Tuesday, August 7, 2018

ፍልሰታ ኪዳነ ምህረት


«ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ»
ቅዱስ ያሬድ
click here For PDF
ፆመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚታሰብበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ምእመናንን ከአካባቢያቸው ራቅ ብለው በተለያዩ ገዳማትና አድባራት በመሄድ አሊያም በአጥቢያቸው በመሰባሰብ እመቤታችን ለሐዋርያት በተለያዩ ጊዜያት ተገልጻ ሞትና ትንሣኤዋን የገለጸችበትን ሁኔታ ያስባሉ፡፡ ጌታም እናቱን መንበር አድርጎ ቀድሶ ማቁረቡን ይዘክራሉ በዚህ ወቅት በፆም በጸሎት ተወስነው የልጇን ቸርነት የድንግልን አማላጅነት ይማጸናሉ፡፡ ሁሉም እንደሚደረግላቸው ያምናሉ፡፡ የሱባኤው ወቅት ሲፈጸም «በእውነት ተነሥታለች» ብለው በደስታ የፆሙን ወቅት ይፈጽማሉ፡፡
 ሞትና ትንሣኤዋ እንዴት ነው ቢሉ፡- የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሞትና ትንሣኤ ነገረ ማርያም፣ ስንክሳር እና ተኣምረ ማርያም እንደሚያስረዱት፤ ጥር 21 ቀን ዐርፋለች፡፡ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን ታላቁ የቤተክርስቲያናችን አባት ቅዱስ ያሬድ «ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የሐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» በማለት ገልጾታል፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያት የእመቤታችንን የከበረ ሥጋዋን ገንዘውና ከፍነው ለማሳረፍ ወደ ጌቴሴማኒ መካነ ዕረፍት (የመቃብር ቦታ) ይዘው ሲሄዱ አይሁድ በቅንአት መንፈስ ተነሣሥተው «ቀድሞ ልጇን በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሣ፤ በዐርባኛው ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ እንደገናም ተመልሶ ይህን ዓለም ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ፡፡ አሁን ደግሞ እርሷንም እንደ ልጇ ተነሣች፣ ዐረገች እያሉ ሲያውኩን ሊኖሩ አይደለምን) ተሰብሰቡና ሥጋዋን በእሳት እናቃጥላት» ብለው ተማክረው መጡ፡፡ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ የከበረ ሥጋዋን የተሸከሙበትን አጎበር (የአልጋ ሸንኮር) በድፍረት ያዘ፡፡
የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁለት እጆቹን ቆረጣቸው፡፡ እጆቹ ተንጠልጥለው ከቆዩ በኋላ በእውነት የአምላክ እናት ናት በማለት ስለ አመነ እጆቹ ተመልሰው እንደነበሩ ሆነውለታል፡፡ ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የከበረ ሥጋ ከሐዋርያው ዮሐንስ ጋር ነጥቆ ወስዶ በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ ሐዋርያት ሲመጣ የእመቤታችንን የከበረ ሥጋ በገነት መኖሩን ነገራቸው፡፡ ሐዋርያትም የእመቤታችንን የከበረ ሥጋ አግኝተው ለመቅበር በነበራቸው ምኞትና ጉጉት ዮሐንስ አይቶ እኛ እንዴት ሳናይ እንቀራለን ብንጠየቅስ ምን እንመልሳለን በማለት በነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ጀምረው ሲጾሙና ሲጸልዩ ከሰነበቱ በኋላ 14 (በሁለተኛው ሱባኤ መጨረሻ) ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ የከበረ ሥጋ አምጥቶ ስለሰጣቸው በታላቅ ዝማሬ፣ በውዳሴ ወስደው ቀድሞ በተዘጋጀው መካነ ዕረፍት በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡
የእመቤታችን የቀብር ሥነ ሥርዐት በተፈጸመ ጊዜ 12 ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ አልነበረም፡፡ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ፣ እመቤታችን በተቀበረች በሦስተኛው ቀን እንደ ልጇ ትንሣኤ ተነሥታ ስታርግ ያገኛታል፡፡ ቀድሞ የልጅሽን አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ ብሎ ቢያዝን እመቤታችን ከእርሱ በቀር ሌሎች ሐዋርያት ትንሣኤዋን እንዳላዩ ነግራው ቅዱስ ቶማስን አጽናናችው፡፡ ሄዶም ለሐዋርያት የሆነውን ሁሉ እንዲነግራቸው አዝዛው ለምልክት ይሆነው ዘንድ የተገነዘችበትን ሰበኗን ሰጥታው ወደ ሰማይ ዐርጋለች፡፡
ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት የእመቤታችን ትንሣኤ አስቀድሞ በትንቢት መስታወትነት ታይቶት «ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅድስከ፤ አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት» (መዝ.1318)፡፡ ነቢዩ ዳዊት ይህን ቃለ ትንቢት አስቀድሞ ክርስቶስ እንደሚነሣ ከገለጸ በኋላ ቀጥሎ የመቅደሱ ታቦት እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም እንደምትነሣ ይናገራል (ማቴ535 ገላ 4 26 ዕብ 1222 ራዕ 312)፡፡
 ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ ቶማስም ሐዋርያት ወደ አሉበት ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ «የእመቤታችን ነገር እነዴት ሆነብሎ ቢጠይቃቸው፤ «እመቤታችንን እኮ ቀበርናት» ብለው ነገሩት፡፡ እርሱም ዐውቆ ምስጢሩን ደብቆ «አይደረግም ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንደምን ይሆናልአላቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ መጠራጠር ልማድህ ነው፡፡ ቀድሞ የጌታን ትንሣኤ ተጠራጠርክ አሁንም አታምንም ብሎ የእመቤታችን መካነ መቃብር ሊያሳዩት ይዘውት ሔዱ፡፡ መቃብሩን ቢከፍቱ የእመቤታችንን የከበረ ሥጋ አጡት፤ ደነገጡም፡፡
 በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቶማስ «አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችንስ ተነሥታ ዐርጋለች» ብሎ የሆነውን ሁሉ ተረከላቸው፡፡ ከዚያም ምልክት እንዲሆን የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው፡፡ እነርሱም ማረጓን አምነው ሰበኗን ለበረከት ከተከፋፈሉ በኋላ ወደየአህጉረ ስብከታቸው ሄዱ፡፡ በየሀገረ ስበከታቸውም ሕሙማንን ሲፈውሱበትና ገቢረ ተአምር ሲያደርጉበት ኖረዋል፡፡ በዓመቱ ትንሣኤሽን ቶማስ አይቶ እንዴት ይቅርብን ብለው ነሐሴ አንድ ቀን ጀምሮ ሱባኤ ገቡ፡፡
 በሱባኤው መጨረሻ ነሐሴ 16 ቀን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የለመኑትን ልመና ተቀብሎ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቀ (ረዳት) ቄስ) ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ (ዋና) ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ አቁርቦአቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ እመቤታችንን ሐዋርያት በግልጽ ትንሣኤዋን ዕርገቷን እያዩዋት ከጌታችን ጋር በክብር በይባቤና በመዝሙር ወደ ሰማይ ዐርጋለች፡፡
ቅዱስ ያሬድ በመዝሙሩ «እመቤታችን ድንግል ማርያም ከምድር ወደ ሰማይ ዐረገች በሰማይም ከልጇ ጋር በአብና በመንፈስ ቅዱስ ቀኝ ተቀመጠች»፡፡ የእመቤታችን ትንሣኤ፣ ዕርገት ልዩ የሆነበት ምስጢር በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መሠረት ትንሣኤ ጊዜያዊና ዘለዓለማዊ በመባል ይታወቃል፡፡ ጊዜያዊ ትንሣኤ የሚባለው የእግዚአብሔር ከሃሊነት የሚገለጽበት ተኣምራዊ ሥራ ሆኖ በተወሰኑ ሰዎች ላይ ይፈጸምና ዳግም ሞትን የሚያስከትል ነው፡፡ ለምሳሌ ኤልያስ ያስነሣውን ወልደ መበለት (1 ነገ 178-24) ዐጽመ ኤልሳዕ ያስነሣውን ሰው (2ኛነገ 132021) ትንሣኤ ወለተ ኢያኢሮስን (ማቴ 9 8-26) በዕለተ ስቅለት ከመቃብር ወጥተው በቅድስት ከተማ የታዩ ሙታን (ማቴ 2752-53) በቅዱስ ጴጥሮስ ጸሎትና ምልጃ የተነሣች ጣቢታን (ሐዋ 936-41) እንዲሁም ትንሣኤ አልዓዛርን መጥቀስ ይቻላል፡፡
 አልዓዛር ከሞተ በኋላ በአራት ቀን እንደተነሣ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጽፏል፡፡ «በታላቅ ድምፅ አልዓዛር ሆይ ወደ ውጭ ብሎ ጮኸ፡፡ የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደተገነዙ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ እንደተጠመጠመ ነበር፡፡ ኢየሱስም ፍቱትና ይሂድ ተውት አላቸው(ዮሐ 1143-44)፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያነሣውም ለማየት በመቃብሩ ዙሪያ የነበሩ አይሁድ ከሞተ በኋላ በአራት ቀን መነሣቱን ተመልክተው አደነቁ የአልዓዛር እኅቶችም ተደሰቱ፡፡ አልዓዛር ግን ለጊዜው ቢነሣም ቆይቶ ተመልሶ ዐርፏል ወደፊት ትንሣኤ ዘጉባኤ ይጠብቀዋል፡፡
የቅድስት ድንግል ማርያም ትንሣኤ የክብርና የሕይወት ትንሣኤ ሲሆን ሁለተኛ ሞትን አያስከትልም ትንሣኤ ዘጉባኤንም አይጠብቅም፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤያችን በኩር ሆኖ በሞተ በሦስተኛው ቀን ተነሥቷል፡፡ እናቱ እመቤታችንም በልጇ ሥልጣን፤ እንደ ልጇ ትንሣኤ በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ትንሣኤ ዘጉባኤን ሳትጠብቅ በክብር ዐርጋለች፡፡ እንደዚህ ያለውን ትንሣኤ ከእርሷ በቀር ሌሎች ቅዱሳን ወይም ነቢያትና ሐዋርያት አላገኙትም በዚህም ሁኔታ የቅድስት ድንግል ማርያም ትንሣኤ ከማናቸውም ትንሣኤ ልዩ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ይህም ትንሣኤ ዘለዓለማዊ የሆነ ከዳግም ሞተ ሥጋ ነጻ የሆነ ትንሣኤ ነው፡፡
 ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ከመቃብር መነሣት ነሐሴ 16 ቀን የሚነበበው መጽሐፈ ስንክሳር እንደሚያስረዳን አባቷ ዳዊት በገናውን እየደረደረ ጸሐፊው የነበረው ዕዝራም መሰንቆውን ይዞ ቅዱሳን መላእክት ነቢያትና ጻድቃን እያመሰገኗት በብሩህ ደመና ወደ ሰማይ ዐረገች ከዚያም በክብር ተቀመጠች፡፡ በዚያም ስፍራ ሁለተኛ ሞት ወይም ሐዘን ጩኸትና ስቃይ የለም የቀደመው ሥርዐት አልፎአልና (ራዕ 214-5)፡፡
የእመቤታችን ዕርገትም በመጽሐፍ ቅዱስ ከተገለጸው ከእነ ሄኖክና ኤልያስ ዕርገት የተለየ ነው፡፡ ሄኖክ ወደ ሰማይ ያረገው በምድር ሳለ እግዚአብሔርን በእምነቱና በመልካም ሥራው ስለአስደስተና በሥራውም ቅዱስ ሆኖ ስለተገኘ ሞትን እንዳያይ ዐረገ፡፡ ወደፊት ገና ሞት ይጠብቀዋል ሞቶም ትንሣኤ ዘጉባኤ ያስፈልገዋል፡፡ «ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም» (ዕብ 115)፡፡
 ነቢዩ ኤልያስም በእሳት ሠረገላ ተነጥቋል «እነሆ የእሳት ሠረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው፤ ኤልያስም በአውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ» (2 ነገ 210)፡፡ ነቢዩ በእሳት ሠረገላም ቢነጠቅም ወደፊት ሞት ይጠብቀዋል፤ ትንሣኤ ዘጉባኤም ያስፈልገዋል፡፡
ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድም በድርሰቱ ስለ ዕርገትዋ ጽፏል፡፡ በቃልዋ የታመነች በሥራዋም የተወደደች ቅድስት ድንግል ማርያምን መላእክት እያመሰገኗትና በመንፈሳዊ ደስታ እያጀቧት ወደ ሰማይ አሳረጓት ሲል በዘመረው መዝሙር አስረድቶናል፡፡
የእመቤታችን አማላጅነት የትንሣኤያችን በኲር የሆነው የአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነቱ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን፡

25 comments:

  1. Amen Amen Amen! Kale hiwot yasemalin! Egziabher yistilin!

    ReplyDelete
  2. Kale Hiwot yasemalen,Bealun ye selam yaderglen!!!

    ReplyDelete
  3. +++ አሜን የእመቤታችን አማላጅነት; የትንሣኤያችን በኲር የሆነው የአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነቱ ከሁላችን ጋር ይሁን+++ ቃለ ህይወትን ያሰማልን +++

    ReplyDelete
  4. Kale Hiwot Yasemalin Deacon!

    ReplyDelete
  5. amen kale hiwot yasemalin

    ReplyDelete
  6. Kale Hiwot Yasemalen Dn Melaku ! Well written !

    ReplyDelete
  7. kale hiwot yasemalen!!!

    ReplyDelete
  8. WENDIMACHIN KALE HIYWOT YASEMALIN YAGELIGLOT ZEMENIHIN YARZIMILIN

    ReplyDelete
  9. kale hiwot yasemalen!!!
    08/06/2014 @11:11AM

    ReplyDelete
  10. Amine Kale Hiwet yasemalene !

    ReplyDelete
  11. Kalehiwot yasemalin

    ReplyDelete
  12. kalehiwot yasemalin

    ReplyDelete
  13. Amen kalehiwot yasemalen!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  14. +++ አሜን የእመቤታችን አማላጅነት; የትንሣኤያችን በኲር የሆነው የአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነቱ ከሁላችን ጋር ይሁን+++ ቃለ ህይወትን ያሰማልን +++

    ReplyDelete
  15. can anybody tell me why the Apostles didn't write all this story of Mary in the Bible? Because as you told us it is a very interesting story.

    ReplyDelete
  16. ስለ እመቤታችን ቅድስት ማርያም ብዕት ገድል እንደዚህ ማሳወቃቹህ በጣም ኣመሰግናሉ፡፡

    ReplyDelete
  17. ከጥር እስከ ነሀሴ የት ነበር የቆየችው? ማለት ማረግዋን ያውቁ ነበር ሀዋርያት ወይስ ጠፍታባቸው ነው? ጥር አርፋ አገች ከዛ ተመልሳ ተቀበረች ከዛ ተነስታ አረገች ነው? እፀረነቱ ስር በሂዎት ነበር የቆየችው ? የውሀንስም አርጎ ነበር?

    ReplyDelete
  18. ከጥር እስከ ነሀሴ የት ነበር የቆየችው? ማለት ማረግዋን ያውቁ ነበር ሀዋርያት ወይስ ጠፍታባቸው ነው? ጥር አርፋ አገች ከዛ ተመልሳ ተቀበረች ከዛ ተነስታ አረገች ነው? እፀረነቱ ስር በሂዎት ነበር የቆየችው ? የውሀንስም አርጎ ነበር?

    ReplyDelete
  19. ቃለሕይወት ያሰማልን



    ReplyDelete
  20. «ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የሐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» በማለት ገልጾታል፡፡
    የሐጽብ-የዓፅብ ና የሐፅብ ይለያያሉ፡፡
    ዕጹብ- ገራሚ ማለት ሲሆን
    ሐጽበ- ዓጠበ አነጻ ቀደሰ ማለት ነው፡፡
    መአስተምህሮቶ እያቀያየሩ መጠቀሞ ልክ አይደለም፡፡ ግእዝን ለማያውቁ ሰዎች ያደናግራል ያሳስታል፡፡

    ReplyDelete
  21. በምልጀዋ የመትልያን ሁል ጊዜ ለትውልድ ኹሉ የተመሰገነች ትኹን። አሜን።

    ReplyDelete