Tuesday, March 11, 2014

መፃጉዕ (የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት)

መድኃኔዓለም በቤተ ሳይዳ መጻጉዕን እንደፈወሰው

 የዮሐንስ ወንጌል ም 5 ቁ 1
ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት።
በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና ዕውሮች አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር።
ቤተ ሳይዳ ዛሬ
አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር።
በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤
ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ። ልትድን ትወዳለህን? አለው።
ድውዩም። ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት።
ኢየሱስ፦ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው።
ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ።
ያም ቀን ሰንበት ነበረ። ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውን ሰው። ሰንበት ነው አልጋህንም ልትሸከም አልተፈቀደልህም አሉት።
እርሱ ግን፦ ያዳነኝ ያ ሰው። አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ ብሎ መለሰላቸው።
እርሱም፦ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ያለህ ሰው ማን ነው? ብለው ጠየቁት።
ዳሩ ግን በዚያ ስፍራ ሕዝብ ስለ ነበሩ ኢየሱስ ፈቀቅ ብሎ ነበርና የተፈወሰው ሰው ማን እንደ ሆነ አላወቀም።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመቅደስ አገኘውና። እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ አለው።
ሰውዬው ሄዶ ያዳነው ኢየሱስ እንደ ሆነ ለአይሁድ ነገረ።

ምንባባት መልዕክታት 

(ገላ. 5÷1-ፍጻሜ ምዕ.) እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ እንደገናም በባርነት ቀንበር አትኑሩ፡፡ እነሆ÷እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ፤ብትገዘሩም በክርስቶስ ዘንድ ምንም አይጠቅማችሁም፡፡” ...... 
(ያዕ.5÷14- ፍጻሜ ምዕ.) ከእናንተ የታመመ ሰው ቢኖር በቤተ ክርስቲያን ያሉ ቀሳውስትን ይጥራና ይጸልዩለት፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጸለየበትንም ዘይት ይቅቡት፡፡ ....... 

ግብረ ሐዋርያት 

(የሐዋ.3÷1-11) ጴጥሮስና ዮሐንስም በዘጠኝ ሰዓት ለጸሎት በአንድነት ወደ ቤተ መቅደስ ወጡ፡፡ ከእናቱ ማኅፀንም ጀምሮ እግሩ ሽባ ሆኖ የተወለደ አንድ ሰው ነበር፤ ወደ መቅደስም ከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ ሁል ጊዜ እየተሸከሙ መልካም በሚልዋት በመቅደስ ደጃፍ ያስቀምጡት ነበር፡፡(ተጨማሪ ያንብቡ) 

ምስባክ 
(መዝ.40÷3)እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ፡፡ ወይመይጥ ሎቱ ኩሎ ምስካቢ እምደዌሁ አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ
ትርጉም፦ እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውንም ሁሉ ከበሽታው የተነሣ ይለውጥለታል፡፡ 


ወንጌል 
(
ዮሐ. 5÷1-24) ከዚህም በኋላ በአይሁድ በዓል እንዲህ ሆነ፤ ጌታችን ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡ በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ መጠመቂያ ነበረች፤ ስምዋንም በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ይሉአታል፤ አምስት እርከኖችም ነበሩአት፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ) 

ቅዳሴ: - ቅዳሴ ዘእግዚእነ  

19 comments:

  1. Kale Hiwot Yasemalin Be'edme Be'tsega yitebikilin!

    ReplyDelete
  2. Kezih Tomar bizu temirebetaleh
    Eziabher kalehiwot yasemain
    Kekifu neger hulu yitebikilin
    Rejim edmie yistilin

    ReplyDelete
  3. ብዙ ጊዜ ከሚታዩት ስህተቶች መካከል «ቤተ ሳይዳ» እና «ቤተ ስዳ» የሚባሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቦታዎችን አቀላቅሎና እርስ በእርስ አጣርሶ የመጻፍ ችግር ነው። የሚገርመው ይህ ስህተት የአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሳይቀር ተጽፎ መገኘቱ ነው። እነዚህን ጥቅሶች ይመልከቱ።
    ዮሐ 5፥2
    «በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት»
    ይህችኛዋ «ቤተ ሳይዳ» የምትገኘው በኢየሩሳሌም ከተማ በበጎች በር አጠገብ ነው። ሌላኛዋን ደግሞ፣
    ዮሐ 12፥21
    «እነርሱም ከገሊላ ቤተ ሳይዳ ወደሚሆን ወደ ፊልጶስ መጥተው። ጌታ ሆይ፥ ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን ብለው ለመኑት»
    ይህችኛዋ «ቤተ ሳይዳ» ደግሞ የምትገኘው በሰሜናዊቷ የእስራኤል አውራጃ በገሊላ ነው። በሌላ ቦታም ከገሊላ ባህር ማዶ የምትገኝ መሆኗን የሚያጠናክር ጽሁፍ እንዲህ ተጽፎ እናገኛለን።
    ማር 6፥45
    «ወዲያውም ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ ደቀ መዛሙርቱ በታንኳ ገብተው ወደ ማዶ ወደ ቤተ ሳይዳ እንዲቀድሙት ግድ አላቸው»
    እንግዲህ የምንረዳው ነገር ሁለቱም ቦታዎች በተለያየ ቦታ ተራርቀው የሚገኙ መሆናቸውን ነው። ታዲያ የተለያዩ ቦታዎች መሆናቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ካረጋገጠ አንድ ዓይነት ስም የያዙት በስመ ሞክሼነት ነው ወይስ በስህተት ብለን ልንጠይቅ የተገባ ነው።
    አስረጂያችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ ነው። በጥንቱ የኢየሩሳሌም ከተማ አጥር ክልል ውስጥ ከጲላጦስ አደባባይ (ወደ በጎች በር ወይም የእስጢፋኖስ በር ወይም የአንበሶች በር) ተብሎ በሚጠራው መንገድ ላይ ሰሜናዊ አቅጣጫ ላይ የሚገኘው የውሃ መጠመቂያ «ቤተ ስዳ» ተብሎ ይጠራል። በእብራይስጥም (בית חסד )ቤት ስዳ ይባላል። የእብራይስጥ ትርጉሙም «ቤት» በቁሙ የአማርኛው ቃል «ቤት» ማለት ሲሆን «ስዳ» ማለት ደግሞ «ጸጋ» ወይም «ምህረት» ማለት ነው። በአንድነት ሲጠራ «ቤተ ስዳ» ማለት የጸጋ(የምህረት) ቤት ማለት ይሆናል። እንግሊዝኛው የኪንግድ ጀምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን በትክክል አስቀምጦት ይገኛል።
    (John 5፣2) Now there is at Jerusalem by the sheep market a pool, which is called in the Hebrew tongue Bethesda, having five porches
    ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለችው የበጎች መጠመቂያና የ38 ዓመቱ መጻጉዕ የተፈወሰባት ሥፍራ የምትጠራው «ቤተ ሳይዳ» ተብላ ሳይሆን «ቤተ ስዳ» ነው። እንደስሟ ትርጓሜ ቤተ ስዳ የተባለችበትም ምክንያት የሰሎሞን ቤተ መቅደስ አጠገቧ የሚገኝ ሲሆን ለቤተመቅደሱ መስዋእት የሚሆኑ በጎች ሁሉ በዚህ መጠመቂያ ሳይጠመቁ ወደ መስዋእቱ እርድ ቦታ አይቀርቡም ነበር። እንዲህ ተብሎ የለ!!
    «አሮንንም አለው። ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ከመንጋው እምቦሳውን፥ ስለሚቃጠልም መሥዋዕት አውራውን በግ ነውር የሌለባቸውን ወስደህ በእግዚአብሔር ፊት አቅርባቸው» ዘሌ 9፣2
    እነዚህ በጎችና የበጎች መጠመቂያ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ናቸው። በክርስቶስ ንጽሐ ባህሪው፣ የበጎቹ በመጠመቂያው ንጹህ ሆኖ መገኘት ሲሆን ንጹህ ከሆኑ በኋላ ለመስዋእት ቀርበው ኃጢአትን ማስወገድ መቻላቸው ደግሞ የእግዚአብሔር በግ የሆነው ክርስቶስም የዓለሙን ሁሉ ኃጢአት የሚያስወግድ ሆኖ መገኘቱን ያመለክታል።
    ዮሐ 1፥29
    በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ» እንዳለው።
    ስለዚህ ይህችን «የጸጋ ወይም የምህረት ቤት «ቤተ ስዳ»ን ወደ «ቤተ ሳይዳ» መቀየር መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ምስጢርና ትርጉም የሚያፋልስ ይሆናል።
    እስከዚህ ስለ «ቤተ ስዳ» ይህንን ካልን «ቤተ ሳይዳ» ታዲያ ማናት? የሚለውን በአጭሩ ማየት ተገቢ ይሆናል።
    ቤተ ሳይዳ በገሊላ ሐይቅ ዳርቻ ምእራባዊ ሰሜን አቅጫጫ የምትገኝ ከተማ ነበረች። ቤተ ሳይዳ ማለት በእብራይስጥ ( בית צידה)«የዓሳ ቤት» ማለት ነው። ይህች ከተማ የዓሳ ቤት የተባለችውም ከተማዋ እንደኢትዮጵያዋ የጣና ሃይቅ ስር የባህር ዳር ከተማ ዓይነት ከገሊላ ባህር ስር የምትገኝ ስለሆነና ዓሳ የሚያሰግሩ፣ የሚነግዱባት ስለሆነች ነበር። በዚህ በደራ ንግዷ የተነሳ ከተማዋ የሚነገራትን ለመስማት ባለመቻሏ ዛሬ የዚህች ከተማ ቅሪት ያለው ፍርስራሽ ብቻ ነው። በእርግጥ ፍርስራሿ ተቆልሎ ሲታይ ትልቅ ከተማ እንደነበረች ማረጋገጥ ይቻላል። ከእህቷ ከኮራዚን ጋር አብረው የጠፉና በአጠገባቸው የሚያልፉ ሁሉ የሚያፏጭባቸው የታሪክ ሀገር ሆነው ቀርተዋል።
    ማቴ 11፣21«ወዮልሽ ኮራዚ፤ ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ፤ በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው አመድም ነስንሰው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበርና» ተብሎ የተተነበየባቸው መሆናቸውን ቅዱሱ መጽሐፍ ይነግረናል።
    ስለዚህ ባለኝ መረዳት «ቤተ ስዳ» እና «ሳይዳ» ን ማቀላቀሉ ሊስተካከል ይገባል እላለሁ።
    http://masho.ourtoolbar.com

    ReplyDelete
    Replies
    1. «ቤተ ስዳ» እና «ቤተ ሳይዳ» ልዩነት ላስተማርከን ቃለ ህይወት ያሰማልን እግዚያብሔር ይባርክህ

      Delete
    2. Thanks. Kale hiwot yasemalign

      Delete
  4. kalehiwot yasemalen.

    ReplyDelete
  5. Kale hewot yasemalin!

    ReplyDelete
  6. ቃለ ህይወት ያሰማልን

    ReplyDelete
  7. kalhiwot yasemalen astyayet yestehewm egzeabher yestlen endezeh eytememarn emnetachnen enatenker

    ReplyDelete
  8. ቃለ ህይወትን ያሰማልን!!! በእለተ መጻጉ የሚዘመረው መዝሙር ቢኖር ደሞ ይበልጥ መልካም ነበር!!!

    ReplyDelete
  9. ቤተ ስዳ እና ቤተ ሳይዳን ላሳወከን ቃለ ሕይወት ያሰማልን ተባረክ!!!

    ReplyDelete
  10. ቤተ ስዳ እና ቤተ ሳይዳን ላሳወከን ቃለ ሕይወት ያሰማልን ተባረክ!!!

    ReplyDelete
  11. ለጀማሪውም ለጨራሹም ቃለ ሕይወት ያሰማልን።

    ReplyDelete
  12. Wondimachin Dn, Engineer Melaku kale hiwot yasemalin. Keep on teaching us up to Tinsae. I also thank our bro/Sister who told us the differecnes b/n Bete Sayda and Bete Sada. But still I would like the writer to put his inputs on the explanation given.

    ReplyDelete
  13. እንካን አደረሰን

    ReplyDelete
  14. Kale hiwot yasemalin! Beselam betena yitebikilin!

    ReplyDelete
  15. Kale hiwoten yasemalen.

    ReplyDelete
  16. ዲ/ን ቃለ ሔይወት ያሰማልን:: ሥራ እንደሜበዛብህ ይነገራል : ሆኖም እባክህ ትምህርትህ በተለይ ባሕር ማዶ ላለን ወገኖችህ በጣም ጠቃሜ ሰለሆነ ካለህ ስዓት እያብቃቃህ በርታልን::

    ReplyDelete