Monday, December 12, 2011

በዓታ ለማርያም


እመቤታችን በ5485 ዓ.ዓ ከአባቷ ከኢያቄም ከእናቷ ከሐና እም ሊባኖስ ትወጽዕ መርዓት፡፡ ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች” ተብሎ በተነገረው መሠረት ነሐሴ 7 ቀን ተጸነሰች፡፡ግንቦት አንድ ቀን ሊባኖስ በምትባል ወረዳ በብጽአት እንደተወለደች የቤተክርስቲያን ታሪክ በሰፊው ያስረዳል፡፡ በጾም በጸሎት በአስተብቁዖት የተገኘች ናት፡፡ ንጽሕት በመሆኗም ማኅደረ እግዚአብሔር ሆናለች፡፡
ከዚህ በኋላ እመቤታችን መዋዕለ ጥብ እስክታደርስ ድረስ በአባት እናቷ ቤት 3 ዓመት ተቀመጠች፡፡ ከመዝ ነበረት ውስተ ቤተ አቡሃ ወእማ 3ተ ዓመተ እንዘ ትጠቡ ሐሊበ እማ (እንዳለ በነገረ ማርያም፡፡)
ኢያቄምና ሐናም ልጃቸውን ሲያሰሳድጉና ስላደረገላቸውም ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽመው ሲያመሰግኑት ሦስት ዓመት ኖሩ። በጾም፤ በጸሎት ተወስነው ለድሆችና ለጦም አደሮች ምፅዋት እየሰጡ በጐ ሥራ መሥራትን አበዙ።
      ልጃቸውንም ድንግል ማርያምን በንጽሕና ሲያሳድጉ ሦስት ዓመት በተፈጸመ ጊዜ ሐና ባሏን ኢያቄምንወንድሜ  ሆይ ልጃችንን ለቤተ እግዚአብሔር ብፅዐት አድርገን እንስጥ። ልጃችን ቤተ እግዚአብሔርን ልታገለግል እንጂ በዚህ ዓለም እኛን ልታገለግል እንዳልተሳልን አስብ አለችው።ኢያቄምም ይህን ነገር ከሚስቱ በሰማ ጊዜ ደስ አለው።

ነብየ እግዚአብሔር ዳዊት ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ጆሮሸንም አዘንብዪ ወገንሽን የአባትሽንም ቤት እርሺ ንጉሥ/ክርስቶስ/ ውበትሽን /ንጽሐ ባሕርይሽን/ ወድዶአልና መዝ 44÷10-11 ብሎ እንደተናገረ ለወላጆቿ የብፅዐት ልጅ የሆነችው ድንግል ማርያም ሆዷ ዘመድ ሳይወድ አፏ እህል ሳይለምድ ከእናቷና  ከአባቷ ተለይታ ታህሣሥ ሦስት ቀን በሦስት ዓመት ወደ መቅደሰ ኦሪት ገብታለች። በአታ ለማርያም ማለትም የድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ማለት ነው።
ከዚህም በኋላ በ3 ዓመት ልተተ ሕፃናትን ፈጸመች አበ እመ እያለች ታጫውት ጀመር እነርሱም ከእንግዲህ ወዲህማ ስእለት መብለት ይሆንብን የለምን ወስደን እንስጥ ብለው ይዘዋት ወደ ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዘካርያስም ሕዝቡን ሰብስቦ ጉባዔ አድርጎ ሲያስተምር ቆያቸው ከዚያውም ደርሰው እነሆ ተቀበሉን አሏቸው እነርሱም እንቀበላለን ብለው ቢያዩዋት ከፀሐይ 7 እጅ አብርታ ዕንቈ ባሕርይ መስላ ታያቻቸው እነርሱም እኛ ይህችን የመሰለች ፍጡር ምን እናደርጋታለን ምን እናበላታለን ምን እንጋርድላታለን ብለው ሲጨነቁ ከዚህም መካከል እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያም መንፈሳዊ ረኅብ ተነስቶባት ምርር ብላ አለቀሰች፡፡
ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል በመሶበ ወርቅ ኅብስት ሰማያዊ ፤ በብርሃን ጽዋ ስቴ ሕይወት ይዞ ረቦ ታያቸው ሕዝቡም ዘካርያስን አባታችን ይህ የወረደው ክብር ላንተ እንደሆነ ተነስተህ ታጥቀህ እጅ ነስተህ ሰግደህ ተቀበል አሉት፡፡ ዘካርያስም እሽ ብሎ እጅ ነስቶ ሰግዶ እቀበላለሁ ብሎ ሲያይ ወደሰማይ እራቀው መጠቀው፡፡ ከሕዝቡም እያንዳንዱ እየተነሱ እንቀበላለን ብለው ቢያዩ ወደሰማይ ራቃቸው መጠቃቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ ለናንተ ለእንግዶች የወረደ ክብር እንደሆነ ሕፃኒቱን ይዘሽ ወደዚያ ፈቅ ብለሽ ተቀመጪ አላት፡፡ እርሷም ሕፃኒቱን ይዛ ወደዚያ ፈቅ ብላ ተቀመጠች፡፡ መልአኩም ከራሳቸው ላይ ረቦ አልወርድም አለ፡፡
አዲስ አበባ ዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ በዓታ ለማርያም ገዳም 
ሁለተኛም ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ነገር የሚያውቅ የለም ሕፃኒቱን ከዚያው ትተሽ አንቺ ወዲህ ነይ አላት፡፡ እርሷም እሽ ብላ ሕፃኒቱን እዚያው ትታ ወደነሱ ሄደች፡፡ ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል ወርዶ 1 ክንፉን ጋርዶ 1 ክንፉን አጐናፅፎ ኅብስቱን አብልቷት ወይኑን አጠጥቷት እመቤቴ ሆይ መንገድ ባስመታሁሽ ማሪኝ ብሎ የብርሃን መሶብ የብርሃን ጽዋ  ይዞ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡
ሕዝቡም የምግቧማ ነገር ከተያዘ ከሰው ጋራ ምን ያጋፋታል ቦታዋ ከቤተ መቅደስ ይሁን እንጂ ብለው ዙፋኑን ዘርግተው ምንጣፏን አንጥፈው መክዳውን ግራና ቀኝ መጋረጃውን አድርገው ከቤተ መቅደስ አኖሯት፡፡ይኸውም የተደረገው የታኅሣሥ በዓታ ዕለት ነው፡፡
እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ኅብስት ሰማያዊ እየተመገበች፤ ስቴ ሕይወት እየጠጣች ከመላእክት ጋራ እየተጫወተች 12 ዓመት በቤተ መቅደስ ተቀመጠች፡፡ ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ ፲ተወ፪ተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኅበ መላእክት ወስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ፡፡ ( እንዳለ ቅዱስ ያሬድ፡፡)
እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በቤተ መቅደስ ሳለች ትበላው የነበረ ኅብስት ሰማያዊ ትጠጣው የነበረ ስቴ ሕይወት የት የተገኘ ነው ቢሉ በገበሬ እጅ ያልተዘራ በቤተ ሰብእ እጅ ያልተሠራ በእግዚአብሔር እጅ የተፈጠረ ያማረ የተመረጠ ነው እንጂ  ፡፡
ኦ ድንግል አኮ ኅብስተ ምድራዊ ዘተሴሰይኪ አላ ኅብስተ ሰማያዌ እም ሰማየ ሰማያት ዘበሰለ ፤ ኦ ድንግል አኮ ስቴ ምድራዌ ዘሰተይኪ አላስቴ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት ዘተቀድሃ፡፡ (እንዳለ አባ ሕርያቆስ፡፡)
እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በቤተ መቅደስ ሳለች አይሁድ ተሰብስበው መከሩ ምክሩስ እንዴት ነው ቢሉ ቀድሞ ሳሚናስ ሙቶ የተነሣ ዕለት የነገረንን ነገር እረሳችሁት ሰማይ ምድርን እመቅ አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች ብሎ ነግሮን አልነበረምን ? የኢያቄምና የሐና ልጅ እኛን እስከ መቼ ድረስ ባሮች አድርጋ ትገዛናለች ያ አምላክ የሚባለውን ሳትወልደው ይኸን ጊዜ ገድላችሁ ውሀ ጣሏት ብለው ሰደዷቸው እነርሱም እንገላለን ብለው ቢሄዱ ቤተ መቅደሱ 4 ማዕዘን እሳት ሁኖ መላእክትም ሰይፍ ሰይፋቸውን መዘው ረበው ታዩአቸው፡፡እነርሱም እርሷንስ እሳት ፈጃት ብለው ተመልሰው ወደየቤታቸው ሄዱ ፡፡
በማግስቱ አይሁድ ከቤተ መቅደስ ቢደርሱ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያምን ደህናዋን አገኟት ተመልሰው ሂደው እነዚያን የላኳቸውን ሰዎች ጠርተው ምነው ገድላችሁ ከውሀ ጣሏት ብለናችሁ አልነበረምን? ምነው ትታችኋት መጣችሁ አሁንም ሂዳችሁ ግደሉና ከውሀ ጣሏት ብለው ቢሰዷቸው እነርሱም እንገላለን ብለው ቢሄዱ መንገዳቸው ዱር ገደል ባሕር ሁኖ ቈያቸው ተመልሰው ሄደው ቢነግሯቸው ይህን ሁሉ የምትጫወትብን በአስማቷ አይደለምን የእሷን አስማት የሚጠፋ አስማተኛ እንፈልግ እንጂ ብለው እየራሳቸው ቢበተኑ መጥቁል የሚባል አስማተኛ በምትሐት መጫኛ የሚያቆም አገኙ፡፡
ከዚያውም ደርሰው በሐና በኢያቄምና በኛ መካከል ትፈርድብን ትፈርድልን ብለን መጥተናል እነርሱ ጌቶች እኛን ባሮች አድርገው ሊቀሩ ስራይ ይሰርያሉ አሉት፡፡ፍታሕ ማዕከሌነ ወማዕከለ ኢያቄም ወሐና (እንዳለ በነገረ ማርያም፡፡)ከነሳቸው የበለጠች ልጃቸው አስማተኛ መቅደሳችንን እሳት መንገዳችንን ዱር ገደል ባሕር እያደረገች አስቸግራናለችና እሷን ታጠፋልን ብለን መጥተናል አሉት፡፡ ወወለቶሙኒ ተአኪ እምኔሆሙ፡፡ (እንዳለ በነገረ ማርያም፡፡)
እርሱም ይህማ ምን ይቸገረኛል እግዚአብሔርን ቅሉ እረ አዘዋለሁና ና ብለው ይመጣል ሂድ ብለው ይሄዳል ዋጋዬንማ ከሰጣችሁን እሺ እርሷንስ አጠፋላችኋለሁ አላቸው፡፡ ለእግዚአብሔርኒ አነ አመልክ ከመ ገብር ለእመ እብሎ ነዓ ይመጽእ ወለእመ እብሎ ሑር የሐውር (እንዳለ በነገረ ማርያም፡፡)
እነርሱም እርሷንማ ታጠፋህልን ዋጋህንስ እንካ ተቀበለን ብለው 30 ምዝምዝ ወርቅ 30 ብር 7 ፈረስ 40 በግ 70 ፍየል 60 ጊደር 300 አልባሳት አድርገው ሰጡት፡፡ መልዓ ቤቶ ወርቀ ወብሩረ ወአልባሳተ ቀንጠት ዘአልቦ ኁልቀ÷ ወመስፈርት (እንዳለ በነገረ ማርያም፡፡)
መጥቁልም ቤተ መዛግብቱን ከፍቶ አገባለሁ ብሎ መለስ ብሎ ቢያየው ብሩ ወርቁ ዝጐ አፈር በልቶት አፈር ዱቄት ሁኖ አልባሳቱም ብል በልቶት አገኘው እርሱም የኢያቄምና የሐና ልጅ ሳልቀድማት ቀደመችኝ ብሎ እጁን ጾፋ፡፡ ጠፍሐ እደዊሁ እንዳለ በነገረ ማርያም
ደቂቀ እስራኤልን ጠርቶ አንድ አንዱን እያነሳ ያሳያቸው ጀመር፡፡ ንዑ ተጋብኡ ደቂቀ እስራኤል እንዘ ትሬእዩ ዘሠርዓት ብየ (እንዳለ በነገረ ማርያም፡፡)እነርሱም እኛማ አላልንህምን አንተ ነህ እንጂ እግዚአብሔርንም ቅሉ እኔ አዘዋለሁ ና ብለው ይመጣል ሂድ ብለው ይሄዳል አልከን እንጂ ወይንስ እርሷን ታላጠፋህልን ወይንስ የገንዘባችን ነገር እንዴት ታደርግልናለህ ብለው ቢያስጨንቁት እርሱም ቆዩ የርሷንስ ነገር አሁን በመንፈቀ ሌሊት አሳያችኋለሁ ብሎ ይልቁንስ ከሰዎቻችሁ ጐበዝ ጐበዙን መርጣችሁ 370 ሰው ስደዱልኝ አላቸው እነርሱም ሰደዱለት እርሱም ከነዚያው ከሰደዱለት ወንዝ ወርዶ አንዱን አርዶ ሰውቶ 370 አጋንንትን ስቦ አውጥቶ ጠየቀ፡፡
ይህስ እንዴት ነው ቢሉ የኢያቄምና የሐና ልጅ ይኸን ያህል ገንዘብ አጠፋችብኝ አሁንስ የገንዘቤን ነገር እንዴት ታደርጉልኛላችሁ እርዱኝ እንጂ አላቸው አጋንንትም የማይሠሩትን እንሠራለን የማያደርጉትን እናደርጋለን ማለት ልማዳቸው ነውና ይህንማ ምን ይቸግረናል ሰማይን አውርዱ ብትለን እናወርድልሃለን ምድርን ጠቅልሉ ብትለን እንጠቀልልሃለን ይኸንንማ ምን ይቸግረናል እሽ እንረዳሃለን አሉት፡፡
ለእመ ትብለነ ሰማየ አውርዱ ናወርድ ለከ ወለእመ ትብለነ ምድረ ጠብልሉ ንጠበል ለከ ወአልኮ ዘይሰዓነነ (እንዳለ በነገረ ማርያም)
መጥቁልም በመንፈቀ ሌሊት ርዱኝ ያላቸው አጋንንትም ጨለማ ደስታቸው ነውና እሽ ብለው መጡለት አጋንንት ፊት ፊት  መጥቁል በመካከል አይሁድ በኋላ ሁነው ነጋሪት እየተመታ እምቢልታ እየተነፋ እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያምን ለመግደል ለቤተ መቅደስ 2 ምንዳፈ ሐፅ ሲቀራቸው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ እዚያ ድረስ ያልተደረገው ያልተነገረው መብረቅ ነጐድጓድ ወርዶ አጋንንትንም መጥቁልንም አይሁድንም ቀጥቅጦ አጠፋቸው፡፡
መብረቅ ወነጐድጓድ ወፅአ እምውስቴቶሙ ዘኢኮነ እምአመ ከሉ ለ370 ሰብእ 370 እምነ አጋንንት ወኢተርፈ 1ዱ እምኔሆሙ (እንዳለ በነገረ ማርያም)
እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በማግሥቱ ወጥታ አይታ መጥቁል ሆይ እኔን አጠፋ ብለህ መጥተህ አንተ እንዲህ ሆንህ ካንተ መከራ መዓት ያወጣኝ አምላክ ይክበር ይመስገን ብላ ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡ወበሳኒታ ወፅአት እግዝእትነ ማርያም ወርእየቶሙ ለእሙንቱ አብድንት (እንዳለ በነገረ ማርያም፡፡)ከዚህም በኋላ በድኑ ለዝክረ ነገር የ3 ቀን መንገድ እየሄደ ይሸት ጀመር፡፡እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም የጌታን ኅቡዕ ስሙን ብትደግምበት መሬት ተከፍቶ ዋጣቸው ፡፡ወውኅጠቶሙ ምድር ለ370 ሰብእ ወለ370 እምነ አጋንንት ለእሙንቱ አብድንት ምስለ ሥጋሆሙ ወነፍሶሙ ወይትዋነይዎሙ ዐውያነ እሳት (እንዳለ በነገረ ማርያም፡፡)
ከዚያም በኋላ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እጅግ ታፈረች ተፈራች የሚናገራት ሰው ጠፋ፡፡    ኦ ግርምት ድንግል (እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም)፡፡
ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች ዕመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን -አሜን

28 comments:

  1. ቃለ ህይወትን ያሰማልን፣ መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን!!!!!!!
    ቅድስተ ቅዱሳን ወላዲተ አምላክ ዋስ ጠበቃ ትሁንህ!!!

    ReplyDelete
  2. ቃለ ህይወትን ያሰማልን::
    የእመቤታችን በረከት አይለይህ::

    ReplyDelete
  3. ቃለ ህይወትን ያሰማልን

    ReplyDelete
  4. ቃለ ህይወትን ያሰማልን፣ መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን!!!!!!!
    ቅድስተ ቅዱሳን ወላዲተ አምላክ ዋስ ጠበቃ ትሁንህ

    ReplyDelete
  5. ቃለ ህይወትን ያሰማልን፣ መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን!!!!!!!
    ቅድስተ ቅዱሳን ወላዲተ አምላክ ዋስ ጠበቃ ትሁንህ!!!

    ReplyDelete
  6. ቃለ ህይወትን ያሰማልን፣ መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን!!!

    ReplyDelete
  7. ከዚያም በኋላ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እጅግ ታፈረች ተፈራች የሚናገራት ሰው ጠፋ፡፡ ኦ ግርምት ድንግል (እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም)፡፡

    ቃለ ህይወትን ያሰማልን፣ መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን!!!!!!!
    ቅድስተ ቅዱሳን ወላዲተ አምላክ ዋስ ጠበቃ ትሁንህ

    ReplyDelete
  8. weldelibanos abereheDecember 14, 2011 at 9:09 PM

    ቃለ ህይወትን ያሰማልን፣ መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን!!!!!!!
    ቅድስተ ቅዱሳን ወላዲተ አምላክ ዋስ ጠበቃ ትሁንህ

    ReplyDelete
  9. ዲያቆን ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
    ጸጋውን ያብዛልህ።

    ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

    ReplyDelete
  10. qale hiwot yasemalen mengeste semayat yawrselen

    ReplyDelete
  11. kale hiwot yasemalen mengiste semayat yawrselen

    ReplyDelete
  12. ዲያቆን ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
    ጸጋውን ያብዛልህ።

    ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

    ReplyDelete
  13. ዲያቆን ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
    ጸጋውን ያብዛልህ።

    ReplyDelete
  14. ዲያቆን ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
    ጸጋውን ያብዛልህ።

    ReplyDelete
  15. ቃለ ህይወት ያሠማልን። መንግስተ ሰማያት ያዉርስልን ። ያገልግሎት ዘመናችሁን ይባርክልን

    ReplyDelete
  16. ወንድማችን ቃለህይወት ያሰማልን እረጅም እድሜ ይስጥልን ከቤቱ አንጣህ !!

    ReplyDelete
  17. ቃለ ህይወትን ያሰማልን፣ መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን!

    ReplyDelete
  18. ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋራ ፀንቶ ይኑር፡፡ አሜን

    ReplyDelete
  19. Yetebareke Yetekedese hiwot yadelelen!!!

    ReplyDelete
  20. kale hiwot yasemalin

    ReplyDelete
  21. Egziabherin yamene kibru kesemayat belay new. Emebetachin bereketua yideribin! Kale hiwot yasemalin! Beselam betena yitebikilin!

    ReplyDelete
    Replies
    1. ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋራ ፀንቶ ይኑር፡፡ አሜን!

      Delete
  22. ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡

    ReplyDelete
  23. ቃለ ሂወት ያሰማልን ከዚ በላይ የምታስተምርበት እድመና ፀጋ ይስጥህ

    ReplyDelete
  24. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ከዚ በላይ የምታስተምርበት እድሜና ፀጋ ይስጥህ....የ እመበታችን ምልጃና ረዲእት ከሁላችን ይሁን ኣሜን....

    ReplyDelete
  25. የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋራ ፀንቶ ይኑር፡፡ አሜን!

    ReplyDelete