Monday, February 18, 2013

ጾመ ነነዌ


እግዚአብሔር ነብዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ምድር በኃጢአታቸው ምክንያት ሊያመጣው ካሰበው የእሳት ዝናም እንዲትርፉ ቢልከው እግዚአብሔርን ቸርነት ስለሚያውቀው ቸርነትህ ከልክላህ ሳታጠፋቸው ብትቀር እኔ የሐሰት ነቢይ እባል የለምን? ብሎ ሰግቶ ወደ ተርሴስ  ሃገር  ከነጋዴዎች ጋር ተሳፈረ።
          እግዚአብሔርም ታላቅ ማዕበልን አስነሳ በመርከቧ ያሉ ሰዎችም እርስ በራሳቸው ዕጣን ተጣጥለው በዮናስ ላይ ወደቀ። እርሱም ያደረገውን ሰለሚያውቅ ሌሎቹ በውሰጥ ያሉት እንዳይጣል ብዙ ጥረት ቢያደርጉም የግድ መጣል ስለ ነበረበት ወደ ባሕር ተጣለ።  እግዚአብሔርም ታላቅ ዓሣ አንበሪን አዘጋጅቶ በከርሠ ዓሣ አንበሪ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ቆይቶ  በሦስተኛው ቀን  በአንጻረ  ነነዌ  ተፍቶታል። በግድም ቢሆን ስለ ሚመጣባቸው መዓት አስተምሯል። ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 1 እና 2 ነብዩ  ዮናስ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አሕዛብ ሀገር የተላከ ነቢይ ነው።

ዮናስ ማለት ርግብ ማለት ነው። ርግብ የዋህ እንደሆነች እሱም የዋህ ነውና ይህ ቅጽል ተቀጽሎለታል። የርግብ የዋህነት እንደምን ነው ቢሉ በማየ አይኅ (በጥፋት ውሃ )ጊዜ በእባብ አፍ ውስጥ እንቁላል ጥላለች። ጌታም በወንጌልእንድ ርግብ የዋኃን ሁኑ” ብሎ ተናግሯል።   ማቴ 1016 ዮናስም እግዚአብሔር  የሰማይ እና  የምድር የቀላያት እና የአብርሕት ፈጣሪ መሆኑን እያወቀ እያስተማረ ከእርሱ ዓይን እይታ  ለመራቅ እግዚአብሔር በፈጠረው ባሕር ላይ በመርከብ ተሳፍሮ  ሊሸሽ መሞከሩ በራሱ የዋህ ያስብለዋል። በተጨማሪም አብረውት የነበሩ ነጋድያን ከየት ወገን እና ከየት እንደመጣ ሲጠይቁት የሚመልሰው መልስ በራሱ የዋህነቱን  ያሳያል የመጀመርያውዕብራዊ ነኝሲል መልሷል ዕብራዊ መሆን ሃይማኖት አዋቂ እና ሃይማኖተኛ  መሆንን ያሳያል። ሁለተኛው ደግሞ  “ባሕሩን እና የብሱን የፈጠረን አመልካለሁብሎ ባህር ፈጣሪ ዐይን እይታ ለመራቅ ወደ ተርሴስ ለመሄድ መሞከሩ  በእርግጥም የዋህ የሚያሰኘው ነው።
ሌላው ደግሞ ዮናስን ያስጨንቀው የነበረው የራሱ ቃል (ትንቢት) ተፈጻሚነት አለማግኘቱ እንጂ የነነዌ ሰዎች በእነርሱ ላይ ሊደርስ ከነበረው መዓት መዳን አለመዳናቸው  አልነበረም። የሚያስደንቀው ደግሞ በእግዚአብሔር ቸርነት የእርሱ ቃል (ትንቢት) ተፈጻሚነት እንደ ማይኖረው አውቆ ወደ ተላከበት ላለመሄድ አጥብቆ  መጠየቁ ነው። ዮና 42
የእግዚአብሔር ነቢይ ለራሱ ቃል ተጨንቆ እንዲህ ያለ የተማጽኖ  ቃል ቢያሰማ በእርግጥም ከየዋህነት እንጂ ሳያውቅ ቀርቶ አደለም።አቤቱ እለምንሃለሁ በሀገሬ ሳለሁ የተናገርኩት ይህ አልነበረም? አንተ   ይቅር ባይ ታጋሽ ምሕረትህም የበዛ ከክፉው ነገር የምተጸጸት አምላክ እንደሆንክ አውቄ ነበርና᎐᎐᎐ብሎ የእግዚአብሔር ቸርነት ማድረግ አሳዝኖት፣ የርሱ ታማኝነት የሚያሳጣ መስሎት አዘነ።
ዮናስ ያዘነው ሰብአ ነነዌ በመዳናቸው ሳይሆን የእርሱ ቃል በእግዚአብሔር መሸፈኑ ነው። ነገር ግን ይህ በራሱ የዮናስን የዋህነት ያሳያል ይኸውም ሰብዓ ነነዌ ገና የርሱን ቃል ሰምተው እንደዚያ ያለ ለውጥ ማምጣታቸው በራሱ የእርሱን ታማኝነት ያሳያል። ምክያቱም ገና አንድ ዐረፍተ  ነገር ተናግሮ እንዲያ ለመዳን መንቀሳቀሳቸው የቱን ያህል ቃሉን እነዳመኑትና እንደተቀበሉት  ያሳያል! ይህንንም አለማስተዋሉ የዋህነቱን ይመሰክራል።
እግዚአብሔርም የዋህነቱን ስለሚያውቅ ሲያባብለው እና በተለያየ ሁኔታ  እና ምሳሌ ሲያስተመረው እናያለን።በውኑ ትቆጣ ዘንድ ይገባሃልንእያለ ይናገረው ነበር ዮና 49 እሰከ መጨረሻ። በእውነት በፍጹም ክፋት አስቦት ቢሆን  ኖሮ ሲጀመር እግዚአብሔርም እንዲያስተምርለት አያዘውም ነበር። “᎐᎐᎐ በዓይኑ ትዕቢተኛ የሆነውን እና ልቡ የሚሳሳው ከእኔ ጋር አይተባበርምእንዲል          መዝ 100 5
ሌላው የነነዌ  ሰዎች በንስሓ  ሕይወት በመለወጥ እንደምሳሌ የሚጠቀሱ ናቸው። ይኸውም ገና በከተማዋ ገብቶበሦስት ቀን ወስጥ ትገለበጣለችስላለ ብቻ ሀገሩም አመነው አዋጅን አውጀው ፍጹም ጾምን ጾሙ፤ የእግዚአብሔርን መዓት በምሕረት መልሰዋል። የነነዌ ሰዎች ነቢዩ ዮናስ ገናትገለበጣለችስላለ ብቻ ሀገሬው ሙሉ ከንጉሥ እስከ ገረድ ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ሆነው ለለውጥ መነሳታቸው በራሱ ሙሉ በሙሉ የንስሓ  ሕይወታቸውን የሚያረጋግጥ ነው።
በአሁኑ ጊዜ መምህራን ሁሉ ትምህርተ ሃይማኖትን እያስተማሩ የንስሓ ሕይወትን እየሰበኩ ለውጡ ግን የትምህርቱን ያህል አለመሆኑ የሰሚውን ጉድለትና ደካማነት ያሳያል  “᎐᎐᎐ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሓደ አልጠቀማቸውምዕብ 42 እንዲል። ልብ እንበል! ነቢዩ ዮናስ ለሰብአ ነነዌ የተናገረው  “ በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለችየሚል አምስት ቃልን ብቻ  ነው በዚህች ቃል ብቻ ይህን የመሰለ ለውጥ ማምጣት መቻል በራሱ ፍጹም የእግዚአብሔርን ሥራ እንድናደንቅ ይረዳናል።
ስለ ነነዌ ሰዎች የንስሓ ሕይወት ጌታ ራሱ በወንጌሉ መስክሯል። ለሕዝቡም መፈራረጃ  አድርጓቸዋል። ሉቃ 1932 “᎐᎐᎐በዮናስ ስብከት ንስሓ ገብተዋልናእንዲል። በተጨማሪም  የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ይፈርዱበታ ይላል ማቴ 1241
ሌላው እግዚአብሔር መቼም ቢሆን ሰው የተመኘውን አያስቀርም። አዳም አምላክነትን ተመኘ ዘመኑ ሲፈጸም አምላክ ሰው  ሆኖ ተምኔቱን (ምኞቱን) ፈጽሞለታል። ዮናስም ምንም እንኳን በቀጥታ እንዲጠፉ ባይፈልግም ውሸታም እንዳይባል ስለሚፈልግ ቀድሞ በተናገረው ቃል መሠረት ትንቢቱ ተፈጽሟል።   ዮናስ በሦስት ቀን ውስጥ እንዳለ በሦስተኛው ትውልድ ተወግታ  ጠፍታለች።
የመጨረሻው ዮናስ ለክርስቶስ  ምሳሌው ሆኗል። ይኽውም በሉቃ 1130 “ ዮናስ ለነነዌ  ሰዎች  ምልክት እንደሆናቸው እንዲሁ ደግሞ የሰው ልጅ ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናልእንዲል። በጌታ ሞትም ምሳሌውሆኗልክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክትን ይሻል ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀን እና ሦስት ሌሊት እንደ ነበር እንዲሁ ሰው ልጅ በምድር ልብ ውስጥ ሦስት ቀን እና ሦስት ሌሊት ይኖራልእንዲል ማቴ 1239
ሰለዚህ እንዲህ ያሉትን ነገር እያሰቡ የነነዌን ሀገር ሰዎች ተግባር ማየት ከእነርሱም መማር ያስፈልጋል እግዚአብሔር ዕድሜ ለንስሐ ዘመን ለፍሥሃ ያድለን
ለንስሐ ሞት ያብቃን!!

22 comments:

  1. amen, kale hiwoten yasemalen

    ReplyDelete
  2. ቃለ ህይወት ያሰማልን። ለመሆኑ እኛ ኢትዮጵያውያን (ከአባቶቻችን ጀምሮ) በእግዚአብሔር ላይ ለፈጸምነው ወንጀል ሁሉ በጋራ ንስሐ የምንገባው መቼ ነው? እግዚአብሔር የሰጠንን የበኩርነት ፀጋ ሁሉ እንደ ኢሳው ለሆድ ስንል አላስልፈን የሰጠን፤ የተቀደሰውን ሁሉ ለውሻ የጣልን ከንቱዎቹ እኛ መቼ ነው እግዚአብሔር አምላክን በአንድ ላይ ሆነን ይቅርታ የምንጠይቀው? ሃገራችን ኢትዮጵያ በአመፀኝነታችንና በሃጢአታችን ብዛት ሳትጠፋ አምላክ ይቅርታ ያደርግልን ዘንድ የተዋህዶ አስተማሪዎች የሆናችሁ ሁሉ ይቅርታ እንጠይቅ ብላችሁ በውን እኛን መሃይምናንን ለቅርብ የንስሃ ቀን የምታዘጋጁን መቼ ነው?

    ReplyDelete
  3. thank you for your current information!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  4. what you have done is very appreciable so keep it up

    ReplyDelete
  5. Amen!!! Kale hiwot yasemalin! Betene behiwot yitebikilin!

    ReplyDelete
  6. Amen. Kale hiwot yasemalin. Egizabhare ragem edemana tena yesteline.

    ReplyDelete
  7. ቃለ ሄወት ያሰማልን ።ለኛም የሰማነውን አንድንተገብር ዓይ ነ ልቦናችንን ያብራልን።
    ለሕዝበ ክርስቴያን በሙሉ የበረከት ጾም እንዲሆንልን እመኛለሁ።

    ReplyDelete
  8. ከንጉሥ እስከ ገረድ do not use this word ገረድ hulachu bekrestose eyesus andnachu selemil kalu . eventhough nice and excellent sebeket

    ReplyDelete
  9. Kale hiwot yasemalin
    Dn. Melaku dehina aleh?
    Ke 4Killo jemiro ejig awkehalew
    Yihin ke ejachin wedko yeneberewin ye ilet migib (Sinkisarun)Alem mayet enditchil bemechalih fetari yimesgen.
    Melkam Subae

    ReplyDelete
  10. ፍሬንድ...ገረድ እኮ ስድብ አይደለም.....በዚህ አገባቡ ደግሞ ፍጥሞ ለስድብ አልተጠቀመበትም...አሽከር፣ ሎሌ፣ አገልጋይ፣ ደንገጡር እንደማት ነው.....

    ReplyDelete
  11. ቃለ ሕይወት ያሰማልን
    kindest regards
    Daniel from Maryland

    ReplyDelete
  12. ቃለ ሕይወት ያሰማልን
    ቃለ ሕይወት ያሰማልን
    ቃለ ሕይወት ያሰማልን።የአባቶቻችን ፀጋ እግዚአብሔር ይሰጠን

    AMEN..AMEN.AMEN


    ReplyDelete
  13. Kalehiwot yasemalen. Amen!!

    ReplyDelete
  14. ዲ/ን መላኩ እንዄን አደረሰሕ!!!
    አሜን!!!

    ReplyDelete
  15. Amen! Amen! Amen! Kale Hiwot Yasemalin!!

    ReplyDelete