Friday, July 11, 2014

ቅዱስ ጴጥሮስ

ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ ጳውሎስ

እንኳን ለቅዱስ ጴጥሮስ እና ለቅዱስ ጳውሎስ በዓለ ዕረፍት መታሰቢያ ሐምሌ 5 በሰላም አደረሳችሁ



በሸመገልህ ጊዜ እጆችህን ትዘረጋለህ ሌላውም ያስታጥቅኻል ወደማትወደውም ይወስድሀል  
                  ዮሐ. 21÷18

ቅዱስ ጴጥሮስ




ቅዱስ ጴጥሮስ  የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው ቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ዮሐ. 1፥45፡፡ የአባቱ ስም ዮና ሲሆን ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው፡፡ ዮና ከነገደ ስምዖን የምትሆን አንዲት ሴት አግብቶ ቅዱስ ጴጥሮስን ወለደ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ከተወለደ በኋላ እንደ ሕገ ኦሪት ትእዛዝ በስምንተኛው ቀን ወደ ግዝረት ቤት አግብተው ስሙን በእናቱ ነገድ ስም ስምዖን ብለው ሰይመውታል፡፡
      እድሜው አምስት ዓመት ሲሆን እንደ አይሁድ ሥርዓት ሕገ ኦሪትን እየተማረ እንዲያድግ በቤተ ሳይዳ አጠግብ ወደሚገኘው ወደ ቅፍርናሆም ሰደዱት፡፡ በዘመኑ በባህር ዳር በምትገኘውና ታላቅ የንግድ መናኸርያ በነበረችው በፍቅር ናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረችው በቅፍርናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረው ኢያኢሮስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት አሰርቶት በነበረው ምኩራብ እየተማረ አደገ፡፡
    
ከዚያም በኋላ በዚያ ከተማ ቤት ሰርቶ ኮን ኮርድያ (ጴርጴቱዋ) የምትባል ሚስት አግብቶ እንደ አባቱ እንደ ዮና ዓሣ እያጠመደና እየሸጠ ይኖር ጀመር፡፡
     ወቅቱ ጌታችን በቸርነቱ በሞት ጥላ የሚኖሩትን የአዳምን ልጆች ከፍዳና ከመርገም ለማዳን ስለ ወደደ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ሰው ሆኖ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሐዋርያትን በሚጠራበት ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስን ከወንድሙ ከእስክንድርያ ጋር በጥብርያዶስ ባሕር መረቡን ዘርግቶ ዓሣ ሲያጠምድ «ከእንግዲህ በወንጌል መረብነት ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ» ብሎ አስከተለው፡፡
     ጌታችን ለአዳም የሰጠውን ተስፋ ፈጽሞ ከማረጉ በፊት በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ለደቀ መዛሙርቱ እንደገና በተገለጠ ጊዜ ምሳ ከበሉ በኋላ ጌታችን ስምዖን ጴጥሮስን  « የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?» አለው፡፡ እርሱም  «እንድወድህ አንተ ታውቃለህ» ብሎ መለሰለት ጌታም « ግልገሎቼን አሰማራ፥ ጠቦቶቼን ጠብቅ ፥ በጎቼን አሰማራ እውነት እውነት እልኻለሁ አንተ ጎልማሳ ሳለህ ወገብህን በገዛ ራስህ ታጥቀህ ወደምትወደው ትሄድ ነበር፡፡ ነገር ግን በሸመገልህ ጊዜ እጆችህን ትዘረጋለህ ሌላውም ያስታጥቅኻል ወደማትወደውም ይወስድሀል » አለው ፡፡ በምን ዓይነት ሞት እግዚአብሔርን ያከብር ዘንድ እንዳለው ሲያመለክት ይህን አለ፡፡ ዮሐ.21፥15-10፡፡
     ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ ሮማ ከመሄዱ አስቀድሞ በኢየሩሳሌምና በሰማርያ ; በልዳና በኢዮጴ በአንጾኪያና በትንሽ እስያ በጳንጦስና በቀጰዶቅያ በገላትያና በቢታንያ እነዚህንም በመሰሉ በሌሎች አገሮች እየዞረ አስተምሮ ሕዝቡንና አሕዛብን በክርስቶስ አሳምኖ በመጨረሻ በዓቱን በሮም አጸና፡፡
     ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም የወንጌል አርበኛ ሆኖ የቃለ እግዚአብሔርን ዝናር በወገቡ ታጥቆ ርኩሳን መናፍስትን በቃለ ወንጌል እያሳደደ ክርስትናን ባእድ አምልኮ ቀስፎ በያዛት በሮም ምድር እያስፋፋ ሳለ አንድ ያልታሰበ ነገር ተከሰተ፡፡
     ታላቋን የሮም ከተማ የፅልመት ሠራዊት ከቧታል በሰማይ ላይ የፈሰሱት ከዋክብት እርስ በእርሳቸው ከመጠቃቀስ በስተቀር ለከተማዋ ብርሃናቸውን በመለገስ ጨለማውን በመጠኑም አላስወገዱላትም፡፡ ሞቃቱ የምሽት ነፋስ የሮም ከተማን ይዞራል፡፡
  
የሮም ከተማ እሳት ቃጠሎ
ከመሃል ከተማው የፈነጠቀው ውጋገን በአንድ ጊዜ እንደ ሞት ከብዶ የነበረውን ጨለማ ገፎ ከተማዋን በብርሃን ጎርፍ እንድትጥለቀለቅ አደረገ ፡፡ የእሳቱ ነበልባል እየተጎረደ፣ እየተጎረደ ግዛቱን ያሰፋል የእሳቱ ቃጠሎ መላ የሮም ከተማን ባጭር ጊዜ አጥለቀለቃት ፡፡ ከተማዋ በእሳት ባህር ተከበበች፡፡ ታላላቅ ቤቶች የእሳት ራት ሆኑ፡፡ ቤተ መቅደሶቹ ፈራረሱ ሱቆች በውስጣቸው ከያዙት ዕቃ ጋር አመድ ሆኑ፡፡ ነገር ግን የእሳቱን አደጋ በቁጥጥር ሥር ማዋል አልተቻለም፡፡ አንድ ጊዜ ፎክሮ የመጣ ይመስል የነበረውን እንዳልነበር አድርጎ አፍርሶና አወዳድሞ ከስድስት ቀን በኋላ ፀጥ ረጭ አለ፡፡
     የሮም ከተማ ሕዝብ የብርቅየ ከተማውን አሳዛኝ ፍፃሜ በሐዘን ተውጦ ተመለከተው ፡፡ ከበርቴዎች ባዶ እጃቸውን አጨብጭበው ቀሩ ፡፡ ብዙ የሮሜ ሰዎች ቤት አልባ ሆኑ፡፡
      የእሳት ቃጠሎው መንስዔ ምን እንደሆነ በውል ባይታወቅም የሮም ሕዝብ ግን በይሆናል ማውራት የጀመረው ወዲያውኑ ነበር ፡፡ በስፋት ይወራ የነበረው የእሳት አደጋ በተነሳበት ወቅት ኔሮን ቄሳር በቤተ መንግስቱ ሠገነት ላይ የተዋናይ ልብስ ለብሶ በገናውን እየደረደረ ሲዘፍን ታይቷል የሚለው ሲሆን በዚህም በእሳቱ ቃጠሎ የኔሮን እጅ አለበት እየተባለ ስለተወራም ምንም እንኳን ኔሮን በዚያ ምሽት ከሮም ከተማ ብዙ ርቆ በሚገኘው ባማረ ቤተ መንግስቱ የነበር ቢሆንም ይህን የህዝቡን ሐሜት ለማስለወጥ ዘዴ ያውጠነጥን ጀመር፡፡
ኔሮን ቄሣር
የእሳቱን ቃጠሎም በሚጠላቸው ክርስቲያኖች ላይ አሳበበ  አማልክቶች በክርስቲያኖች ሥራ ስላልተደሰቱ በቁጣ ሮምን ኣቃጠሏት ብሎ አስወራ፡፡ ይህንንም ለሕዝቡ እንዲሠራጭ አደረገ፡፡ በዚህ የተነሣ ብዙ ክርስቲያኖች ከያሉበት ታድነው በአሠቃቂ ሁኔታ መሥዋዕት ሆኑ ፡፡
     የኔሮን ቄሣር የቅርብ ባልንጀሮች የሆኑት የአልቢኖስና አግሪጳ ሚስቶች በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት ተማርከው ክርስቲያን ሆነው ስለነበር ባሎቻቸው በእርሱ ላይ የሸረቡበትን ሤራ ሄደው በመንገር ከሀገር እንዲወጣ ቅዱስ ጴጥሮስን ግድ አሉት፡፡ እርሱም ለክርስቶስ ታማኝ ወታደር ሆኖ በወንጌል ተጋድሎው ጸንቶ በሰማዕትነት ማለፍ እንዳለበት ቢነገራቸውም እነርሱ ግን ስለ እነርሱና ስለሌሎች ክርስቲያኖች ሲል ለጥቂት ጊዜ በሕይወት መኖሩ ለወንጌል አገልግሎት እንደሚጠቅም ገልጸውለት መሸሹ አማራጭ የሌለው መሆኑን በማሰብ ከሮም ከተማ ወጥቶ ሲሄድ በሮም መግቢያ መውጫ በር ወደ እሱ እየተራመደ የሚመጣ ሰው አየ፡፡
ያም ስው ወደ ሮም ቅጥር እየተጠጋ መጣ፡፡ ለካስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ኑሮአል፡፡ ጴጥሮስም ደንግጦ  ጌታዬ ወዴት ነው የምትሄደው ብሎ ጠየቀው ጌታም  ጴጥሮስ፣ ዳግመኛ በሮም ልሰቀል መሄዴ ነው  ብሎ መለሰለት፡፡
     ቅዱስ ጴጥሮስም የራእዩ ምስጢር ስለገባው ወደ ሮም ከተማ ተመልሶ ድምፁን ከፍ አድርጎ ስለተሰቀለው ጌታ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ጀመረ ፡፡ በዚህ ጊዜ ከኔሮን ቄሣር የታዘዙ አራት ወታደሮች ጴጥሮስን እጁን በሰንሠለት አሥረው ፍርዱ ወደሚፈፀምበት ሥፍራ ወሰዱት ፡፡ ይገደልበት ዘንድ የተዘጋጀለትን መስቀል ፊት ለፊት እንዳየ ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ አለ    ወደ ላይ አትስቀሉኝ እኔ ከጌታዩ እኩል አይደለሁምና ዳሩ ግን ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ 
      ሰቃዮችም ቅዱስ ጴጥሮስን እንደ ተናገረው ዘቅዝቀው ሰቀሉት ፡፡ ጌታ በሸመገልህ ጊዜ እጆችህን ትዘረጋለህ እንዳለው  ሁሉ በተወለደ በ85 ዓመቱ በ67 ዓ.ም ሐምሌ 5 ቀን እጁን ለችንካር ዘረጋ፡፡ ዮሐ.21÷18::
     ክርስቲያኖች ወገኖች የሃይማኖት ልጆች አለቀሱለት ሥጋውንም በሮም ከተማ አሳረፋት፡፡ ከሦስት መቶ ዓመትም በኋላ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ በመቃብሩ ላይ ቤተክርስቲያን አሠራበት፡፡
      እንግዲህ እኔ ከእነሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ ፡፡ በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔር መንጋ ጠብቁ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳየሆን በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጎብኙት ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ $ 1ጴጥ.5÷1-4::
የቅዱስ ጳውሎስን ደግሞ በሚቀጥለው ይጠብቁ
   የአባታችን የቅዱስ ጴጥሮስ የአባታችን የቅዱስ ጳውሎስ ጸሎትና በረከ በሁላችን ይደርብን አሜን         !ይቆየን
ዋቢ   ስንክሳር ሐምሌ 5
       ዜና ሐዋርያት
       ሐመር መጽሔት

24 comments:

  1. ቃለ ህይወት ያሰማልን::

    ReplyDelete
  2. Diakon,
    Girum newu.

    It would be good if verses are under quotation like 1ጴጥ.5÷1-4

    ReplyDelete
  3. ልበ እግዚአብሄር የተባለው ዘማሪው ቅዱስ ዳዊት በምዕራፍ 19።4 “ ድምጻቸው ወደ ምድር ሁሉ፤ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ” በማለት አስቀድሞ ስለ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስም ጭምር በትንቢታዊ መልኩ መናገሩ ይታመናል፣ ከዚህ ተነስተውም የቤተክርስትያን ሊቃውንቶች በግእዝ “አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ፤ ውስተ ኵሉ ምድር ወጽአ ነገሮሙ፤ ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ፣” በማለት የነዚህን ዕንቁ የሆኑ የቤተክርስትያን አባቶች የወንጌል የምስክርነት ገድል ልብ በሚያዋልል ዜማ ያውጃሉ፣ መልአኩ፤ ይህ ቅልብጭብጭ ያለ የቅዱስ ጴጥሮስ ታሪክ። በጣም ደስ ይላል፤ አልፎ አልፎ ማለትም ሰው እንዳሰለች ሳይበዛ፤ የግዕዝ ጥቅሶችን ከነ ትርጉሙ ብትጨምርበት። ቀስ በቀስ የግእዝ ቃላቶችንና የሊቃውንት አባቶችን የመንፈሳዊ ዕውቀት ጥልቀት እንድንረዳና፤ ከእነሱም እንድንማር የሚረዳን ሆኖ ይሰማኛል፣ በርታልን እስቲ ክቡሩ ወንድማችን!!!

    ልጃም

    ReplyDelete
  4. amen enQne abero aderesen dn mele
    የአባታችን የቅዱስ ጴጥሮስ የአባታችን የቅዱስ ጳውሎስ ጸሎትና በረከት በሁላችን ይደርብን amen

    ReplyDelete
  5. Berta wendimachin. Hinedzih ayinet bizu yasifeligenal.

    Tatek

    ReplyDelete
  6. I think it would be the beginning of Ur long dream. Keep going please

    ReplyDelete
  7. Why U R staring me like this(Your profile photo)?

    ReplyDelete
  8. Kale Hiwot Yasemalin. Sewoch yebetekiristianen astemihiro lemekeyer bemimokrubet beahunu gize lemiemenan yemiyasfelgew endezih aynet timihirt new.

    ReplyDelete
  9. kale hiwet yasemalin ageliglothn yibark.

    ReplyDelete
  10. I like all the posts on this site. However i had one expectation as a christian, i expected to get more posts about our creator, Savior & Lord Jesus Christ than about the saints; cause after all, our salvation depends only on our Savior Jesus Christ & it matters more, so pls take my suggestion positively- since it's according to the word of z almighty. "keep your eyes on the Christ."

    ReplyDelete
  11. Qale Hiwot yasemalin wondmachin Dn Melaku. Berta Egziabiher besirah hulu yiqdemih.

    Dear last Anonymous august 14 2011 11:17 PM, there are so many blogs which are writing about the Holy Savior. Hence, you can visit them. This blog fills the gap which was not covered by the other blogs. In addition don't forget that when ever we are talking about Saints God is the center for we are always talking about the power, wisdom, patience, hope. mercy... that God gives them. Without the help of God the Saints can't do anything. So, we never separate God from Saints and dare to talk about them time and then for ever and ever. So, if you gave the comment unknowingly it is okay you can ask the church fathers for the details. If you are differently I beg you to come to your heart and think of your self. May God help us to abide to His words and be a citizen of His Kingdom during the last Judgement. Amen.

    ReplyDelete
  12. Sorry dear readers I wrongly posted my comment for the last anonymous on August 14, 2011 11:17 PM which doesn't exist at all. So my comment goes to the last anonymous dated August 7, 2011 12:32 PM

    ReplyDelete
  13. inspirational history. i wish the current fathers read this again and again

    ReplyDelete
  14. amen, kale hiwot yasemalen.

    ReplyDelete
  15. kalehiwot yasemalin!!!

    ReplyDelete
  16. GOD bless you Mele! Kale hiwot yasemalin!

    ReplyDelete
  17. Amen!!! Kale hiwot yasemalin.

    ReplyDelete
  18. kale hiwot yasemalin!

    ReplyDelete
  19. Amen, Kale Hiwote Yasemalen,Amen

    ReplyDelete
  20. ቃለ ህይወትን ያሰማልን

    ReplyDelete