Friday, October 25, 2013

ብሂለ አበዉ 1

·         ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው  ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ›› 
አባ እንጦንስ
·         ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል››     
  ቅዱስ አትናቴዎስ
·         ‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል››             
        ቅዱስ ሚናስ
·         ‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና›› 
        ታላቁ አባ መቃርስ
·         ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም››
  ቅዱስ አርሳንዮስ
·         ‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል››              
        ቅዱስ እንድርያስ
·         ‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን››                           
  አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን
·         ‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው››  
  ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
·         ‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ››    
  ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
·         ‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር›› 
  ቅዱስ ይስሀቅ ሶርያዊ
·         ‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል  ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል››
  ቅዱስ እንጦ   

o   ለተወሰን ጊዜ ለሀይማኖት መከራከር፤ጠበቃ መሆን፤መዋጋት ብሎም መሞት አይከፋም ሁልጊዜ ለሀይማኖት መኖር ግን ከሁሉ የበለጠ መስዋእትና ክብር ያለው ህይወት ነው፡፡

o   የረብዑ ምግብ ለሀሙስ የአርብ ምግብ ለቅዳሜ ይጠቅማል ነገር ግን የማክሰኞ ምግብ ለረብዑ አይጠቅምም የሀሙስ ምግብ ለአርብ አይሆንም የነፍስና የስጋ ነገርም እዲሁ ነው፡፡
o   የነፍሳችን ነገር ትተን የስጋችንን ብቻ የምናደልብ ከሆነ ነፍስን በስጋ መቃብር እየቀበርናት መሆኑን አንርሳ
o   አንድ በርሜል ወተት በአንድ ጠብታ ኮምጣጤ የበጣጠሳል የብዙ ጊዜ ተጋድሎንም ጠብታ የሀጢያት ኮምጣጤ ያበላሸዋል
o   ራስህን በሀሰት አትውቀስ፡፡ራስህ መክሰስ ትህትና አይደለም፡፡ ታላቅ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስ ነው
o   ትዕቢት ሰይጣን ያለመው ጦር ነው
o   ትህትና ህፀፅን የምታስታውቅ መስታወት ናት
o   ክርስትና ማለት የሰውን ሸክም መሸከምና እስከሞት ድረስ መፅናት ማለት ነው
o   በባልንጀራው ላይ ክፋትን የሚያስብ ሰው ያችው የሚያስባት ክፋት ራሱን ትጎዳዋለች፡፡ በየትና ምን ጊዜ እደምትጥለው ግን አያውቅም
o   ስንፍናውን ወደጥበብ፤አላዋቂነቱን ወደእውቀት ፤መጥፎ ጠባዩን ወደበጎነት የሚመልስ ሰው ብርቱ ነው
o   ፀሎት ገንዘብን ሊያመጣ ይችላል፡፡ ገንዘብ ግን ፀሎትን አያመጣም፡፡
  o   ራስህን በሐሰት አትውቀስ ራስን መክሰስ ትህትና አይደለም ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስ  ነው፡፡                 
   ቅዱስ ስራፕዮን
ò የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ                                   መጽሐፈ ምክር
ò አንደበቱን ከቧልት ከሐሜት ያየውንም ሚስጥር ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከኀልዮ ኃጥያት ያርቀዋል፡፡
   አረጋዊ መንፈሳዊ
ò ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ፡፡
  ማር ይስሐቅ
ò ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል     አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ጥበብ ይለየዋል፡፡                     
  አረጋዊ መንፈሳዊ

በምንማረው ትምህርት ፤ በምንመከረው ምክር ፤ በምናነበው መንፈሳዊ ጦማር እንድንጠቀም እግዚአብሔር ይርዳን

20 comments:

  1. Amen kale hiwot yasmaline.

    ReplyDelete
    Replies
    1. አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን

      Delete
  2. ዘመን ተሻጋሪዎቹ የአባቶቻችን የእምነት ፍሬዎች !ቃለህይወት ያሰማልን




    ReplyDelete
  3. አሜን!ቃለ ሔይወት የሰማልን።

    ReplyDelete
  4. Replies
    1. Amen Kalhiwot yasemalen!!!!

      Delete
    2. አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን::

      Delete
  5. Ye abew Bereket yiderbh kale hiwot yasemalin Amen

    ReplyDelete
  6. ራስህን በሀሰት አትውቀስ፡፡ራስህ መክሰስ ትህትና አይደለም፡፡ ታላቅ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስ ነው.
    kale hiwot yasemalin

    ReplyDelete
  7. Where have you been hidden for for long time D/n? Well come back with your sweet like honey "kale Egziabhere " . God bless you

    ReplyDelete
  8. endih yale bihil Abew tmhrt slemiset ketlbet. kalehiwot yasemaln. Amen!

    ReplyDelete
  9. kale hiwot yasemaln

    ReplyDelete
  10. amen egzeabher yeagolgelot zemenachu yarzem

    ReplyDelete
  11. kalehiwet yasemalen

    ReplyDelete
  12. kale hiwet yasemalen

    ReplyDelete
  13. kale hiwot yasemalen

    ReplyDelete
  14. kale hiwo yasemalen

    ReplyDelete