Saturday, August 20, 2011

ከመ ትንሳኤ ወልዳ ( እንደ ልጅዋ ትንሳኤ )


እንኳን አደረሳችሁ

ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ደባትረ ብርሃን ኀበ ተተክሉ
ለገነተ ጽባሕ በማዕከሉ
እመቤቴ ማርያም ሆይ በምስራቃዊ ተክለ ገነት መካከል የብርሃን ድንኳኖች ወደተተከሉበት 
ለዐረገ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል
መልክአ ማርያም
  ትንሣኤ በሁለት ይከፈላል ጊዜያዊና ዘለዓለማዊ በመባል ፡፡
ጊዜያዊ ትንሣኤ የሚባለው የእግዚአብሔር ከሃሊነት የሚገለጽበት ተኣምራዊ ሥራ ሆኖ በተወሰኑ ሰዎች ላይ ይፈጸምና ዳግም ሞትን የሚያስከትል ነው፡፡

ለምሳሌ ኤልያስ ያስነሣውን ወልደ መበለት (1 ነገ 178-24)
ዐጽመ ኤልሳዕ  ያስነሣው ሰው (2ኛነገ 132021)
ትንሣኤ ወለተ ኢያኢሮስን (ማቴ 9 8-26)
በዕለተ ስቅለት ከመቃብር ወጥተው በቅድስት ከተማ የታዩ ሙታን (ማቴ 2752-53) በቅዱስ ጴጥሮስ ጸሎትና ምልጃ የተነሣች ጣቢታን (ሐዋ 936-41)
እንዲሁም ትንሣኤ አልዓዛርን ፡፡(ዮሐ 1143-44)
                 አልዓዛር ከሞተ በኋላ በአራት ቀን ተነስቷል፡፡ (ዮሐ 1143-44)፡፡  ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያነሣውም ለማየት በመቃብሩ ዙሪያ የነበሩ አይሁድ ከሞተ በኋላ በአራት ቀን መነሣቱን ተመልክተው አደነቁ የአልዓዛር እኅቶችም  ተደሰቱ፡፡ አልዓዛር ግን ለጊዜው ቢነሣም ቆይቶ ተመልሶ ዐርፏል( ሞቷል ) ወደፊት ትንሣኤ ዘጉባኤ ይጠብቀዋል፡፡

              መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤያችን በኩር ሆኖ በሞተ በሦስተኛው  ቀን ሙስና መቃብርን(የመቃብርን ሥልጣን) አጥፍቶ ሞትን ድል አድርጎ በገዛ ሥልጣኑ ተነሥቷል፡፡ እናቱ እመቤታችንም በልጇ ሥልጣን  እንደ ልጇ ትንሣኤ (ከመ ትንሳኤ ወልዳ ) በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ትንሣኤ ዘጉባኤን ሳትጠብቅ በክብር ዐርጋለች፡፡ የቅድስት ድንግል ማርያም ትንሣኤ የክብርና የሕይወት ትንሣኤ ሲሆን ሁለተኛ ሞትን አያስከትልም ትንሣኤ ዘጉባኤንም አይጠብቅም፡፡

እንደዚህ ያለውን ትንሣኤ ከእርሷ በቀር ሌሎች ቅዱሳን ወይም ነቢያትና ሐዋርያት አላገኙትም በዚህም ሁኔታ የቅድስት ድንግል ማርያም ትንሣኤ ልዩ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ይህም ትንሣኤ ዘለዓለማዊ የሆነ ከዳግም ሞተ ሥጋ ነጻ የሆነ ትንሣኤ ነው፡፡

            በነሐሴ 16 በዕመቤታችን ትንሳኤ ጊዜ አባቷ ዳዊት በገናውን እየደረደረ ጸሐፊው የነበረው ዕዝራም መሰንቆውን ይዞ ቅዱሳን መላእክት ነቢያትና ጻድቃን እያመሰገኗት በብሩህ ደመና ወደ ሰማይ ዐረገች ከዚያም በክብር ተቀመጠች፡፡ በዚያም ስፍራ ሁለተኛ ሞት ወይም ሐዘን ጩኸትና ስቃይ የለም የቀደመው ሥርዐት አልፎአልና (ራዕ 214-5)፡፡

            የእመቤታችን ዕርገትም በመጽሐፍ ቅዱስ ከተገለጸው ከእነ ሄኖክና ኤልያስ ዕርገት የተለየ ነው፡፡  ሄኖክ ወደ ሰማይ ያረገው በምድር ሳለ እግዚአብሔርን በእምነቱና በመልካም ሥራው ስለአስደስተና በሥራውም ቅዱስ ሆኖ ስለተገኘ ሞትን እንዳያይ ዐረገ፡፡ ወደፊት ገና ሞት ይጠብቀዋል ሞቶም ትንሣኤ ዘጉባኤ ያስፈልገዋል፡፡ «ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም» (ዕብ 115)፡፡

            ነቢዩ ኤልያስም በእሳት ሠረገላ ተነጥቋል «እነሆ የእሳት ሠረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው፤ ኤልያስም በአውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ»  (2 ነገ 210)፡፡ ነቢዩ በእሳት ሠረገላም ቢነጠቅም ወደፊት ሞት ይጠብቀዋል፤ ትንሣኤ ዘጉባኤም ያስፈልገዋል፡፡

የልጅዋ የመድኃኔዓለም ቸርነት ፤ የዕመቤታችን የድንግል ማርያም ረድኤት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን

13 comments:

  1. Qalehiywot yasemalin.

    ReplyDelete
  2. አሜን እንኳን አብሮ አደረሰን
    መሥፍን እዘዘው

    ReplyDelete
  3. አሜን እንኳን አብሮ አደረሰን
    እግዚአብሔር ይስጥልን
    በርታ
    ቄስ ተሸመ አቡሀይ

    ReplyDelete
  4. AMEN! YE EMEBETACHIN BEREKET AYILEYEN!!

    ReplyDelete
  5. Diakon Melaku Amen enkuan Abro Aderesen

    ReplyDelete
  6. Diakon amen enkuan abero aderessen

    ReplyDelete
  7. Diakon Melku Enqan abro Adersen, Please conitinoue the great job.
    Belachew

    ReplyDelete
  8. Deacon, I really admire the way you organize your articles. I heard most of the contents, presented in your blog, from different sources in our church in different times. However, I have never came across with such a wonderful reference compiled like this one. I think, that is what makes me read your blog as soon as they posted.

    I pray for your patient and endurance every time after I read the materials. I want you to keep posting such a wonderful, meaningful, and helpful religious references.

    You know what, One day who knows, we all might refer these materials for our religious facts and they might be part of our church references.

    Thanks for your time and concern to keep update us and learn a lot about our own church stories, people, places, and more facts.

    God be with you.
    God bless Ethiopia and our church!

    Abebaw

    ReplyDelete
  9. Dia'qon Mel'aku ,

    I hope it is not late to say "enquan abro aderesen" ...Her Resurrection is truly like Her Son in a sense that She won't see death any more by the merit of Her beloved Son ...tensae'ahse keme tensa'ae welda aman be aman::

    May the Loving Mother of God be with you !

    WD

    ReplyDelete
  10. Tefahe, Are U Ok? sele Tekelehayemanot tesefelenalehe beye tebeke nebere.keep writing we are waiting for U. yemiak

    ReplyDelete
  11. Is any way that I can read this ? B/c my phone didn't let me read Amharic words . I really wanna learn about my realign please thank u .

    ReplyDelete