አዕዋዳት
አዕዋዳት የሚለው ዖደ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲሆን ዞረ ማለት
ነው። አዕዋዳት ደግሞ በብዙ እየዞረ የሚመጣ ማለት ነው። የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ጥንት ይጀምራል። ጥንትነቱም
ከፍጥረተ ዓለም፣ ከፍጥረተ ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ነው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሳድሲቱ ዐምሲት፣ ዐምሲቱ ራብዒት፣ ራብዒቱ
ሳልሲት፣ ሳልሲቲ ካልዒት፣ ካልዒቱ ኬክሮስ፣ ኬክሮሱ ሰዓታት፣ ሰዓታቱ ሳምንታት፣ ሳምንታቱ ወራት፣ ወራቱ
ዓመታት፣ ዓመታቱ አዝማናት እየሆኑ ዛሬ ካለንበት ላይ ደርሰል።
ሳድሲት፣ ሃምሲት፣ ራብኢት … ወዘተ ተብለው የተገለጹት
በዘመናዊው አነጋገር ማይክሮ ሰከንድ፣ ሚሊ ሰከንስ፣ ሰከንድ … ወዘተ እንንደሚባሉት እጅግ በጣም ደቃቅ የሆኑ የጊዜ መለኪያዎች
ናቸው። ጊዜያቸው ወይም ቆይታቸው ከዓይን ቅጽበት ያነሰ በመሆኑ አንጠቀምባቸውም፤ በዚህም ምክንያት የተለመዱ አይደሉም።
ዓለምከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ በፀሐይ 5005 ዓመተ ዓለም ነው። ይኸውም
ሀ.
ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት የነበረው 5500 ዘመን ዓመተ ፍዳ ዓመተ ኩነኔ ይባላል። “በሐሙስ ዕለት ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ
- አምስት ቀን ተኩል ሲፈጸም ከልጅህ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለው”
/ቀሌምንጦስ/ እንዳለው አምስት ቀን ተኩል የተባለው ይህ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ማለት ነው። ይህ ሲተነተን ፦
ከአዳም እስከ ኖህ ያለው ዘመን
2250
ከኖህ እስከ
ሙሴ 1588
ከሙሴ
እስከ ሰሎሞን 599
ከሰሎሞን እስከ ልደተ ክርስቶስ 1063 ድምር 5500 ይሆናል።

