Tuesday, January 15, 2013

ምሥጢረ ሥላሴ

                  እንኳን ለጥር ሥላሴ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ምሥጢር
አመሠጠረ ከሚለው ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ስውር ፣ ድብቅ ፣ ሽሽግ ማለት ሲሆን አምስቱ አዕማደ ምሥጢራትም ምሥጢር የተባሉበት ምክንያት
  • በሥጋዊ ጥበብ ምርምር መረዳት ስለማይቻሉ
  • ላመኑት እንጂ ላላመኑት ሰዎች የተሰወሩ በመሆኑ
 ምሥጢር በሁለት ይከፈላል፡፡ እነርሱም፡-
 የፈጣሪ ምሥጢር፡- ሊገለጥ የማይችል ነው፡፡ ከ እስከ የሌለው ምሥጢርም ይባላል፡፡
 የፍጡራን ምሥጢር፡- በጊዜ የሚገለጥ /የሚታወቅ/ ነው፡፡ የሰውና የመላእክት ምሥጢር በዚህ ውስጥ የሚካተት ነው፡፡

ምሥጢረ ሥላሴ
ሥላሴ፡- የግእዝ ቃል ሲሆን ሦስትነት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አንድ ሲሆን ሦስት ፣ ሦስት ሲሆን አንድ ነው፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ሦስትነት ልዩ ሦስት ነው፡፡ ሦስት ብቻ ተብሎ አይቆምምና ሦስት ሲሆን አንድም ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር የአንድነት የሦስትነት ባለቤት በመሆኑ ሥላሴ ይባላል፡፡
 የእግዚአብሔር አንድነት
 እግዚአብሔር አንድ ነው ስንል በመለኮት ፣ በባሕርይ ፣ በአገዛዝ ፣  በሥልጣን ፣ በሕላዌ /ሕልውና/ በመፍጠር በልብ በቃል በእስትንፋስ ይህን ዓለም በመፍጠር እና በማሳለፍ ይህን በመሳሰለው ነው፡፡

  በመፍጠር መዝ 101፡25 ፣ ዘፍ 1፡1 ፣ ኢሳ 66፡1-2 
  በሥልጣን ዮሐ 10፡30 
  በመለኮት መለኮት ማልኩት ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ ሲሆን መንግስት ግዛት ማለት ነው፡፡ ይህም ለእግዚአብሔር ብቻ የተሰጠ ነው፡፡ ቆላ 2፡9፣ 1ኛ ጴጥ 1፡3 
  በሕላዌ /ሕልውና/  አኗኗር ማለት ነው፡፡ መብለጥ ፣ መቅደም ፣ መቀዳደም የለባቸውም፡፡ ዮሐ 1፡1-2፣ ዮሐ 14፡10 
ጎንደር ደብረብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን የውስጥ ገጽታ

የእግዚአብሔር ልዩ ሦስትነት
 እግዚአብሔር በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ነው፡፡
 የስም ሦስትነት አብ ወልድ መንፈስቅዱስ ናቸው፡፡ ማቴ 28፡19፡፡
እግዚአብሔር አብ፡- ከዘለዓለም እስከዘለዓለም ከሦስቱ አካላት የአንዱ የአብ ስም ነው፡፡ 1ኛ ጴጥ 1፡2፣ ዮሐ 3፡16
እግዚአብሔር ወልድ፡- ከዘለዓለም እስከዘለዓለም ከሦስቱ አካላት የአንዱ የወልድ ስም ነው፡፡ ወልድ ሰው በሆነ ጊዜ በተለያ ስሞች ተጠርቷል፡፡ እነዚህም፡-
        ኢየሱስ- መድኃኒት አዳኝ ማለት ነው፡፡ ማቴ 1፡21
         ክርስቶስ- መሲሕ /ንጉሥ/ ማለት ነው፡፡ ሉቃ 2፡11፣ ዮሐ 4፡25
         አማኑኤል-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው፡፡ ትን.ኢሳ 7፡14 ፣   ማቴ 1፡21

እግዚአብሔር ወልድ ን አምላክነት አስረጂ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ዮሐ 20፡9 ፣ ሮሜ 10፡12 ፣ ዮሐ 1፡1 ፣ ዮሐ 1፡14 ፣ ዮሐ 20፡28 ፣ ዮሐ 4፡42 ፣ የሐዋ.ሥራ 20፡28 ፣ ራዕይ 1፡8 ፣ ትን.ኢሳ 9፡6 ፣ ራዕይ 22፡12 ፡፡
 እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- ከዘለዓም እስከ ዘለዓለም ከሦስቱ አካላት የአንዱ መንፈስ ቅዱስ ስሙ ነው፡፡
 መንፈስ ቅዱስ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፡፡
  • መንፈስ- ዮሐ 3፡5 ፣ 1ኛ ቆሮ 12፡4 ፣ ዘፍ 1፡2 ፣ ትን.ኢሳ 48፡16
  • የእግዚአብሔር መንፈስ - ት.ኢሳ 61፡6
  • ጰራቅሊጦስ /አጽናኝ/ እየተባለ ይጠራል፡፡ ዮሐ 15፡26 ፣ ዮሐ 14፡16 ፣ ዮሐ 16፡7
  • የእውነት መንፈስ፡፡ ዮሐ 15፡26

የአካል ሦስትነት
    ለአብ ፍጹም ገጽ ፣ ፍጹም መልክ ፣ ፍጹም አካል አለው፡፡
    ለወልድም ፍጹም ገጽ ፣ ፍጹም መልክ ፣ ፍጹም አካል አለው፡፡
    ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም ገጽ ፣ ፍጹም መልክ ፣ ፍጹም አካል አለው፡፡
የግብር ሦስትነት
የአብ ግብሩ መውለድ ማስረጽ ፣ የወልድ ግብሩ መወለድ ፣ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መስረጽ ነው፡፡ አብ ወልድን ውልዷል ፤ መንፈስ ቅዱስን አስርጽዋል ፤ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ሰርጽዋል፡፡ ወልድ ከአብ ተወልዷል ፡፡

  • አብ ወልድን ወለደ ማለት ፤ ከአካሉ ከባሕርይው ፤ አስገኘው ማለት ነው፡፡
ምሳሌ የሰው ነፍስ ልብነቷ /አሳቢነቷ/ ቃልነቷን እንደሚያስገኘው

  • ወልድ ከአብ ተወለደ ማለት ፤ አብን አክሎ አብን መስሎ ከአብ ተገኘ ማለት ነው፡፡
ምሳሌ የነፍስ ቃልነቷ ከልብ እንደተገኘ

  • አብ መንፈስ ቅዱስን አሰረጸው ማለት ፤ ከአካሉ ከባሕርይው አስገኘው ማለት ነው፡፡
ምሳሌ የነፍስ ልብነቷ እስትንፋስነት /ሕይወትነቷን/ እንዳስገኘ ማለት ነው

  • መንፈስ ቅዱስ ከአብ ሰረጸማለት ፤ አብን አህሎ አብን መስሎ ከአብ ተገኘ ማለት ነው፡፡
ምሳሌ የነፍስ እስትንፋስነቷ ከልብ እንደተገኘ

 ይህ ማለት ግን መቀዳደም ፤ መበላለጥ አለባቸው ማለት አይደለም ፡፡
ጎንደር ደብረብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን የውጭ ገጽታ

ለምሥጢረ ሥላሴ የፍጡራን ምሳሌ

የሰው ነፍስ፡- የመናገር ፣ የማሰብ ፣የመተንፈስ /የሕያውነት/ ሁኔታ አላት፡፡
ማሰብ በአብ ፤ መናገር በወልድ ፤ ሕያውነት በመንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡
የነፍስ ልብነቷ ቃልነቷን ሕይወትነቷን ከራሷ ታስገኛለች፡፡
ነፍስ ስትገኝ በሦስትነቷ በአንድ ጊዜ ተገኘች እንጂ ልብነቷ ቀድሞ ቃልነቷ እስትንፋስነቷ በኋላ አልተገኘም፡፡ ነፍስ በኩነታት ሦስትነት ቢኖራትም በአካል አንድ ናት፤ ሥላሴ ግን አብ አካላዊ ልብ፤ ወልድ አካላዊ ቃል ፤ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ እስትንፋስ ነው፡፡

ፀሐይ፡- አንድ ስትሆን ሦስትነት አላት፡፡ አካሏ ፣ ብርሃኗ ፣  ሙቀቷ ናቸው፡፡ አካሏ በአብ፣ ብርሃኗ በወልድ፣ ሙቀቷ በመንፈስ ቅዱስ ይመስላል፡፡

ባሕር፡- ስፋቱ በአብ፣ ርጥበቱ በወልድ ፣ ማዕበሉ በመንፈስ ቅዱስ ይመሰላል፡፡

ስለ ምሥጢረ ሥላሴ የማገናዘቢያ ጥቅሶች ፡-

            በብሉይ ኪዳን     
ት.ኢሳ 48፡12 ፣ መዝ 117፡16፣ ዘኁ 6፡24 ፣ ዘፍ 3፡22 ፣ት.ኢሳ 6፡3 

            በሐዲስ ኪዳን
1ኛ ቆሮ 19፡14 ፣ ማቴ 17፡15 ፣ ሉቃ3፡22 ፣ ማቴ 28፡19 ፣ ማቴ 3፡16 ፣ ዩሐ 16፡7 ፣ የሐዋ.ሥራ 7፡55 ፣ ዮሐ 14፡15 ፣ ራዕይ 14፡1-2

በዓሉን በዓለ ሰላም ፤ በዓለ ክብር ፤ በዓለ ፍስሐ ያድርግልን - አሜን

29 comments:

  1. Diakon Kal Hiwote Yiasemalen,Yiaglglote Zemenewoten Yiarzemlen. Mitafite yehiwote Kal Ena Temeherte nwe.

    ReplyDelete
  2. ዲያቆን
    ቃለ ህይወት ያስማልን !!!
    ዕድሜ ይስጥልን ባባትህ እግር ተተክትህ የጌታ አገልጋይ እንድትሆን አምላክ ይርዳህ እመቤታችን ትጠብቅህ::
    01/13/2012 @ 10:42AM

    ReplyDelete
  3. endezih berta wotatun ketelat tebikew.....woladite amlak fitsamehen tasamirilih

    ReplyDelete
  4. I suggest Begashaw better visite this cite and learn before he opens his mouth and try to talk about some thing he doesn't even understand for himself. I think any ordinary Tewahido believer has better understanding of MISTRE SILLASSIE than Begashaw. Far more! Don't let him confuse you my people.

    ReplyDelete
  5. ሳሚ(ወ/ሚካኤልJanuary 24, 2012 at 6:41 PM

    ቃለህይዎት ያሰማልን!!!ልንናገረው እነጅ ልንተረጉመው የማንችለውን ይህን ረቂቅ ሚስጥር ጌታ መንፈስ ቅዱስ ገልጦልን እስከመጨረሻይቱ ሕቅታችን ድረስ ልዩ ሶስትነቱን ማመንን ይፈጽምልን!!!አሜን!!!!

    ሳሚ(ወ/ሚካኤል)ሰመራ

    ReplyDelete
  6. ቃለ ህይወት ያሰማልን ዲያቆን
    የተዋህዶን ሚስጥር ለሚሹ ትሩ ትምህርት ነው

    ReplyDelete
  7. qal hiwot yasemalen

    ReplyDelete
  8. ቃለ ሕይወት ያሰማልን።

    ReplyDelete
    Replies
    1. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ወንድማችን ዲያቆን

      Delete
  9. ዲያቆን መላኩ የአገልግሎት ዘመንህን እግዚአብሔር ይባርክልህ፣ ጸጋውን ያብዛልህ!


    ReplyDelete
  10. Kale hiwot yasemalin! Egziabher beselam betena yitebikilin!

    ReplyDelete
  11. ቃለ ህይወት ያስማልን !

    ReplyDelete
  12. ዲያቆን መልአኩ
    ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
    አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ከነቤተሰብህ ይባርክ!
    ሁላችንንም ይጠበቀን!
    አሜን።

    ReplyDelete
  13. እንዳትታዘበኝ እንጂ....የአመቱ በዓል ምክንያት ግን አልተገለጠም...የጥር ሥላሴ ምን የተደረገበት በዓል ነው፡፡ እባክህ ንገረኝ...liyuhosi@gmail.com

    ReplyDelete
  14. ቃለ ህይወት ያስማልን !

    ReplyDelete
  15. ቃለ ሑወት ያሰማልን።

    ReplyDelete
  16. ቃለ ህይወት ያስማልን !
    አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ከነቤተሰብህ ይባርክ!
    ሁላችንንም ይጠበቀን!
    አሜን።

    ReplyDelete
  17. ቃለ ህይወት ያስማልን !
    አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ከነቤተሰብህ ይባርክ!
    ሁላችንንም ይጠበቀን!
    አሜን።

    ReplyDelete
  18. ዲያቆን መላኩ ቃለ ህይወት ያሰማልን ስላሴዎች በሰላም በጤና ይጠብቁልን።

    ReplyDelete
  19. በቫም ጠቃሚ ነገር ነው ያወኩት እግዚአብሔር ያክብርልን

    ReplyDelete
  20. ቃለ ሕይዎት ያሰማልን፣ አጋዕዝትዓለም ሥላሴ እረዴታቸው አይለየን።

    ReplyDelete
  21. ቃለ ሕይዎት ያሰማልን፣ አጋዕዝትዓለም ሥላሴ እረዴታቸው አይለየን።

    ReplyDelete
  22. ቃለ ሕይዎት ያሰማልን፣ አጋዕዝትዓለም ሥላሴ እረዴታቸው አይለየን።

    ReplyDelete
  23. ቃለሕይዎት ያሰማልን፣ አጋዕዝትዓለም ሥላሴ እረዴታቸው እና ጥበቃቸው አይለየን።

    ReplyDelete
  24. ቃለሕይዎት ያሰማልን፣ አጋዕዝትዓለም ሥላሴ እረዴታቸው እና ጥበቃቸው አይለየን።

    ReplyDelete
  25. ቃለሕይዎት ያሰማልን፣ አጋዕዝትዓለም ሥላሴ እረዴታቸው እና ጥበቃቸው አይለየን።

    ReplyDelete