪያ አለው:: ገብር ኄር ይባላል:: ትርጓሜውም በጎ፣ ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው::በዚህ ሳምንት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምታስተላልፈው መልእክት ከባለፈው ሳምንት/ደብረ ዘይት/ የቀጠለ ነው:: የዐብይ ጾም አምስተኛው ሳምንት /ደብረ ዘይት/ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት የሚታሰብበት  ሲሆን ይሄኛው ሳምንት ደግሞ ነቢዩ ዳዊት “እስመ አንተ ትፈድዮ ለኵሉ በከመ ምግባሩ/አንተ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ትከፍለዋለህና/ መዝ 61፡12 እንዳለ ጌታ ዳግም ሲመጣ ለሁላችንም እንደ ሥራችን ዋጋችንን እንደሚከፍለን የምናስብበት ሳምንት ነው::
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ስለ ዳግም ምጽአቱና ስለሚሆነው ምልክት ሲጠይቁት በመጀመሪያ በ70 ዓ ም አካባቢ የሚሆነውን የኢየሩሳሌምን ጥፋት ከዚያም በኋላ እሱ ዳግም ሲመጣ የሚሆኑትን ምልክቶች ከነገራቸው በኋላ ከዚሁ ጋር አያይዞ የእርሱን መምጣት ተከትሎ የሚሆነውን ክስተት በሦስት ምሳሌዎች ለጊዜው ለደቀመዛሙርቱ በመጨረሻ ግን ለሁላችንም እንዲሆን ነግሮናል::
የመጀመሪያው በቤተሰቦቹ ላይ የሾመውን የጌታውን አደራ በሚገባ በመወጣቱ በጌታው ዘንድ በተመሰገነው በልባሙ ባሪያ ምሳሌነት ለመልካም የሚተጉ ሰዎችን አስደሳች ፍጻሜ፣ እንደዚሁም በተቃራኒው የጌታውን አደራ ችላ በማለት የማይገባ ሥራ በመሥራት ጊዜውን ባባከነው ክፉ ባሪያ ምሳሌነት የቸልተኞችን አስከፊ ፍጻሜ የሚያሳየው ነው (ማቴ 24፡45-51)::
ሁለተኛው የሙሽራውን መምጣት በዝግጅት ይጠብቁ በነበሩ በአምስቱ ብልሆች ደናግላን ምሳሌነት የዝግጁዎችን ስኬታማ ፍጻሜ፣ እንደዚሁም ባልተሟላ ዝግጅት የሙሽራውን መምጣት ሲጠባበቁ በነበሩ በአምስቱ ሰነፎች ደናግላን ምሳሌነት ማስተዋልና ጥንቃቄ በጎደለው ሕይወት የሚኖሩ ሰዎችን ፍጻሜ የሚያሳየው ነው ፡፡ (ማቴ 25፡1-13)
ሦስተኛው ደግሞ ከመጀመሪያዎቹ ሁለቱ በተለየ መልኩ በዚህ ሳምንት በይበልጥ የሚታሰቡ ከጌታቸው ዘንድ መክሊትን የተቀበሉ ባሮችን ታሪክ የያዘው ምሳሌ ነው::