አዲስ አበባ መናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
|
የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠፆሙ ያርምሙ አንከሩ ምህሮቶ ሞገስ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፡፡
ትርጉም: ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤ ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው ፡፡ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት፤ቤቴስ የጸሎት ቤት ይባላል (እያለ የሃይማኖትን ቃል አስተማራቸው) ፤ ወደ ምኩራባቸውም ገብቶ ዝም ይሉ ዘንድ ገሠፃቸው፤ እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩን ጣዕምና፣ የአንደበቱን ቅልጥፍና አደነቁ።
(ቆላ. 2÷16-ፍጻ.) እንግዲህ በመብልም ቢሆን÷ በመጠጥም ቢሆን÷ በልዩ ልዩ በዓላትም ቢሆን÷ በመባቻም ቢሆን÷ በሰንበትም ቢሆን የሚነቅፋችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፡፡ ......
(ያዕ.5÷14) ወንድሞቻችን ሆይ÷ እምነት አለኝ፤ ምግባር ግን የለኝም የሚል ሰው ቢኖር÷ ምን ይጠቅመዋል? በውኑ እምነቱ ልታድነው ትችላለችን? ከወንድሞቻችን÷ ወይም ከእኅቶቻችን÷ የታረዙ ወይም የዕለት ምግብ ያጡ ቢኖሩ÷ ከእናንተም አንዱ .......
ግብረ ሐዋርያት
(የሐዋ.10÷1-8.) በቂሳርያም ቆርኔሌዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራም የመቶ አለቃ ነበር፡፡ እርሱም ጻድቅና ከነቤተሰቡ እግዚአብሔርን የሚፈራ ነበር፤ ለሕዝቡም ብዙ ምጽዋት ይሰጥ ነበር፤ ዘወትርም ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር፡፡
........
ምስባክ
መዝ 68፡9
እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡
ትርጉም፦የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና
ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፡፡
እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡
ትርጉም፦የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና
ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፡፡
ወንጌል
• ዮሐ. 2÷12-ፍጻ. ከዚህም በኋላ እርሱና እናቱ÷ ወንድሞቹና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ቅፍርናሆም ወረዱ፤ በዚያም ብዙ ያይደለ ጥቂት ቀን ተቀመጡ፡፡ ........
ቅዳሴ: - ቅዳሴ ዘእግዚእ
Hi Deacon I think Misbaku ye next week new?
ReplyDeleteQalehiywot yasemalin rejim yeaglgilot zemin yistilin.
ReplyDeleteyeabyi tsom 3tegnaw samint misbak mezmur 68 quter 9 lay yalew ESME QNAT BETEKE BELHANI...... Sihon post kaderkew lay gin lela new...
keanbabiwoch andu negn
በቻህን ሆነህ ከሆነ ይህን ሁሉ የምትሰራው በእርግጥ ይከብዳል.....ተመዳድባችሁ ከሆነ ግን ወንጌሉ ላይ ትርጓሜውን ብትጨምርበት በጣም ጥሩ ነው...
ReplyDeleteበነገራችን ላይ 3ኛ ሳምንት እንዴት ይባላል...ገና ሁለተኛ አይደል እንዴ? እባክህ አልገብቶም....liyuhosi@gmail.com
ReplyDeleteKeep it up.Yemitech mechem bihon aytefam.
ReplyDeleteKale hiwot Yasemalin! Amen.
ትምህርቱ፡ስለ፡መጪው፡ሦስተኛው፡የዓቢይ፡ጾም፡ቀድሞ፡ተሰጠን፡እንጂ፡ዲን.መላኩ፡ሑለተኛው፡ሳምንት፡
ReplyDeleteነው፡ብሎ፡አለማቅረቡን፡እናስተውል!ስለ"አንደኛውና፡ሁለተኛው፡ሳምንት፣"የተነበቡ"የሚለውን፡ማውጫ፡ብንመለከት፣ሁሉም፡በየተራቸው፡መቅረባቸውን፡እንረዳለን።ዲን.መላኩ፡እግዚአብሔር፡ያበርታህ፤በትጋት፡ለምታቀርባቸውም፡በተዋሕዶ፡ላይ፡የተመሠረቱ፡ትምህርቶች፡ተቀባይ፡ያብዛልህ!
ስለ፡ዋልድባ፡ገዳም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እናልቅስ!
ስለ፡ስልጢና፡አላባም፡ሕዝበ፡ክርስቲያን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እናልቅስ!!
ስለ፡ተዋሕዶ፡ኢትዮጵያ፡በሙሉ፡በምሕረቱ፡እንዲታደገን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እናልቅስ!!!
የጻድቃንና፡ሰማእታት፡አምላክ፡ማረን፣ይቅር፡በለን፣
በእንተ፡እግዚእትነ፡እግዚኦ፡መሐረነ፡ክርስቶስ!!!አሜን
ሳሙኤል፡ዘአሰቦት
Dn. Melaku ....Betam Yemadinkihi EgziAbHer'm Enditebikhi ena Yebelete tsega endisethi yemimegnilihi YeTewahedo lij neh. And asteyayet begilts listhi ena tegibereh liyih. Please Mention a source where you took something at least give a credit for who typed first and you copied and pasted so i hvae seen you for the last 3 weeks you copied from mahibere kidusan site and you didn't mentioned (minch) so please don't do that . i hope you know the truth and do the truth.Let me tell you what i did.... one day one sunday school somebody brought your writing and didn't mentioned the source that's you and i told the guy to mention the source as "Sinksar of Dn Melaku Ezezew". I hope since this is an advice you can keep this comment to yourself ...and starting next week i hope i will see source at least for creating the idea ( esuma tsome digua neww sourcu ante gin copy sitaderg keyet endehone mention adrig).....Tsomun yibarkilin. Ewidihalew Bertalign yeTewahido lij. Andu kin ena yemsasalhi wondimhi negn!!!!
ReplyDeleteትእግስቱን ብርታቱን ይስጥህ ፣ በርታ።
ReplyDeleteto Anonymous March 4, 2012 at 11:13 AM
ReplyDeletebete kirstiyanachin wete yehone sirat yalat nat! silzih mahibere kidusanm hone dn. melaku post yaderegut ke"GITSAWE"awttew silehone
korejik minch tikes ayibalem!
Egziabher Kale hiwotin yasemalin! Beselam betena yitebikilin!
ReplyDelete