Friday, July 11, 2014

ቅዱስ ጴጥሮስ

ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ ጳውሎስ

እንኳን ለቅዱስ ጴጥሮስ እና ለቅዱስ ጳውሎስ በዓለ ዕረፍት መታሰቢያ ሐምሌ 5 በሰላም አደረሳችሁ



በሸመገልህ ጊዜ እጆችህን ትዘረጋለህ ሌላውም ያስታጥቅኻል ወደማትወደውም ይወስድሀል  
                  ዮሐ. 21÷18

ቅዱስ ጴጥሮስ




ቅዱስ ጴጥሮስ  የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው ቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ዮሐ. 1፥45፡፡ የአባቱ ስም ዮና ሲሆን ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው፡፡ ዮና ከነገደ ስምዖን የምትሆን አንዲት ሴት አግብቶ ቅዱስ ጴጥሮስን ወለደ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ከተወለደ በኋላ እንደ ሕገ ኦሪት ትእዛዝ በስምንተኛው ቀን ወደ ግዝረት ቤት አግብተው ስሙን በእናቱ ነገድ ስም ስምዖን ብለው ሰይመውታል፡፡
      እድሜው አምስት ዓመት ሲሆን እንደ አይሁድ ሥርዓት ሕገ ኦሪትን እየተማረ እንዲያድግ በቤተ ሳይዳ አጠግብ ወደሚገኘው ወደ ቅፍርናሆም ሰደዱት፡፡ በዘመኑ በባህር ዳር በምትገኘውና ታላቅ የንግድ መናኸርያ በነበረችው በፍቅር ናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረችው በቅፍርናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረው ኢያኢሮስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት አሰርቶት በነበረው ምኩራብ እየተማረ አደገ፡፡