Wednesday, January 25, 2012

አባ መቃርዮስ


በአንድ ወቅት አባ መቃርዮስ ይህንን ታሪክ ተናግሮ ነበር። ወጣት ሆኘ በአንዲት በዓት ውስጥ ስኖር መንደሩ ጸሐፊ ሊያደርጉኝ ፍለጉ። ይህንን ክብር መቀበል ስላልፈለኩ ሸሽቼወደ ሌላ መንደር ገባሁ። ሸሽቼ ስሔድም አንድ ሰው አብሮኝ ነበረ። ያም ሰው እኔ በእጄየምሰራውን እየሸጠልኝ ያገለግለኝ ነበር። በዚህ መሐል በዚያ መንደር የምትኖር አንዲትድንግል የነበረች ሴት ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ አርግዛ ተገኘች። ማርገዟም በታወቀ ጊዜከማን እንደጸነሰች ቤተሰቦቿ አጥብቀው ጠየቋት። እሷም የደፈረኝ እና የጸነስኩትም ከዛመናኝ ሰው ጋር  ብላ ነገረቻቸው። ቢዚህን ጊዜ መንደርተኞችም ሲሰሙ በፍጥነትመጥተው ያዙኝ። በጣም ጥቁር የመሰለ ማሰሮ እና ሌሎችንም የወዳደቁ ነገሮች በአንገቴዙሪያ አጠለቁብኝ ከዛም ወደ መንደሮችና አደባባዮች እያዳፉ ወሰዱኝ። በጣምምአብዝተው ይደበድቡኛል። ደግሞም « ይህ መነኩሴ ልጃችንን አበላሸ፤ ያዙት፤ በሉትእያሉ ይቀጠቅጡኛል» ብዙም ክፉ ቃላትን ይናገሩ ነበር።

እስከ ሞት ድረስ ደበደቡኝ። ከሽማግሌዎች አንዱ ወደ እኔ ቀረበና « ምን እያደረጋችሁነው ምንስ መስራታችሁ ይህን እንግዳ መነኩሴ መከራውን የምታሳዩት ደግሞስ እስከሞት ድረስ እንደዚህ የምትደበድቡት» ምክኒያታችሁስ ምንድን ነው ብሎ ጠየቃቸው። ያእኔን ያገለግለኝ የነበረ ሰው በሃፍረት ስሜት ውስጥ ሆኖ በኋላየ ይከተለኝ ነበር። እሱምእኔን እንደሚያገለግለኝ ያውቁ የነበሩ ሰዎች እርሱን ይሰድቡት ነበር። « ተመልከትይህንን አብዝተህ ታምነውና ታገለግለው የነበረው መነኩሴ እንደዚህ አሳፋሪ፤ ዘግናኝ እናአስነዋሪ ስራ በንጹህ ልጃችን ያደረገውን ስራአያሳፍርምምን እንደሰራ አየህይሉትነበር። የልጅቱም ወላጆች « ልጃችንን ለመንከባከብ ቃል እስኪገባ ድረስ እንዳትለቁት»ብለው ትዕዛዝ አስተላለፉ። እኔም ያንን ትዕዛዝ ሙሉ በሙሉ እንደምፈጽምላቸው ቃልከገባሁላቸው በኋላ ወደ  እንድሄድ ፈቀዱልኝ። እኔም ከዛ መከራ፤ ስቃይና እንግልትእንደተላቀኩ ባየሁ ጊዜ አምላኬን አመስግኜ ወደ በኣቴ ተመለስኩ። 
ከዚያምየሚያገለግለኝን ሰው « ያለኝን ቅርጫቶች ሽጥና ለዚያች ሴት ስጥልኝ» አልኩት እርሱምእንዳልኩት አደረገ። ለራሴም መቃርዮስ ሆይ ለራስህ ሚስት አግንተሃል፤ እርሷንመንከባከብ ትችል ዘንድ ካለፈው የተሻለ ስራ መስራት አለብህ ብየ ለራሴ ነገርኩት።ከዚያም ሌትና ቀን መስራት ጀመርኩ። ያፈራሁትንም ገንዘብ ለልጅቷ እየላኩ መርዳትጀመርኩ። ለብዙ ጊዜ እንደዚህ እያደረኩ መውለጃዋ ጊዜ እስኪደርስ ድረስ እረዳት ነበር።የመውለጃዋ ቀን በደረሰ ጊዜ ምጡ በዛባት ለብዙ ቀናት ብታምጥም መውለድ ግንአልቻለችም ነበር። « መንደርተኞችም ተሰባሰቡ፤ ተጨነቁ ደግሞም እርስ በእርሳቸውይነጋገሩ ጀመር ምንድን ነው ችግሩ እያሉ። የልጅቷ ምጥም እየበዛ፤ እየተሰቃየችበመጣች ጊዜ ምንድን ነው ችግሩብለው እሷን ጠየቋት። እሷም « ምክኒያቱንአውቄዋለሁ፤ ያንን መናኝ ባልፈጸመው ድርጊት ስለ ወነጀልኩት ነው የጸነስኩት ከሱአልነበረም፤ የጸነስኩት ከእገሌ ነው ብላ እውነቱን ከእንባ ጋር ነገረቻቸው። 
በዚህን ጊዜ ያያገለግለኝ የነበረው ሰው በጣም ከመደሰቱ የተነሳ እይሮጠ ወደ እኔ ፈጥኖ መጣናየምስራች ብሎ ሁሉን ነገር ገልጦ ነገረኝ። ያች ሴት የጸነስኩት ከመነኩሴው አይደለምእስክትልና እውነቱን እስክትናገር ድረስ መውለድ አልቻለችም ስለዚህ  እንደዚያሲያሰቃዩህ የነበሩት መንደርተኞች በሙሉ መጥተው ይቅርታ ሊጠይቁህ በዝግጅት ላይናቸው አለኝ። ነገር ግን ይህንን ስሰማ ሕዝቡ ስለ እኔ መልካም በማውራት ነብሴንበውዳሴ ያዝሏታል ብየ በመፍራት ሸሸሁ ወደ ሌላ ገዳምም ሄድኩ። ስለዚህ እኛ ከዚህምን እንማራለንሰውን በሃሰት ከመክሰስ፤ ከመውንጀል መታቀብ ይኖርብናል። ለዚህምእግዚአብሔር አምላካችን ይርዳን። የአባታችን የመቃርዮስ በረከታቸው እና ረድኤታቸውአይለየን አሜን።
የአባ መቃርዮስ በረከት ረድኤት ይደርብን አሜን

14 comments:

  1. kalhywet yasemalen....emeberhan tetetbikhe

    ReplyDelete
  2. የአባ መቃርዮስ በረከት ረድኤት ይደርብን አሜን አሜን አሜን::
    01/26/2012 @ 2:33PM

    ReplyDelete
  3. Berta Mele. Kalehiwot Yasemalen!

    ReplyDelete
  4. kalhywet yasemalen yagelegelote zemeken yarezemelk ....

    ReplyDelete
  5. wayo lena sintun yale hateatu amichew yihone thank you melaku azezew berta berta

    ReplyDelete
  6. በእውነት ይህ ነው አይባልም፣ በጣም ጥሩ ነው...ግን ከሆነ አይቀር በደንመብ ሙሉ ታሪካቸው በጣፍ ጥሩ ነው....በነገራችን ላይ 2ኛውን ልጄን መቃርስ ነው የምለው...

    ReplyDelete
  7. በነገርህ ላይ፣ በስምህ መሆኑ ምክንያቱ ግልጥ ነው...ግን መጀመሪያ ወይ መጨረሻ ላይ ስንክሳርን ብተጨምርበት ለሰርች ኢንጅንነ ይመች ነበር...

    ReplyDelete
  8. kalhywet yasemalen....emeberhan tetetbikhe

    ReplyDelete
  9. kale hiwot yasemelen rejeme edemena tena yestelen!

    ReplyDelete
  10. Egziabiher bidiratihin yikfelih

    ReplyDelete