Monday, August 18, 2014

ምሥጢረ ደብረታቦር


አሐደ ለከ ወአሐደ ለሙሴ ወአሐደ  ለኤልያስ ንግበር ማኅደረ
ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ ፤ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ኤልያስ እንሥራ  ›      
 ቅዱስ ጴጥሮስ

ታቦር ተራራ የዛሬ ገጽታው
           ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ቅዱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤሌያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ከኤልያስ እንሥራ አለ።

እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር። ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና። ተነሡ አትፍሩም አላቸው።ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም። የማቴዎስ ወንጌል 17፡1-8

በቂሳርያ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ ለሰዎች  የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ጠይቋቸው አንዳንዶች ከነቢያት አንዱ ነህ ይሉሃል፣ አንዳንዶች ሙሴ ነህ ይሉሃል፣ ሌሎች ደግሞ ኤልያስ ነህ ይሉሃል እያሉ መለሱለት ጌታችንም መልሶ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ ሲጠይቃቸው የሐዋርያት አፈጉባዔ ሊቀ ሐዋርያት ቅ/ጴጥሮስ ‹አንተ ክርስቶስ  የሕያው እግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ነህ› ብሎ በመመስከሩ ጌታም ‹የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማይ ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ…› ተብሏል፡፡

ይህ በሆነ በሰባተኛው ቀን ሦስቱን ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ በዚያም እንደ ዮርዳኖስ ወንዝ መድኃኔዓለም ክብረ መንግስቱን ፤ ብርሃነ መለኮቱን ገልጧል ፡፡ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ የሆነው በዓለ ደብረታቦር የዚህ ታሪክ መታሰቢያ ነው ፡፡

ታቦር ተራራ ከገሊላ ባሕር በስተምዕራብ 17 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ፤ ከናዝሬት ከተማ በስተምስራቅ ፤ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ አቅጣጫ ሲገኝ ከባሕር ጠለል በላይ 572 ሜትር ነው ፡፡ከላይ ወደታች ሲታይ ታቦር ተራራ ቅርጹ የተገለበጠ የሻይ ስኒ ይመስላል ይላሉ ፡፡
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። 

ምሥጢረ መንግሥቱን ለምን በታቦር ተራራ ገለጸው ?
መድኃኔዓለም ሌሎች ተራሮች እያሉ ክብሩን ለመግለጥ ስለምን ደብረ ታቦርን መረጠ ቢሉ ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡
  1. ትንቢት 
“ ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ ወይሰብሑ በስምከ ”

ታቦርና አርሞንኤም በስምህ አምነው በተደረገላቸው ነገር ደስ ይላቸዋል፣ ስምህን ያመሰግናሉ፣ ለስምህም ምስጋና ያቀርባሉ፡፡ “ መዝ 88፡12

  1. ምሳሌ

ባርቅ ሲሳራን ድል አድርጎበታል መሳፍንት 4፡6 ይኸውም ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡‹… የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደገና ክፉ ሥራ ሠሩ፡፡ እግዚአብሔርም በአሶር በነገሠው በከነዓን ንጉሥ በኢያቡስ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው የሠራዊቱም አለቃ በአሕዛብ አሪሶት የተመረጠው ሲሣራ ነበር… ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩትና የእስራኤልንም ልጆች ሃያ ዓመት ያስጨንቃቸው ነበር›/መሳ 4.1-3/

ሁሌም ቢሆን የሰውን በደል ዐይቶ እንደወጣችሁ ግቡት፣ እንደገባችኋት ውጧት የማይልና ‹… ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል› የተባለለት እግዚአብሔር ከዚህ ቀንበር የሚላቀቁበትን መላ ራሱ አመለከታቸው፡፡ /1ቆሮ. 10-13/፡፡

እስራኤላውያን ወደ ፈጣሪያቸው በጮኹ ጊዜ የለፊዶት ሚስት የሆነችውንና እስራኤልን በነቢይነትና ዳኝነት ታገለግል የነበረችው ነቢይቱን ዲቦራን ተጠቅሞ የማሸነፊያ መላውን አመለከታቸው፡፡ ነቢይቱ ዲቦራ ትንቢት ከመናገር አልፋ የእስራኤልን ንጉሥ ባርቅ ከእኔ ጋር ወደ ጦርነቱ ውጪ ብሎ ባስጨነቃት ጊዜ በጦር አዝማችነትም ተሳተፈች፡፡

እግዚአብሔር በነቢይቱ በዲቦራ በኩል ለእስራኤል ንጉሥ ‹ሔደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጡ…› ብሎ አዞት ነበርና ንጉሡ ዐሥር ሺሕ ብረት ለበስ ያልሆነ እግረኛ ሠራዊት ይዞ ደብረ ታቦርን ተማምኖ በተራራው ላይ መሸገ ጦርነቱ ሳይጀመር አለቀ፡፡ ምክንያቱም ‹እግዚአብሔርም ሲሣራን ሰረገሎቹንም ሁሉ ሠራዊቱንም ሁሉ ከባርቅ ፊት በሰይፍ ስለት አስደነገጣቸው፡፡ ሲሣራም ከሰረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ…› /መሳ. 4.15/

እስራኤል በእግዚአብሔር አጋዥነት በታቦር ተራራ ላይ የሃያ ዓመት የግፍና የሰቀቀን አገዛዝ ቀንበራቸውን ከትከሻቸው አሽቀንጥረው በምትኩ የድል ካባን ደረቡ ‹… በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ የባዕድ ጭፍሮችንም አባረሩ› ተብሎም ጀግንነታቸው ተጻፈላቸው፡፡ የታቦር ተራራ ያኔ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ባለውለታቸው ነበር፡፡ /ዕብ. 11.32-34/

ጌታም በልበ ሐዋርያት ያለ ሰይጣንን ድል ያደርግበታልና ማለትም በልባቸው ጥርጥርን እና ፍቅረ ሢመትን( የሥልጣን ፍቅር) ያሳደረ ዲያብሎስን ድል ነስቶላቸዋል ፡፡ከዚህም በመነሳት ነው በዓለ ደብረታቦር የደቀመዛሙርት ተማሪዎች በዓል ነው የሚባለው ፡፡
ለምን 3ቱን ሐዋርያት ( ጴጥሮስ ፤ዮሐንስ እና ያዕቆብን)  ብቻ ይዞ ወደ ተራራ ወጣ፡-
  1. ለፍቅሩ ስለሚሳሱ ነው፡፡ ይህም በዕብራይስጡ ኬፋ ፤ በግሪኩ ጴጥሮስ ፤በግዕዙ ኰኲሕ( ዐለት) የተባለው የዮና ልጅ ስምዖን ጌታ   እሞታለሁ እያለ ጌታችን ሲናገር አይሁንብህ በማለቱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ እርሱን ስሙት የሚል መለኮታዊ ድምጽ ሰምቷል፡፡ዮሐንስና ያዕቆብ ጌታን ምድራዊ መሲህ አድርጎ በማሰብ ቀኝ ጌትነትን እና ግራ ጌትነትን በእናታቸው በኩል  የማይገባ ልመና አቀረቡ ዮሐንስና ያዕቆብ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ? ሲባሉ አዎ ብለው መለሱ በዚህም ከባሕርይ አባቱ እርሱን ስሙት የሚል ድምጽ ሰሙ፡፡
  2. በይሁዳ ምክንያት ነው ኢሳ 26.13 ‹ኃጥእ ሰው የእግዚአብሔርን ክብር እንዳያይ ያርቁታል› እንዲል እርሱን ጥሎ አስራ አንዱን ወደ ተራራ ይዞ ቢወጣ ከምሥጢር ቢለየኝ በሞቱ ገባሁበት እንዳይል፡፡ ያም ባይሆን  ስምንቱ ደቀ መዛሙርት ለምን ይከለከላሉ ቢሉ አልተከለከሉም በርዕሰ ደብር (በተራራው አናት) ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት የተገለጸው ምስጢር በእግረ ደብር (በተራራው ግርጌ) ለነበሩት ስምንቱ ደቀ መዛሙርት ተገልጦላቸዋል፡፡ ይህም በደብረሲና ለሰባው ሊቃናት የተገለጠ ምሥጢር በከተማ ለነበሩት ለኤልዳድና ሙዳድ እንደተገለጠ ማለት ነው፡፡ ዘኁልቊ 11፡26
ኤልያስና ሙሴን ለምን አመጣቸው?
ሀ- በአንድ ወቅት ነቢዩ ሙሴ እግዚአብሔርን ‹‹ወለእመሰ ረከብኩ ሞገሰ በኀቤከ አስተርእየኒ ገሐደ ሊተ ወአእምር ወእርአይከ ከመ ይኩነኒ ርኪበ ሞገሰ በቅድሜከ ዮም›› ፣ በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘቴ እውነት ከሆነስ ፊት ለፊት ተገልጸህልኝ ልይህና በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘቴን ልወቀው› ሲል ጠይቆት ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ‹… ትሬኢ ድኅሬየ ወገጽየሰ ኢያስተርኢ ለከ፣ ጀርባዬን ታያለህ ፊቴን ግን አታይም› ብሎት ነበር፡፡ /ዘጸ. 33.13 እና 23/
የዚህ ኃይለ ቃል ትርጓሜና ሐተታ በደብረ ታቦር ተፈጸመ፡፡ እንዲህ ማለቱ በአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን ሰው ሆኜ ሥጋ ለብሼ ኋላ በደብረ ታቦር እስክገለጽልህ ድረስ አንተ በመቃብር ተወስነህ ትኖራለህ ማለቱ ነበር፡፡ ይህን ማለቱ እንደሆነ የታወቀው ግን በደብረ ታቦር ሙሴን ከብሔረ ሙታን አምጥቶ ባቆመው ጊዜ ነበር፡፡ 
ለ- ልዑል እግዚአብሔር ነቢዩ ኤልያስን ‹አንተሰ ትከውነኒ ስምዓ በደኃሪ መዋዕል፣ አንተ በኋለኛው ዘመን ምስክር ትሆነኛለህ› ብሎት ነበርና ይኸውም ኃይለ ቃል ኤልያስ ከብሔረ ሕያዋን መጥቶ ‹የእኔን የኤልያስን ጌታ ማን ኤልያስ ነው ይልሃል እግዚአ ኤልያስ፤ አምላከ ኤልያስ ይበሉህ እንጂ› ሲል በደብረ ታቦር ተፈጸመ፡፡  ታያለህ የተባለው ሙሴም አየ፣ ትመሰክራለህ የተባለው ኤልያስም መሰከረ፡፡ 
ሐ- በፊልጶስ ቂሳርያ ጌታ ሐዋርያትን ‹ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል?› ብሎ በጠየቃቸው ጥያቄ ሲመልሱ ሙሴ ነው ይሉሃል ፤ እንዲሁም የኃይል ስራህን ተመልክተው ኤልያስ ነህ ይሉሃል ብለው ነበርና ሙሴን ከመቃብር ፤ ኤልያስን ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ እግዚአ ሙሴ ፤ አምላከ ሙሴ ፤ እግዚአ ኤልያስ ፤ አምላከ ኤልያስ መሆኑን ለማስመስከር፡፡
ታቦር ተራራ የዛሬ ገጽታው ከሩቅ ዕይታ
ታቦር ተራራ የወንጌል ምሳሌ
1.     ተራራ ሲወጡት ያደክማል፣ ከወጡት በኋላ ግን ጭንጫውን፣ ግጫውን ሲያሳይ ደስ ያሰኛል፡፡ ወንጌልም ሲማሯት ትከብዳለች በኋላ ግን ጽድቅን እና ኃጢአትን ለይታ ስታሳውቅ ደስ ታሰኛለች፡፡

ታቦር ተራራ የቤተክርስቲያን ምሳሌ
1.     በታቦር ተራራ ከብሉይ ኪዳን ነቢያት ኤልያስና ሙሴን፣ ከሐዲስ ኪዳን ሦስቱን ሐዋርያት እንደተገኙ በቤተክርስቲያን ብሉይ ከሐዲስ እንዲነገር ለማጠየቅ ፤ ሐዋርያት የሰበኩት ወንጌል አስቀድመው ነቢያት በምሳሌና በትንቢት የተናገሩት እንደሆነ ሲያስረዳ ነው ፡፡ ነቢያት በቀየሱ ሐዋርያት ገሰገሱ እንዲል ‹በሐዋርያት በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል›ኤፌ 2፣20
2.    በታቦር ተራራ ከመዓስባን (ባለትዳር) ሙሴን ከደናግል ደግሞ ኤልያስ እንደተገኙ በቤተክርስቲያን በድንግልና የሚኖሩ መናንያን መነኮሳትም፣ በሕግ በሥርዓት የሚኖሩ ባለትዳሮችም ይገኛሉና፡፡
ታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ
1.     ተራራውን ችግር እንዲወጡት መንግሥተ  ሰማያትንም በብዙ መከራ የምትገኝ ናትና ‹እስመ  በብዙኅ ጻማ ወድካም ኀለወነ ንባአ ለመንግሥተ እግዚአብሔር› ‹ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል› ሐዋ 14፡22
2.    በታቦር ተራራ የብሉይ ኪዳን ነቢያት፣ ከሐዲስ ኪዳን ሐዋርያት እንደተገኙ መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም፣ ሐዋርያትም አንድ ሆነው እንደሚወርሷት ያጠይቃል፡፡
3.    በታቦር ተራራ ከመዓስባን ሙሴ፣ ከደናግል ደግሞ ኤልያስ እንደተገኙ መንግሥተ ሰማያትን  ደናግልም መዓስባንም በአንድ ላይ እንዲወርሷት ያጠይቃል፡፡
4.    በታቦር ተራራ ሞተው ከተቀበሩት መካከል ሙሴን አመጣ፣ በብሔረ ሕያዋን ካሉት ደግሞ ኤልያስን አመጣ መንግሥተ ሰማያትንም ሞተው የተቀበሩትም በብሔረ ሕያዋን ያሉትም በአንድነት እንደሚወርሷት ያጠይቃል፡፡
በአጠቃላይ ታቦር ተራራ፡-
1.     የክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት የተመሠከረበት፣
2.    የምስጢረ ሥላሴ ትምህርት የተሰጠበት
3.    ፈጣሪ ከቅዱሳን ሰዎቹ ጋር የተገኘበት
4.    በልበ ሐዋርያት የነበረ ሰይጣን ድል የተደረገበት 
5.    የሐዋርያት በተለይም የሦስቱ ባለሟልነት የተገለጠበት፣
6.    አሉባልታና ተራ ወሬ የከሸፈበት፣
7.    የቅዱሳንን ክብር ለሚያናንቁ ተራራም እንኳን ‹ቅዱስ› እንደሚባል የተማሩበት፣
8.    የብሔረ ሕያዋን መኖር የተመሰከበረበት
9.    የትንሣኤ ሙታን ዋስትና የተገለጠበት የክብር ሰገነት፣ የምስጢረ መቅደስ፣ ታላቅ ትምህርት ቤትም ጭምር ነው፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታ ሆይ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው ማለቱ
1.     የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት በሚታመንበት፣ ዋልድ ዋሕድ በምትለው ሃይማኖት መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡
2.    መድኃኔዓለም  ከቅዱሳን ወዳጆቹ ጋር በምትገኝበት አንተ እያበላኸን እየፈወስከን፣ ሙሴ ደመና እየጋረደ መና እያወረደ ባሕር እየከፈለ፣ ኤልያስ ሰማይ እየለጐመ እሳት እያዘነመ ዝናም እያቆመ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡
3.    በልበ ሐዋርያት ያደረ ሰይጣን ድል በተደረገበት በታቦር ተራራ ምሳሌ አንድም በወንጌል ሕይወት፣ አንድም በቤተ ክርስቲያን መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡

ፈጣሪያችን እግዚአብሔር እስከመጨረሻዋ ሕቅታ (እስትንፋስ) በታቦር ተራራ በተመሰለች ቤተክርስቲያን በሃይማኖታችን ጸንተን የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች የስሙ ቀዳሾች እንድንሆን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡

25 comments:

  1. GOD bless you GOD always help you. You are a blessing to us. Amlak lante yemitastemirbetin legna yeminredabetin tibeb yisten.

    ReplyDelete
    Replies
    1. qalehiwot Yasemalen tebarek

      MelakuT.

      Delete
  2. Amen!Amen!Amen! kale hiwotn yasemaln. yabertaln! eregim yagelglot zemenn yadliln!
    Tsion

    ReplyDelete
  3. እግዚአብሔር ይስጥልን
    መሥፍን እዘዘው

    ReplyDelete
    Replies
    1. እግዚአብሔር ይስጥልን

      Delete
  4. ejig betam tiru ena astemari Blog newe. sele-eyandandu kebere beale yemisetewe temeheret des yilal coz yemanawekewen enawekalen yeresanewen enasetawesalen. ye lemadun sayhone haymanotawiwen merja enizebetalen. I like it very much I have never put any comments on any Blog Before. But now I am v.much happy. For those of us who can't follow preaching @the church due to time constraint, this Blog will help us to read & know many things. keep writing. Let God help U to help others.

    Yemiak

    ReplyDelete
  5. kale hiywet yasemalin AMEN!

    ReplyDelete
  6. Qale Hiwot yasemalin

    ReplyDelete
  7. ርብቃ ከጀርመንAugust 18, 2011 at 9:35 PM

    እንኩዋን አብሮ አደረሰን እግዚአብሄ ይስጥልን ወቅታዊ የሆነ ትምህርትነው አገልግሎትህን እግዚአብሄር ይባርክልህ ከማያልቀው የውቀት ጸጋው በቸርነቱ ይለግስህ እንዳልከውም እስከመጨረሻው እስትፋሳችን የብርሀን መገለጫ ከሆነችው ተዋህዶ ሀይማኖታችንና ከቅድስት ቤተክርስቲያናችን አይለየን አሜን!

    ReplyDelete
  8. እግዚአብሄ ይስጥልን ወቅታዊ የሆነ ትምህርትነው አገልግሎትህን እግዚአብሄር ይባርክልህ ከማያልቀው የውቀት ጸጋው በቸርነቱ ይለግስህ እንዳልከውም እስከመጨረሻው እስትፋሳችን የብርሀን መገለጫ ከሆነችው ተዋህዶ ሀይማኖታችንና ከቅድስት ቤተክርስቲያናችን አይለየን አሜን!

    ReplyDelete
  9. Amen
    Kale Hiwot Yasemalin
    Mengiste Semayat Yawursilin
    Rejim Edme Ena Tena Yistilin

    ReplyDelete
  10. ቃለ ህይወት ያሰማልን እግዚአብሔር በረከቱን ያብዛልህ

    ReplyDelete
  11. diacon melaku ezezew amlak yatsinah betam temechitognal.bezihiw ketil

    ReplyDelete
  12. Dkon Solomon Addisu said ...
    Atlanta

    Kale heowt ysamalnInkon abro adrsen menfswe wendma.

    ReplyDelete
  13. ቃለ ህይወትን ያሰማልን! መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን እንጅነር ዲ/ን መልአኩ!!!
    በ እውነት አገልግሎትህን አምላከ ቅዱሳን ይባርክልህ! እግዚአብሔር ብርታቱን ያድልህ!!

    ሳሙኤል ከጀርመን

    ReplyDelete
  14. Kale hiwotn yasemalin! Egziabher yitebikih! Egnanim libona yadilen.

    ReplyDelete
  15. Hello,

    I am from CANADA. I wish i could read you pages. However, our computer has no Amharic font. If you can could u prepare ur articles in pdf format and readable to us please??. This is the practice currently used by DN.Daniel and DN Ephrem. please do yours too.

    Thank you for your cooperation.

    ReplyDelete
  16. አሜን!! ቃለ ሕይወት ያሰማልን! የማይጠገብ፣ የማይሰለች፣ ዘላለማዊ ምግብ አቀረብክልን፡፡ እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጥህ!

    ReplyDelete
  17. amen, kale hiwot yasemalen, mengeste semayaten yawerselen

    ReplyDelete
  18. Amen!Amen!Amen! kale hiwotn yasemaln. yabertaln! eregim yagelglot zemenn yadliln!

    ReplyDelete
  19. ቃለ ህይወትን ያሰማልን!

    ReplyDelete
  20. ቃለ ህይወትን ያሰማልን!

    ReplyDelete
  21. Kale hiwot yasemalen.

    ReplyDelete
  22. this an interesting keep it up .GOD may bless you.

    ReplyDelete
  23. Musé yetenesaw be menfes new weyis sigawn tewahido neber??

    ReplyDelete