“መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም፤ ባንበላም ምንም አይጎድለንም ብንበላም ምንም አይተርፈንም።” ፩ቆሮ.፰፡፰
ዳግመኛም ቅዱስ ጳውሎስ
“ሁሉ ተፈቅዶልኛል፡ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሰለጥንብኝም መብል ለሆድ ነው ሆድም ለመብል ነው” ብሏል።
‘አሁንስ ይላል እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁ በጾምም በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ፡፡’’ ኢዩ.፪፡፲፪
‘በጽዮን መለከትን ንፉ ጾምንም ቀድሱ፡፡ ጉባኤውንም አውጁ፡፡’’ ኢዩ.፪፡፲፭
ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መከልከል ማለት ነው፡፡ ወይም ለሰውነት የሚያምረውንና የሚያስጉመዠውን ነገር መተው ማለት ነው፡፡ ሃይማኖት ባለበት ቦታ ሁሉ ጾም አለ፡፡ ጾም ከሃይማኖት ጋር ዘለዓለማዊ ዝምድና አለው፡፡ ከጥንት ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምሮ ጾም ከፍተኛ ቦታ አለው፡፡ የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ጋር በሚገናኙበት ወራት እህል ውኃ በአፋቸው አይገባም ነበር፡፡ ዘጸ.፴፬፡፳፰