Sunday, February 12, 2012

ዐቢይ ጾም


በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ባሕልና ትውፊት  እና ሥርዓት መሠረት በዘንድሮው ዓመት በመጪው ሰኞ የካቲት 12 2004 ( 20 ፌብርዋሪ 2012 ) የሚጀመረው የጾም ወራት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱና ዋነኛው፣ ጌታ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው፡፡ ምእመናን ጌታቸው ያደረገውን ምሳሌ ተከትለው ይጾሙታል፡፡

   ይህ ታላቅ የሆነው የጾማችን ወራት በተለያየ ስያሜ  ይጠራል፡፡
1. ዐቢይ ጾም ይባላል፡፡

ሌሎች አጽዋማት ከቅዱሳን አበው የወረስናቸው የኑሮአቸው ፍሬዎች (ዕብ.13፤7) ሲሆኑ ይኼኛው ግን በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተመሠረተ በመሆኑ ዐቢይ (ታላቅ) ይባላል፡፡ የጌታ ጾም ስለሆነ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች (አርእስተ ኃጣውእ) ድል የተነሡበት፣ ድል የሚነሡበት ጾም ስለሆነም ዐቢይ ጾም ይባላል፡፡


2. ጾመ ሁዳዴ ይባላል፡፡

ሁዳድ ማለት የመንግሥት መሬት፣ የመንግሥት ርስት ማለት ነው፡፡ የመንግሥት ሁዳድ በሚታረስበት ጊዜ፣ አዝመራው በሚሰበሰብበት ጊዜ ልጅ ዐዋቂ ሳይባል የመንግሥቱ ዜጋ ሁሉ ለሥራ ታጥቆ እንደሚነሣ ይህንንም የጌታ ጾም የጌታ ወይም የጌታ ሁዳድ የክርስቶስ ዜጎች የሆኑ ምእመናን ሁሉ ይጾሙታልና ጾመ ሁዳዴ ይባላል፡፡

3. የካሣ ጾም ይባላል፡፡

አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን ከገነት የተባረሩት ለውርደት ሞት$ ለሲዖል ባርነት የበቁት በመብል ምክንያት ነበር፡፡ በሆዳምነቱ የወደቀውን የሰው ልጅ በፈቃዱ በጾመው ጾም ካሠው$ እንዲሁም አዳም ከገነት ሲባረር ረሃበ ጸጋ (መንፈሳዊ ረሃብ) ደርሶበት ነበርና ረሃቡን በረሃብ ካሠለት፡፡ የኛን ረሃብ እርሱ ተራበ፡፡


4. የድል ጾም ይባላል፡፡

ጌታችን ተጠምቆ ዕለቱን ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ በመሔድ ከሰው ተለይቶ አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት በመጾም አዳምና ሔዋንን በመብል የረታቸውን ዲያብሎስን እርሱ ድል አደረገላቸው፡፡ ዲያብሎስን ድል ያደርግ ዘንድ ከዚህ ዓለም ርቆ ወደ ገዳም መሄዱ አዳም ከዚህ ዓለም ርቃ በምትገኘው ገነት ድል ሆኖ ነበርና እርሱም ዲያቢሎስን በገዳም$ በዚህ ዓለም ርቆ ድል አደረገልን ለእኛም ፈቃደ ሥጋችንን የምናሸንፍበተ ኃይል ሰጠን፡፡ ይህ ጾም ጠላት ዲያቢሎስ የተሸፈነበት ነው፡፡


5. የመሸጋገሪያ ጾም ይባላል፡፡

ሊቀ ነቢያት ሙሴ ሕዝቡን ከሕገ ልቡና ወደ ሕገ ኣሪት ሲያሸጋግር አርባ መዓልትና ሌሊት በደብረ ሲና እንደ ጾመው ሁሉ ጌታችንም እኛን ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል ሲያሸጋግረን አርባ መዓልትና ሌሊት ጾመ፡፡ ስለዚህም የመሸጋገሪያ ጾም እንለዋለን፡፡


6. ጾመ አስተምህሮ ይባላል፡፡

ሁሉን ነገር በቅጽበትና ያለ ድካም ማድረግ የሚችለው አምላክ እኛን ልጆቹን ያስተምረን ዘንድ ራሱን ዝቅ አደረገ፡፡ መልካም መምህር ተማሪዎቹ ይገባቸው ዘንድ ዝቅ ብሎ በነርሱ ቋንቋ እየተናገረ በሚችሉት እየመሰለ እንዲያስረዳ ጌታችንም እኛን ወደርሱ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እርሱ ወደ እኛ መጣ፡፡ ረሃባችንን ተራበ ፤ ድካማችንን ደከመ ፤ ፈተናችንን ተፈተነ ለእኛም አርአያ ሆኖ ትሕትናን ፤ ትዕግሥትንና ፈተናን በጾም ማሸነፍን አስተማረን፡፡


7. የቀድሶተ ገዳም ጾም ይባላል፡፡

እነ መጥምቁ ዮሐንስ እነ ነቢዩ ኤልያስ የኖሩትን የብሕትውና ኑሮ ጌታ ባርኮ ሰጠን፡፡ ከከተማ ወጥቶ ከሰው ርቆ በበረሃ ከአራዊት ጋር እየኖረ በዲያብሎስ ተፈትኖ ድል አደረገ፡፡ ዛሬም ልጆቹ በየገዳማቱ ድምፀ አራዊትን ግርማ ሌሊትን ተግሠው ዓለምን ንቀው ፤ ከሰው ርቀው በጾም በጸሎት ከአጋንንት ጋር ይታገላሉ$ ድልም ያደርጋሉ፡፡


8. የመዘጋጃ ጾም ይባላል፡፡

ለእሥራኤላውያን ስለ በዓለ ፋሲካ አከባበር ሲነገራቸው የፋሲካውን በግ ሥጋ ከመራራ ቅጠል ጋር እንዲበሉት ታዘው ነበር (ዘጸ.12፤18)፡፡ ይኽም መራራ ቅጠል በግብፅ ይኖሩት የነበረውን የመከራ ኑሮ የሚያሳስባችውና ደግም ወደ ግብፅ (ምድረ ፋይድ) እንዳይመለሱ ከኃጢአተ ይርቁ ዘንድ የሚያስተምራቸው ነበር፡፡ የፋሲካው በግ ደግሞ እግዚአብሔር በፍቅሩ የሰጣቸውን ነፃነት ያሳስባቸዋል፡፡

ዛሬም በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከበዓለ ትንሣኤው በፊት የጾም ወራት ያስቀደምነው ለዚህ ነው፡፡ ከመብል ስንከለከል ለአዳምና ሔዋን የተሰጠውን ሕግ እናስባለን$ ረሃብ ሲሰማን በሰው ልጅ ላይ ደርሶ የነበረው የጸጋ ረሃብ$ የመንፈስ ረሃብ ይታወሰናል$ ስንደክም ስንጐሰቁል በአዳምና ሔዋን የደረሰው የመንፈስ ጉስቁልና$ የበደልን የዕዳ ቀንበር ተሸክመው የደረሰባቸው ድካም ይታሰበናል፡፡ እኛም በነርሱ የደረሰችው ሞት በእኛ እንዳትደርስ ዳግም ወደ ኃጢአት እንዳንመለስ ይመክረናል ያሳስበናል፡፡


በጾሙም መጨረሻ የሐዲስ ኪዳንን በግ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋና ደም እንቀበላለን፡፡ ያን ጊዜም ሞትን ካሸነፈው አምላክ ጋር አንድ እንሆናለን (ዮሐ.6፤55-58)፡፡ ሞታችን በሞቱ እንዳለፈ እናስባለን (1ቆሮ.11፤26)፡፡ በመሆኑም ይህ ወቅት በዓለ ትንሣኤ- የሐዲስ ኪዳን ፋሲካን ለማክበር$ ሥጋ ወደሙን ለመቀበል ራሳችንን የምናዘጋጅበት የምንፈትንበት ነው (1ቆሮ.11፤27)፡፡


9. የሥራ መጀመሪያ ጾም ነው፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማስተማር ሥራውን ከመጀመሩ$ የመንግሥተ ሰማያትን አንቀጽ ከማስተማሩ በፊት በገዳመ ቆሮንቶስ አርባ መዓልትና ሌሊት ጾመ፡፡ ይህም ለእኛ የማንኛውም ነገር መጀመሪያው ጾም መሆኑን ሲያሰተምረን ነው፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያት ጾምን የሥራቸው መጀመሪያ ያደረጉት፡፡


እንዲሁም ይህ የጾም ወቅት፡-

የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡ ተኩላዎች እንድንጠነቀቅ ያስተምረናል፡፡ ጠላት ዳያብሎስ ጌታችንን ሲፈትን ከመጽሐፍ ቅዱሰ እየጠቀሰ ነበር (መዝ 2ዐ፤11)፡፡ የእግዚአብሔርን ስም የጠራ፣ ጥቅስ የጠቀሰ ሁሉ መንፈሳዊ ሰው ፤ እውነተኛ ክርስቲያን ሊባል አይችልም፡፡ መጥቀስማ ዲያብሎስም ይጠቅሳል ሕይወቱን አይኖረውም እንጂ፡፡


እንዲሁም በዚህ የጾም ሰሞን ጠላታችን ዲያብሎስ ያዘጋጀልንን ወጥመድ አስበን ለገድል የምንዘጋጅበትም ነው፡፡ ጌታን ወደ መቅደስ ጫፍ አውጥቶ ወደ ታች ተወርወር እንዳለው ሁሉ እኛንም በትዕቢትና በከንቱ ውዳሴ ወደ ላይ አውጥቶ በኃጢአትና በውርደት በኃፍረትና ከመንፈስ በማራቆት ሊወረውረን ይሻል፡፡


ስለዚህ ትሕትናን በምታለብስ ጾም ድል እንንሣው፡፡

እንግዲህ ዐቢይ ጾም ማለት፡-
·        ጌታ ስለኛ ባየው መከራ የምናዝንበት፣

·        በሰጠን ኃይል ከሰይጣንና ከፈቃደ ሥጋ የምንዋጋበት፣

·        በበደልነው ተገብቶ የካሠልንን እያሰብን ዳግም ወደ ኃጢአት ላንመለስ ቃል የምንገባበት ፤
·        አርአያ ሆኖ ከሠራልን ሥርዓት፣ ከኖረልን ሕይወት የምንማርበት፣

·        ራሳችንን ለፋሲካው በግ ለሥጋ ወደሙ የምናዘጋጅበት ሰሞን ነው፡፡


በመሆኑም በሰላም፣ በፍቅር፣ በትሕትና ጾመን ለበዓለ ትንሣኤው በሰላም እንድንደርስ  ጾመን ለማበርከት እንዲያበቃን እግዚአብሔር በቸርነቱ ይጠብቀን አሜን፡፡
                                       ከኢሚሬትስ -ዱባይ


31 comments:

  1. kale hewote yasemalene wondemachen!!!

    ReplyDelete
  2. kale hewate yasemalen wondemachen!!!

    ReplyDelete
  3. kale hewat yasemalen wondemachen!!!

    ReplyDelete
  4. kale hewat yasemalen wondemachen!!!

    ReplyDelete
  5. kale hewat yasemalene wondemachen!!!

    ReplyDelete
  6. selame lante wendemachen ejeg betame enamesegenalen endezeh tafache yehonu kalatochen azegajetehe bemakerebeh enamesegenale!MT

    ReplyDelete
  7. እናመሰግላለን መላክ እ /ር ይስጥልን

    ReplyDelete
  8. amen amen amen kale hiewot yasemalin

    ReplyDelete
  9. wendmachen melaku enamesgenalen !!

    ReplyDelete
  10. egzabher edemihen yebarekew le hulachen ye selam ye feker ye tehethna tsome yaderegew amen!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  11. GOD bless you so much!!! ጌታን ወደ መቅደስ ጫፍ አውጥቶ ወደ ታች ተወርወር እንዳለው ሁሉ እኛንም በትዕቢትና በከንቱ ውዳሴ ወደ ላይ አውጥቶ በኃጢአትና በውርደት በኃፍረትና ከመንፈስ በማራቆት ሊወረውረን ይሻል፡፡

    GOD bless you so much!!!

    ReplyDelete
  12. ቃለ ህይዎት ያሰማልን!!!

    ReplyDelete
  13. thank u d,n melaku! pls God let us have absolute fasting for all of us with full love & peace!

    ReplyDelete
  14. amen enkan abro aderesen haylu birtatu ysten Egziabiher.

    ReplyDelete
  15. ወንድማችን በርታ ረድኤተ እግዚአብሔር አይለይህ:: በቤተክርስቲያን አስተምህሮ የጾሙን ዝርዝር ቀጥልበት (ዘወረደ: ቅድስት ወዘተ)
    ፎንቱ ከበፊቱ አሁን ጥሩ ነው በርታ

    ReplyDelete
  16. Amen!! Egizabiher beselam Yasigemiren endehum Yasifetsmen Waga Yeminagignebet Yadiregelin

    ReplyDelete
  17. ..... አሜን!!!...." በመሆኑም በሰላም፣ በፍቅር፣ በትሕትና ጾመን ለበዓለ ትንሣኤው በሰላም እንድንደርስ ጾመን ለማበርከት እንዲያበቃን እግዚአብሔር በቸርነቱ ይጠብቀን አሜን፡፡"

    ReplyDelete
  18. Yekedusan amlak abzeto Yebarkeh

    ReplyDelete
  19. kale hewat yasemalen wondemachen!!!

    sle waldba gedam hunita ebakh lemetsaf mokr. yetebalew hulu weri huno endiqer beyalenbet betsolet entga.

    ReplyDelete
  20. እግዚአብሄር ይስጥልንዲያቆን መልአኩ ። በርታ ጠንክር እግዚአብሄር ከአንተ ጋር ይሁን።

    ReplyDelete
  21. ቃለ ህይዎት ያሰማልን እግዚአብሄር ይስጥልን ዲያቆን መልአኩ ።

    ReplyDelete
  22. kale hiyiwot yasemalin!agelglotihin yibarkilh! tsega memihiran we likawunt yadililin!

    ReplyDelete
  23. ቃለ ሕይወትን ያሰማልን ዲያዎን መልአኩ፣ መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን በርታ ትልቅ ሥራ እየሰራህ ስለሆነ ለተዋሕዶ ልጆች እንዲሁም ለክርስቲያኖች በሙሉ የምትሰጠውን ትምህርተ ሃይማኖት ቀጥል እግዚአብሔር በሥራህ ሁሉ ይርዳህ አሜን።

    ReplyDelete
  24. Amen! Amen! Amen! Lantem kalehiwpt yasemalen!!! Bezih Tsome waket yenafse megeb endetemageben Geta Egziabehere yerdah!!!

    ReplyDelete
  25. ቃለህይወት ያሰማልን ወንድማችን! እግዚአብሔር ፀጋዉን ያብዛልህ!!!

    ReplyDelete
  26. ameeeeeeeeeeen
    egziabhair bemengstu yasbih

    ReplyDelete
  27. ቃለህይወት ያሰማልን ወንድማችን!!!

    ReplyDelete
  28. ቃለህይወት ያሰማልን ወንድማችን!!!

    ReplyDelete
  29. egzeabher serahn ybark ltlk kbr ybkah!

    ReplyDelete